ኢሳይያስ
መንፈሴን በዘርህ ላይ፣
በረከቴንም በልጅ ልጆችህ ላይ አፈሳለሁ።+
ሌላውም ራሱን በያዕቆብ ስም ይጠራል፤
ሌላው ደግሞ በእጁ ላይ “የይሖዋ ነኝ” ብሎ ይጽፋል።
ደግሞም ራሱን በእስራኤል ስም ይጠራል።’
‘የመጀመሪያው እኔ ነኝ፤ የመጨረሻውም እኔ ነኝ።+
ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም።+
በድፍረት ይናገር፤ ያሳውቅም፤ ማስረጃውንም ለእኔ ያቅርብ!+
የጥንቱን ሕዝብ ካቋቋምኩበት ጊዜ ጀምሮ፣
በቅርቡ የሚከሰቱትንና
ወደፊት የሚሆኑትን ነገሮች ይናገሩ።
አስቀድሜ ለእያንዳንዳችሁ አልነገርኳችሁም? ደግሞስ አላሳወቅኳችሁም?
እናንተ ምሥክሮቼ ናችሁ።+
ከእኔ ሌላ አምላክ አለ?
በፍጹም፣ ሌላ ዓለት የለም፤+ እኔ የማውቀው አንድም የለም።’”
የእጅ ጥበብ ባለሙያዎቹ ተራ ሰዎች ናቸው።
ሁሉም ተሰብስበው ይቁሙ።
በፍርሃት ይዋጣሉ፤ ሁሉም ያፍራሉ።
12 አንጥረኛ በመሣሪያው* ተጠቅሞ ብረቱን በከሰል ፍም ላይ ይሠራዋል።
ብርቱ በሆነው ክንዱ
በመዶሻ ቅርጽ ይሰጠዋል።+
ከዚያም ይርበዋል፤ ጉልበትም ያጣል፤
ውኃ ስለማይጠጣ ይደክማል።
13 እንጨት ጠራቢው በገመድ ይለካል፤ በቀይ ጠመኔም ንድፍ ያወጣል።
በመሮም ይጠርበዋል፤ በማክበቢያም ምልክት ያደርግበታል።
14 አርዘ ሊባኖስ የሚቆርጥ ሰው አለ።
እሱም አንድ የዛፍ ዝርያ ይኸውም የባሉጥ ዛፍ ይመርጣል፤
እስኪጠነክርለት ድረስ በጫካው ውስጥ ባሉት ዛፎች መካከል ይተወዋል።+
የላውሮ ዛፍ ይተክላል፤ ዝናብም ያሳድገዋል።
15 ከዚያም ሰው ለማገዶ ይጠቀምበታል።
የተወሰነውን እንጨት ወስዶ በማንደድ እሳት ይሞቃል፤
እሳት አያይዞም ዳቦ ይጋግራል።
ይሁንና አምላክ ሠርቶም ያመልከዋል።
የተቀረጸ ምስል ሠርቶበት በፊቱ ይደፋል።+
16 ግማሹን በእሳት ያነደዋል፤
በዚያም ላይ የሚበላውን ሥጋ ይጠብሳል፤ በልቶም ይጠግባል።
እሳቱንም እየሞቀ
“እሰይ! እሳቱን እያየሁ ሞቅኩ” ይላል።
17 የቀረውን ግን ምስል ይቀርጽበታል፤ አምላክ አድርጎም ይሠራዋል።
በፊቱም ተደፍቶ ይሰግድለታል።
“አንተ አምላኬ ነህና አድነኝ” ብሎ
ወደ እሱ ይጸልያል።+
19 ቆም ብሎ በልቡ ያሰበ
ወይም እውቀትም ሆነ ማስተዋል ኖሮት እንዲህ ብሎ የተናገረ የለም፦
“ግማሹን እሳት አንድጄበታለሁ፤
በፍሙም ላይ ዳቦ ጋግሬአለሁ፤ ሥጋም ጠብሼ በልቻለሁ።
ታዲያ በቀረው እንጨት አስጸያፊ ነገር መሥራቴ ተገቢ ነው?+
ከዛፍ ለተቆረጠ እንጨት* መስገድ ይገባኛል?”
20 እሱ አመድ ይበላል።
የተታለለው የገዛ ልቡ አስቶታል።
ራሱን* ሊያድን አይችልም፤
ደግሞም “በቀኝ እጄ ያለው ውሸት አይደለም?” አይልም።
21 “ያዕቆብ ሆይ፣ አንተም እስራኤል ሆይ፣
አገልጋዬ ስለሆንክ እነዚህን ነገሮች አስታውስ።
እኔ ሠርቼሃለሁ፤ አንተ የእኔ አገልጋይ ነህ።+
እስራኤል ሆይ፣ አልረሳህም።+
ወደ እኔ ተመለስ፤ እኔም እቤዥሃለሁ።+
23 እናንተ ሰማያት በደስታ እልል በሉ!
ይሖዋ እርምጃ ወስዷልና።
እናንተ ጥልቅ የምድር ክፍሎች በድል አድራጊነት ጩኹ!
እናንተ ተራሮች፣ አንተም ደን ሆይ፣
በውስጡም ያላችሁ ዛፎች ሁሉ በደስታ እልል በሉ!+
ይሖዋ ያዕቆብን ተቤዥቷልና፤
በእስራኤልም ላይ ግርማውን ገልጧል።”+
“ሁሉንም ነገር የሠራሁ እኔ ይሖዋ ነኝ።
ያኔ ከእኔ ጋር ማን ነበር?
25 የሆነ ያልሆነውን የሚቀባጥሩ ሰዎችን* ምልክቶች አከሽፋለሁ፤
ሟርተኞችንም ነፈዝ አደርጋለሁ፤+
ጥበበኞቹንም ግራ አጋባለሁ፤
እውቀታቸውንም ሞኝነት አደርጋለሁ፤+
26 የአገልጋዬን ቃል እውን አደርጋለሁ፤
የመልእክተኞቼንም ትንቢት ሙሉ በሙሉ እፈጽማለሁ፤+
ስለ ኢየሩሳሌም ‘የሰው መኖሪያ ትሆናለች’፤+
ስለ ይሁዳ ከተሞችም ‘ዳግም ይገነባሉ፤+
ፍርስራሾቿንም መልሼ እሠራለሁ’+ እላለሁ፤
27 ጥልቁን ውኃ ‘ደረቅ ሁን፤
ወንዞችህንም ሁሉ አደርቃለሁ’+ እላለሁ፤
ፈቃዴንም ሁሉ ሙሉ በሙሉ ይፈጽማል’+ እላለሁ፤
ስለ ኢየሩሳሌም ‘ዳግም ትገነባለች’፤
ስለ ቤተ መቅደሱም ‘መሠረትህ ይጣላል’+ እላለሁ።”