ኢዮብ
15 ቴማናዊው ኤሊፋዝ+ እንዲህ ሲል መለሰ፦
2 “ጥበበኛ ሰው ከንቱ በሆነ ንግግር* ይመልሳል?
ወይስ በምሥራቅ ነፋስ ሆዱን ይሞላል?
3 በማይረባ ቃል መውቀስ ምንም ዋጋ የለውም፤
ደግሞም ወሬ ብቻውን ምንም ጥቅም የለውም።
4 አንተ ፈሪሃ አምላክን ታጣጥላለህና፤
ስለ አምላክ ማሰብም ዋጋ የለውም ትላለህ።
5 በደልህ በምትናገረው ነገር ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል፤*
ተንኮል ያዘለ ንግግር መናገርም ትመርጣለህ።
6 እኔ ሳልሆን የገዛ አፍህ ይፈርድብሃል፤
የገዛ ከንፈሮችህ ይመሠክሩብሃል።+
7 ለመሆኑ ከሰው ሁሉ በፊት የተወለድከው አንተ ነህ?
ወይስ የተወለድከው ከኮረብቶች በፊት ነው?
8 የአምላክን ሚስጥር ትሰማለህ?
ወይስ ጥበብ ያለህ አንተ ብቻ ነህ?
9 እኛ የማናውቀው አንተ ግን የምታውቀው ምን ነገር አለ?+
ደግሞስ እኛ የማናስተውለው አንተ ግን የምታስተውለው ምን ነገር አለ?
10 የሸበቱም ሆኑ በዕድሜ የገፉ፣
እንዲሁም ከአባትህ በዕድሜ እጅግ የሚበልጡ ከእኛ ጋር አሉ።+
11 የአምላክ ማጽናኛ፣
ወይም በለሰለሰ አንደበት የተነገረህ ቃል አነሰህ?
12 ልብህ ለምን ይታበያል?
ዓይኖችህስ ለምን በቁጣ ይጉረጠረጣሉ?
13 በአምላክ ላይ ተቆጥተሃልና፤
እንዲህ ያሉ ቃላትም ከገዛ አፍህ ወጥተዋል።
17 አዳምጠኝ! እኔ አሳውቅሃለሁ።
19 ምድሪቱ የተሰጠችው ለእነሱ ብቻ ነበር፤
በመካከላቸውም ባዕድ ሰው አላለፈም።
20 ክፉ ሰው ዕድሜውን ሁሉ፣
ለጨቋኙ በተመደቡት ዓመታት በሙሉ ይሠቃያል።
21 አስፈሪ ድምፆችን ይሰማል፤+
በሰላም ጊዜ ወራሪዎች ጥቃት ይሰነዝሩበታል።
22 ከጨለማ እንደሚያመልጥ አያምንም፤+
ሰይፍም ይጠብቀዋል።
23 ‘ወዴት ነው?’ እያለ ምግብ* ፍለጋ ይቅበዘበዛል፤
የጨለማ ቀን እንደደረሰ በሚገባ ያውቃል።
24 ጭንቀትና ሥቃይ ያሸብሩታል፤
ጥቃት ለመሰንዘር እንደተዘጋጀ ንጉሥ ያይሉበታል።
25 በአምላክ ላይ እጁን ያነሳልና፤
ሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ ለመገዳደርም* ይሞክራል፤
26 ወፍራምና ጠንካራ ጋሻ* አንግቦ፣
በእልኸኝነት እየገሰገሰ ይመጣበታል፤
27 ፊቱ በስብ ተሸፍኗል፤
ወገቡም በስብ ተወጥሯል፤
28 በሚፈራርሱ ከተሞች፣
ደግሞም ማንም በማይኖርባቸውና
የድንጋይ ክምር በሚሆኑ ቤቶች ውስጥ ይኖራል።
29 ባለጸጋ አይሆንም፤ ሀብቱም አይከማችም፤
ንብረቱም በምድሪቱ ላይ አይበረክትም።
31 መንገድ መሳትና ከንቱ በሆነ ነገር መታመን የለበትም፤
በአጸፋው የሚያገኘው ነገር ዋጋ አይኖረውምና፤
32 ቀኑ ከመድረሱ በፊት ይፈጸማል፤
ቅርንጫፎቹም አይለመልሙም።+
33 ያልበሰሉ ፍሬዎቹን እንደሚጥል የወይን ተክል፣
አበቦቹን እንደሚያረግፍ የወይራ ዛፍም ይሆናል።
35 ችግር ይፀንሳሉ፤ ክፉ ነገርም ይወልዳሉ፤
ማህፀናቸውም ተንኮል ያፈራል።”