ኢዮብ
20 ናአማታዊው ሶፋር+ እንዲህ ሲል መለሰ፦
2 “ስሜቴ ስለታወከ፣
የሚረብሸኝ ሐሳብ መልስ እንድሰጥ ይገፋፋኛል።
3 እኔን የሚዘልፍ ወቀሳ ሰምቻለሁ፤
ያለኝ ማስተዋል* መልስ እንድሰጥ ይገፋፋኛል።
6 ታላቅነቱ ወደ ሰማይ ከፍ ቢል፣
ራሱም እስከ ደመናት ቢደርስ፣
7 እንደ ራሱ እዳሪ ለዘላለም ይጠፋል፤
ያዩት የነበሩ ሰዎችም ‘የት ገባ?’ ይላሉ።
8 እንደ ሕልም በሮ ይጠፋል፤ እነሱም አያገኙትም፤
እንደ ሌሊት ራእይ ይሰደዳል።
9 ቀድሞ ያየው ዓይን ዳግመኛ አያየውም፤
የነበረበት ስፍራም ከእንግዲህ አይመለከተውም።+
10 የገዛ ልጆቹ የድሆችን ሞገስ ለማግኘት ይሻሉ፤
የገዛ እጆቹም ሀብቱን መልሰው ይሰጣሉ።+
11 አጥንቶቹ በወጣትነት ጉልበት የተሞሉ ነበሩ፤
ሆኖም ጉልበቱ ከእሱ ጋር አፈር ውስጥ ይተኛል።
12 መጥፎ የሆነ ነገር በአፉ ውስጥ ቢጣፍጥ፣
ከምላሱም በታች ቢደብቀው፣
13 እንዳያልቅበት ሳስቶ ቢያላምጠው፣
በአፉም ውስጥ ቢያቆየው፣
14 ምግቡ በውስጡ ይጎመዝዛል፤
15 የዋጠውን ሀብት መልሶ ይተፋዋል፤
አምላክ ከሆዱ ውስጥ ያወጣዋል።
16 የጉበናዎችን መርዝ ይጠባል፤
የእፉኝት ጥርስ* ይገድለዋል።
17 የውኃ ፈሳሾችን፣
የማርና የቅቤ ጅረቶችን ፈጽሞ አያይም።
18 ንብረቱን ሳይጠቀምበት ይመልሳል፤
ነግዶ ባገኘው ሀብት አይደሰትም።+
19 ድሆችን አድቅቋልና፤ ደግሞም ትቷቸዋል፤
ያልገነባውን ቤት ቀምቷል።
20 ሆኖም በውስጡ ሰላም አይኖረውም፤
ያካበተው ሀብት አያድነውም።
21 ሊበላው የሚችል የተረፈ ነገር አይኖርም፤
ከዚህም የተነሳ ብልጽግናው ዘላቂ አይሆንም።
22 ሀብቱ ሲትረፈረፍ በጭንቀት ይዋጣል፤
የመከራ ዓይነት ይፈራረቅበታል።
24 ከብረት የጦር መሣሪያ ሲሸሽ፣
ከመዳብ የተሠራ ቀስት ይወጋዋል።
26 ውድ ሀብቱ ለድቅድቅ ጨለማ ይዳረጋል፤
ማንም ያላርገበገበው እሳት እሱን ይበላዋል፤
በድንኳኑ ውስጥ የቀረ ማንኛውም ሰው ጥፋት ይደርስበታል።
27 ሰማይ በደሉን ይገልጥበታል፤
ምድር በእሱ ላይ ትነሳለች።
28 ጎርፍ ቤቱን ጠርጎ ይወስደዋል፤
በአምላክ የቁጣ ቀን* የውኃ መጥለቅለቅ ይከሰታል።
29 ክፉ ሰው ከአምላክ የሚቀበለው ድርሻ፣
አምላክም የወሰነለት ርስት ይህ ነው።”