ኢያሱ
15 ለይሁዳ ነገድ ለየቤተሰቡ በዕጣ የተሰጠው ርስት+ እስከ ኤዶም+ ይኸውም እስከ ጺን ምድረ በዳና እስከ ኔጌብ ደቡባዊ ጫፍ ድረስ ይዘልቃል። 2 ደቡባዊው ወሰናቸው ከጨው ባሕር* ዳርቻ+ ይኸውም ከባሕሩ ደቡባዊ ወሽመጥ ይነሳል። 3 ከዚያም በስተ ደቡብ እስከ አቅራቢም አቀበት+ ድረስ ይዘልቅና ወደ ጺን ይሻገራል፤ በመቀጠልም ከደቡብ ወደ ቃዴስበርኔ+ ይወጣና በኤስሮን በኩል አልፎ ወደ አዳር ከሄደ በኋላ ወደ ቃርቃ ይዞራል። 4 ከዚያም ወደ አጽሞን+ ይዘልቅና ወደ ግብፅ ሸለቆ*+ ይቀጥላል፤ ወሰኑም ባሕሩ* ጋ ሲደርስ ያበቃል። ደቡባዊ ወሰናቸው ይህ ነበር።
5 ምሥራቃዊው ወሰን ደግሞ ጨው ባሕር* ሲሆን ይህም እስከ ዮርዳኖስ ጫፍ ይደርሳል፤ በስተ ሰሜን በኩል ያለው ወሰን በዮርዳኖስ ጫፍ ላይ የሚገኘው የባሕሩ ወሽመጥ ነበር።+ 6 ከዚያም ወሰኑ ወደ ቤትሆግላ+ ይወጣና ከቤትአረባ+ በስተ ሰሜን በኩል ያልፋል፤ የሮቤል ልጅ የቦሃን ድንጋይ+ እስካለበትም ድረስ ይዘልቃል። 7 በመቀጠልም በአኮር ሸለቆ*+ ወደምትገኘው ወደ ደቢር ይወጣና በስተ ሰሜን ወደ ጊልጋል+ ይኸውም ከሸለቆው በስተ ደቡብ ከሚገኘው ከአዱሚም አቀበት ፊት ለፊት ወዳለው ቦታ ይታጠፋል፤ ከዚያም ወደ ኤንሼሜሽ+ ውኃዎች ይሄድና ኤንሮጌል+ ላይ ያበቃል። 8 ወሰኑ እስከ ሂኖም ልጅ ሸለቆ+ ይኸውም በስተ ደቡብ እስከሚገኘው እስከ ኢያቡሳውያን+ ሸንተረር ማለትም እስከ ኢየሩሳሌም+ ድረስ ይወጣል፤ በተጨማሪም በረፋይም ሸለቆ* ሰሜናዊ ጫፍ ላይ እስከሚገኘውና ከሂኖም ሸለቆ ምዕራባዊ ክፍል ትይዩ እስካለው ተራራ አናት ድረስ ይዘልቃል። 9 ከዚያም ከተራራው አናት ተነስቶ እስከ ነፍቶአ+ የውኃ ምንጮች ድረስ ይሄዳል፤ እንዲሁም በኤፍሮን ተራራ ላይ እስካሉት ከተሞች ይዘልቃል፤ በመቀጠልም እስከ ባዓላ ማለትም እስከ ቂርያትየአሪም+ ይሄዳል። 10 ወሰኑ ከባዓላ ተነስቶ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ በመዞር ወደ ሴይር ተራራ ይሄዳል፤ ከዚያም በስተ ሰሜን ወደ የአሪም ተራራ ሸንተረር ማለትም ወደ ከሳሎን ያልፋል፤ በመቀጠልም ወደ ቤትሼሜሽ+ በመውረድ ወደ ቲምና+ ይዘልቃል። 11 ወደ ሰሜን አቅጣጫ ወደ ኤቅሮን+ ሸንተረር ከወጣም በኋላ ወደ ሺከሮን ይሄዳል፤ ከዚያም ባዓላ ተራራን አልፎ ወደ ያብነኤል ይወጣል፤ ባሕሩም ጋ ሲደርስ ያበቃል።
