2 ብሔራት የታወኩት ለምንድን ነው?
ሕዝቦችስ ከንቱ ነገር የሚያጉተመትሙት ለምንድን ነው?+
2 የምድር ነገሥታት ተሰለፉ፤
ከፍተኛ ባለሥልጣናትም በአንድነት ተሰብስበው+
በይሖዋና እሱ በቀባው ላይ+ ተነሱ።
3 “ሰንሰለታቸውን እንበጥስ፤
ገመዳቸውንም እናስወግድ!” ይላሉ።
4 በሰማያት በዙፋን ላይ የተቀመጠው ይስቃል፤
ይሖዋ ይሳለቅባቸዋል።
5 በዚያን ጊዜ በቁጣ ይናገራቸዋል፤
በሚነድ ቁጣውም ያሸብራቸዋል፤
6 እንዲህም ይላቸዋል፦ “እኔ ራሴ በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን+ ላይ
ንጉሤን ሾምኩ።”+
7 የይሖዋን ድንጋጌ ልናገር፤
እንዲህ ብሎኛል፦ “አንተ ልጄ ነህ፤+
እኔ ዛሬ ወለድኩህ።+
8 ጠይቀኝ፤ ብሔራትን ርስትህ፣
የምድርንም ዳርቻዎች ግዛትህ አድርጌ እሰጥሃለሁ።+
9 በብረት በትረ መንግሥት ትሰብራቸዋለህ፤+
እንደ ሸክላ ዕቃም ታደቃቸዋለህ።”+
10 እንግዲህ እናንተ ነገሥታት አስተውሉ፤
እናንተ የምድር ፈራጆች እርማት ተቀበሉ።
11 ይሖዋን በፍርሃት አገልግሉ፤
ለእሱ በመንቀጥቀጥም ሐሴት አድርጉ።
12 ልጁን አክብሩ፤+ አለዚያ አምላክ ይቆጣል፤
ከመንገዱም ትጠፋላችሁ፤+
ቁጣው ፈጥኖ ይነድዳልና።
እሱን መጠጊያ የሚያደርጉ ሁሉ ደስተኞች ናቸው።