ኢዩኤል
1 ወደ ፐቱኤል ልጅ፣ ወደ ኢዩኤል* የመጣው የይሖዋ ቃል ይህ ነው፦
በእናንተም ዘመን ይሁን በአባቶቻችሁ ዘመን
እንዲህ ያለ ነገር ተከስቶ ያውቃል?+
እናንተ የወይን ጠጅ የምትጠጡ ሁሉ
ጣፋጩ የወይን ጠጅ ከአፋችሁ ላይ ስለተወሰደ ዋይ ዋይ በሉ።+
6 ኃያል የሆነና የሕዝቡ ብዛት ስፍር ቁጥር የሌለው ብሔር ምድሬን ወሮታልና።+
ጥርሶቹ የአንበሳ ጥርሶች ናቸው፤+ መንገጭላውም የአንበሳ መንገጭላ ነው።
7 የወይን ተክሌን አጠፋው፤ የበለስ ዛፌንም ጉቶ አደረገው፤
ቅርፊታቸውን ሙልጭ አድርጎ ልጦ ወዲያ ጣላቸው፤
በቅርንጫፎቻቸው ላይ አንድም ልጥ አልቀረም።
12 ወይኑ ደርቋል፤
የበለስ ዛፉም ጠውልጓል።
ሽማግሌዎቹንና የምድሪቱን ነዋሪዎች ሁሉ ወደ አምላካችሁ ወደ ይሖዋ ቤት ሰብስቡ፤+
እርዳታም ለማግኘት ወደ ይሖዋ ጩኹ።
15 ከቀኑ የተነሳ ወዮላችሁ!
የይሖዋ ቀን ቀርቧልና፤+
ሁሉን ከሚችለው አምላክ ዘንድ እንደ ጥፋት ይመጣል!
16 ምግብ ከዓይናችን ፊት፣
ሐሴትና ደስታም ከአምላካችን ቤት ጠፍቶ የለም?
17 ዘሮቹ* ከአካፋዎቻቸው ሥር ጠውልገዋል።
ጎተራዎቹም ተራቁተዋል።
ጎታዎቹ* ፈራርሰዋል፤ እህሉ ደርቋልና።
18 መንጎቹ እንኳ ሳይቀሩ ያቃስታሉ!
ከብቶቹ ግራ ተጋብተው ይቅበዘበዛሉ፤ መሰማሪያ የላቸውምና!
የበጎቹም መንጋ ቅጣቱን ይቀበላል።
20 የዱር አራዊትም እንኳ አንተን በጉጉት ይጠባበቃሉ፤
ምክንያቱም የውኃ ጅረቶቹ ደርቀዋል፤
በምድረ በዳ ያለውን የግጦሽ መሬትም እሳት በልቶታል።”