12 ምዕራባዊው ወሰን ታላቁ ባሕርና*+ ዳርቻው ነበር። እንግዲህ የይሁዳ ዘሮች በየቤተሰባቸው ወሰናቸው ዙሪያውን ይህ ነበር።
13 ኢያሱ ይሖዋ ባዘዘው መሠረት ለየፎኒ ልጅ ለካሌብ+ በይሁዳ ዘሮች መካከል የምትገኘውን ኬብሮን+ የተባለችውን ቂርያትአርባን ድርሻ አድርጎ ሰጠው (አርባ የኤናቅ አባት ነበር)። 14 በመሆኑም ካሌብ የኤናቅ+ ዘሮች የሆኑትን ሦስቱን የኤናቅ ልጆች ማለትም ሸሻይን፣ አሂማንን እና ታልማይን+ ከዚያ አባረራቸው። 15 ከዚያ ተነስቶም በደቢር ነዋሪዎች ላይ ዘመተ።+ (ደቢር ቀደም ሲል ቂርያትሰፈር ትባል ነበር።) 16 ካሌብም “ቂርያትሰፈርን መትቶ በቁጥጥር ሥር ላደረጋት ሰው ሴት ልጄን አክሳን እድርለታለሁ” አለ። 17 የካሌብ ወንድም የሆነው የቀናዝ+ ልጅ ኦትኒኤልም+ ከተማዋን በቁጥጥር ሥር አደረጋት። ስለሆነም ካሌብ ሴት ልጁን አክሳን+ ዳረለት። 18 እሷም ወደ ባሏ ቤት እየሄደች ሳለ ባሏን ከአባቷ መሬት እንዲጠይቅ ወተወተችው። ከዚያም ከአህያዋ ላይ ወረደች።* በዚህ ጊዜ ካሌብ “ምን ፈለግሽ?” ሲል ጠየቃት።+ 19 እሷም “የሰጠኸኝ በስተ ደቡብ* ያለ ቁራሽ መሬት ስለሆነ እባክህ ባርከኝ፤ ጉሎትማይምንም* ስጠኝ” አለችው። ስለዚህ ላይኛውን ጉሎት እና ታችኛውን ጉሎት ሰጣት።
20 የይሁዳ ነገድ በየቤተሰባቸው የተሰጣቸው ርስት ይህ ነበር።
21 በኤዶም+ ወሰን በኩል ባለው የይሁዳ ነገድ ክልል ደቡባዊ ጫፍ ላይ የሚገኙት ከተሞች እነዚህ ናቸው፦ ቃብጽኤል፣ ኤዴር፣ ያጉር፣ 22 ቂና፣ ዲሞና፣ አድዓዳ፣ 23 ቃዴሽ፣ ሃጾር፣ ይትናን፣ 24 ዚፍ፣ ተሌም፣ በዓሎት፣ 25 ሃጾርሃዳታ፣ ቀሪዮትሄጽሮን ማለትም ሃጾር፣ 26 አማም፣ ሼማ፣ ሞላዳ፣+ 27 ሃጻርጋዳ፣ ሄሽሞን፣ ቤትጳሌጥ፣+ 28 ሃጻርሹአል፣ ቤርሳቤህ፣+ ቢዝዮትያ፣ 29 ባዓላ፣ ኢዪም፣ ኤጼም፣ 30 ኤልቶላድ፣ ከሲል፣ ሆርማ፣+ 31 ጺቅላግ፣+ ማድማና፣ ሳንሳና፣ 32 ለባኦት፣ ሺልሂም፣ አይን እና ሪሞን፤+ በአጠቃላይ 29 ከተሞች ከነመንደሮቻቸው ነበሩ።
33 በሸፌላ+ የነበሩት ከተሞች እነዚህ ናቸው፦ ኤሽታዖል፣ ጾራ፣+ አሽና፣ 34 ዛኖሃ፣ ኤንጋኒም፣ ታጱአ፣ ኤናም፣ 35 ያርሙት፣ አዱላም፣+ ሶኮህ፣ አዜቃ፣+ 36 ሻአራይም፣+ አዲታይም፣ ገዴራ እና ገዴሮታይም፤* በአጠቃላይ 14 ከተሞች ከነመንደሮቻቸው ነበሩ።
