መዝሙር
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ “በአበቦች” የሚዘመር። ማስታወሻ። የአሳፍ+ መዝሙር። ማህሌት።
80 ዮሴፍን እንደ መንጋ የምትመራ
የእስራኤል እረኛ ሆይ፣+ አዳምጥ።
4 የሠራዊት አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ ሕዝቦችህ የሚያቀርቡትን ጸሎት የምትጠላው* እስከ መቼ ነው?+
5 እንባን እንደ ምግብ ትመግባቸዋለህ፤
ደግሞም እንባ ትግታቸዋለህ።
6 ለጎረቤቶቻችን የጠብ ምክንያት አደረግከን፤
ጠላቶቻችን እንዳሻቸው ያላግጡብናል።+
7 የሠራዊት አምላክ ሆይ፣ ወደ ቀድሞው ሁኔታችን መልሰን፤
እንድንም ዘንድ ፊትህን በእኛ ላይ አብራ።+
8 የወይን ተክል+ ከግብፅ እንድትወጣ አደረግክ።
ብሔራትን አባረህ እሷን ተከልክ።+
9 መሬቱን መነጠርክላት፤
እሷም ሥር ሰዳ በምድሪቱ ላይ ተንሰራፋች።+
10 ተራሮች በጥላዋ፣
የአምላክ አርዘ ሊባኖሶችም በቅርንጫፎቿ ተሸፈኑ።
13 ከጫካ የወጡ የዱር አሳማዎች ያወድሟታል፤
በሜዳ ያሉ የዱር አራዊትም ይበሏታል።+
14 የሠራዊት አምላክ ሆይ፣ እባክህ ተመለስ።
ከሰማይ ወደ ታች እይ፤ ተመልከትም!
16 እሷ ተቆርጣ በእሳት ተቃጥላለች።+
ሕዝቡ ከተግሣጽህ* የተነሳ ይጠፋል።
17 እጅህ በቀኝህ ላለው ሰው፣
ለራስህም ስትል ብርቱ ላደረግከው የሰው ልጅ ድጋፍ ትስጥ።+
18 እኛም ከአንተ አንርቅም።
ስምህን መጥራት እንድንችል በሕይወት አኑረን።
19 የሠራዊት አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ ወደ ቀድሞው ሁኔታችን መልሰን፤
እንድንም ዘንድ ፊትህን በእኛ ላይ አብራ።+