ሚክያስ
1 በይሁዳ ነገሥታት+ በኢዮዓታም፣+ በአካዝና+ በሕዝቅያስ+ ዘመን ወደ ሞረሸታዊው ወደ ሚክያስ*+ የመጣው እንዲሁም ሚክያስ ስለ ሰማርያና ስለ ኢየሩሳሌም በራእይ ያየው የይሖዋ ቃል ይህ ነው።”+
2 “እናንተ ሕዝቦች ሁላችሁም ስሙ!
ምድርና በውስጧ ያሉ ሁሉ፣ በትኩረት ያዳምጡ፤
ይሖዋ ቅዱስ በሆነው ቤተ መቅደሱ ነው።
ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ በእናንተ ላይ ይመሥክርባችሁ።+
3 እነሆ፣ ይሖዋ ከስፍራው ይወጣል፤
ወደ ታች ወርዶ የምድርን ከፍ ያሉ ቦታዎች ይረግጣል።
ለያዕቆብ ዓመፅ ተጠያቂው ማን ነው?
ሰማርያ አይደለችም?+
በይሁዳ ለሚገኙት ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎችስ ተጠያቂው ማን ነው?+
ኢየሩሳሌም አይደለችም?
ጣዖቶቿን ሁሉ እደመስሳለሁ።
እነዚህን ሁሉ ነገሮች የሰበሰበችው ለዝሙት አዳሪነቷ በተከፈላት ደሞዝ ነው፤
አሁን ደግሞ እነዚህ ነገሮች በሌላ ቦታ ላሉ ዝሙት አዳሪዎች ክፍያ እንዲሆኑ ይወሰዳሉ።”
እንደ ቀበሮዎች አላዝናለሁ፤
እንደ ሰጎኖችም አለቅሳለሁ።
መቅሰፍቱ እስከ ሕዝቤ በር፣ እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ ተዛምቷል።+
10 “በጌት አታውሩት፤
ከቶም አታልቅሱ።
በቤትአፍራ* በአፈር ላይ ተንከባለሉ።
11 የሻፊር ነዋሪዎች ሆይ፣ እርቃናችሁን ሆናችሁ በኀፍረት ተሻገሩ።
የጻናን ነዋሪዎች አልወጡም።
በቤትዔጼል ዋይታ ይኖራል፤ ለእናንተ ድጋፍ መስጠቱንም ያቆማል።
12 የማሮት ነዋሪዎች መልካም ነገርን ተጠባበቁ፤
ይሁንና ከይሖዋ ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም በር የወረደው ክፉ ነገር ነው።
13 የለኪሶ+ ነዋሪዎች ሆይ፣ ፈረሶቹን ከሠረገላው ጋር እሰሩ።
ለጽዮን ሴት ልጅ የኃጢአት መጀመሪያ ነበራችሁ፤
በእናንተ ውስጥ የእስራኤል ዓመፅ ተገኝቷልና።+
14 ስለዚህ ለሞረሸትጋት የመሰነባበቻ ስጦታ ትሰጫለሽ።
የአክዚብ ቤቶች ለእስራኤል ነገሥታት ማታለያ ነበሩ።
15 የማሬሻህ+ ነዋሪዎች ሆይ፣ ድል አድራጊውን* ገና አመጣባችኋለሁ።+
የእስራኤል ክብር እስከ አዱላም+ ድረስ ይመጣል።
16 ለምትወዷቸው ልጆቻችሁ ፀጉራችሁን ተቆረጡ፤ ራሳችሁንም ተላጩ።
እንደ ንስር ተመለጡ፤
ልጆቻችሁ በግዞት ተወስደውባችኋልና።”+