37 ጸናን፣ ሃዳሻ፣ ሚግዳልጋድ፣ 38 ዲልአን፣ ምጽጳ፣ ዮቅተኤል፣ 39 ለኪሶ፣+ ቦጽቃት፣ ኤግሎን፣ 40 ካቦን፣ ላህማም፣ ኪትሊሽ፣ 41 ገዴሮት፣ ቤትዳጎን፣ ናዕማ እና መቄዳ፤+ በአጠቃላይ 16 ከተሞች ከነመንደሮቻቸው ነበሩ።
42 ሊብና፣+ ኤቴር፣ አሻን፣+ 43 ይፍታህ፣ አሽና፣ ነጺብ፣ 44 ቀኢላ፣ አክዚብ እና ማሬሻህ፤ በአጠቃላይ ዘጠኝ ከተሞች ከነመንደሮቻቸው ነበሩ።
45 ኤቅሮን እንዲሁም በሥሯ* ያሉት ከተሞችና መንደሮቿ። 46 ከኤቅሮን በስተ ምዕራብ በአሽዶድ በኩል ያሉት አካባቢዎች በሙሉና መንደሮቻቸው።
47 አሽዶድ+ እንዲሁም በሥሯ* ያሉት ከተሞችና መንደሮቿ፤ ጋዛ+ እንዲሁም በሥሯ ያሉት ከተሞችና መንደሮቿ እስከ ግብፅ ሸለቆ፣ እስከ ታላቁ ባሕርና* በባሕሩ ጠረፍ እስካለው አካባቢ ድረስ።+
48 በተራራማው አካባቢ የነበሩት ከተሞች እነዚህ ናቸው፦ ሻሚር፣ ያቲር፣+ ሶኮህ፣ 49 ዳና፣ ቂርያትሳና ማለትም ደቢር፣ 50 አናብ፣ ኤሽተሞህ፣+ አኒም፣ 51 ጎሸን፣+ ሆሎን እና ጊሎ፤+ በአጠቃላይ 11 ከተሞች ከነመንደሮቻቸው ነበሩ።
52 ዓረብ፣ ዱማ፣ ኤሽዓን፣ 53 ያኒም፣ ቤትታጱአ፣ አፌቃ፣ 54 ሁምጣ፣ ቂርያትአርባ ማለትም ኬብሮን+ እና ጺኦር፤ በአጠቃላይ ዘጠኝ ከተሞች ከነመንደሮቻቸው ነበሩ።
55 ማኦን፣+ ቀርሜሎስ፣ ዚፍ፣+ ዩጣ፣ 56 ኢይዝራኤል፣ ዮቅደአም፣ ዛኖሃ፣ 57 ቄይን፣ ጊብዓ እና ቲምና፤+ በአጠቃላይ አሥር ከተሞች ከነመንደሮቻቸው ነበሩ።
58 ሃልሁል፣ ቤትጹር፣ ጌዶር፣ 59 ማአራት፣ ቤትአኖት እና ኤልተቆን፤ በአጠቃላይ ስድስት ከተሞች ከነመንደሮቻቸው ነበሩ።
60 ቂርያትበኣል ማለትም ቂርያትየአሪም+ እና ራባ፤ በአጠቃላይ ሁለት ከተሞች ከነመንደሮቻቸው ነበሩ።
61 በምድረ በዳው የነበሩት ከተሞች እነዚህ ናቸው፦ ቤትአረባ፣+ ሚዲን፣ ሰካካ፣ 62 ኒብሻን፣ የጨው ከተማ እና ኤንገዲ፤+ በአጠቃላይ ስድስት ከተሞች ከነመንደሮቻቸው ነበሩ።
63 የይሁዳ ሰዎች በኢየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩትን+ ኢያቡሳውያንን+ ሊያባርሯቸው አልቻሉም ነበር፤+ ስለሆነም ኢያቡሳውያን እስከ ዛሬ ድረስ ከይሁዳ ሰዎች ጋር በኢየሩሳሌም ይኖራሉ።