ኢዩኤል
2 “በጽዮን ቀንደ መለከት ንፉ!+
በቅዱሱ ተራራዬ ላይ ቀረርቶ አሰሙ።
ስፍር ቁጥር የሌለውና ኃያል የሆነ ሕዝብ ይመጣል፤+
ከዚህ በፊት እንደ እሱ ያለ ፈጽሞ ታይቶ አያውቅም፤
ወደፊትም ከትውልድ እስከ ትውልድ ድረስ
እንደ እሱ ያለ አይኖርም።
3 ከፊቱ ያለውን እሳት ይበላዋል፤
ከኋላው ያለውንም ነበልባል ያቃጥለዋል።+
4 መልካቸው እንደ ፈረስ መልክ ነው፤
እንደ ጦር ፈረሶችም ይጋልባሉ።+
5 በተራሮች አናት ላይ ሲዘሉ የሚሰማው ድምፅ እንደ ሠረገሎች ድምፅ፣+
ገለባንም እንደሚበላ የሚንጣጣ የእሳት ነበልባል ድምፅ ነው።
ለጦርነት እንደተሰለፈ+ ኃያል ሕዝብ ናቸው።
6 ከእነሱም የተነሳ ሕዝቦች ይጨነቃሉ።
የሰውም ፊት ሁሉ ይቀላል።
8 እርስ በርሳቸው አይገፋፉም፤
እያንዳንዱ ሰው መንገዱን ይዞ ይገሰግሳል።
አንዳንዶቹ በመሣሪያ* ተመተው ቢወድቁ እንኳ
ሌሎቹ አይፍረከረኩም።
9 ወደ ከተማዋ እየተጣደፉ ይገባሉ፤ በቅጥርም ላይ ይሮጣሉ።
ቤቶችም ላይ ይወጣሉ፤ እንደ ሌባ በመስኮት ይገባሉ።
10 ምድሪቱ በፊታቸው ትንቀጠቀጣለች፤ ሰማያትም ይናወጣሉ።
ፀሐይና ጨረቃ ጨልመዋል፤+
ከዋክብትም ብርሃናቸውን መስጠት አቁመዋል።
11 ይሖዋ በሠራዊቱ+ ፊት ድምፁን በኃይል ያሰማል፤ ሠራዊቱ ስፍር ቁጥር የለውም።+
ቃሉን የሚፈጽመው ኃያል ነውና፤
የይሖዋ ቀን ታላቅና እጅግ የሚያስፈራ ነው።+
ማንስ ሊቋቋመው ይችላል?”+
14 ደግሞም ተመልሶ ጉዳዩን እንደገና በማጤን፣*+
ለአምላካችሁ ለይሖዋ የእህል መባና የመጠጥ መባ ማቅረብ ትችሉ ዘንድ
በረከት ያስቀርላችሁ እንደሆነ ማን ያውቃል?
15 በጽዮን ቀንደ መለከት ንፉ!
16 ሕዝቡን ሰብስቡ፤ ጉባኤውን ቀድሱ።+
ሽማግሌዎቹን ሰብስቡ፤ ልጆቹንና ጡት የሚጠቡትን ሕፃናት ሰብስቡ።+
ሙሽራው ከውስጠኛው ክፍል፣ ሙሽሪትም ከጫጉላ ቤት ይውጡ።
17 የይሖዋ አገልጋዮች የሆኑት ካህናቱ
በበረንዳውና በመሠዊያው መካከል+ ሆነው ያልቅሱ፤ እንዲህም ይበሉ፦
‘ይሖዋ ሆይ፣ ለሕዝብህ እዘን፤
ርስትህ መሳለቂያ እንዲሆን አታድርግ፤
ብሔራትም አይግዟቸው።
ሕዝቦች “አምላካቸው የት አለ?” ለምን ይበሉ?’+
19 ይሖዋ ለሕዝቡ መልስ ይሰጣል፦
21 ምድር ሆይ፣ አትፍሪ።
ደስ ይበልሽ፤ ሐሴትም አድርጊ፤ ይሖዋ ታላላቅ ነገሮች ያደርጋልና።
23 እናንተ የጽዮን ልጆች ሆይ፣ በአምላካችሁ በይሖዋ ተደሰቱ፤ ሐሴትም አድርጉ፤+
እሱ የፊተኛውን ዝናብ በተገቢው መጠን ይሰጣችኋልና፤
በእናንተም ላይ ዝናቡን ያዘንባል፤
እንደቀድሞውም የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ ይሰጣችኋል።+
25 ደግሞም በመካከላችሁ የሰደድኩት ታላቁ ሠራዊቴ
ይኸውም የአንበጣ መንጋው፣ ኩብኩባው፣ የማይጠግበው አንበጣና አውዳሚው አንበጣ
ሰብላችሁን ለበሉባቸው ዓመታት ማካካሻ እሰጣችኋለሁ።+
ሕዝቤ ከእንግዲህ ወዲህ ፈጽሞ አያፍርም።
28 ከዚያ በኋላ በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ መንፈሴን አፈሳለሁ፤+
ወንዶች ልጆቻችሁና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ፤
ሽማግሌዎቻችሁ ሕልም ያልማሉ፤
ወጣቶቻችሁም ራእዮችን ያያሉ።+
29 በዚያ ቀን በወንዶች ባሪያዎቼና በሴቶች ባሪያዎቼ ላይ ሳይቀር
መንፈሴን አፈሳለሁ።