ኢዮብ
19 ኢዮብ እንዲህ ሲል መለሰ፦
4 ስህተት ብፈጽምም እንኳ፣
የሠራሁት ስህተት ከእኔ ጋር ይኖራል።
5 በእኔ ላይ የደረሰው ነቀፋ ተገቢ እንደሆነ አድርጋችሁ በመከራከር፣
በእኔ ላይ ራሳችሁን ከፍ ከፍ ብታደርጉ፣
6 ያሳተኝ አምላክ እንደሆነ እወቁ፤
በማጥመጃ መረቡም ይዞኛል።
8 መንገዴን በድንጋይ ግንብ ዘጋ፤ እኔም ማለፍ አልቻልኩም፤
ጎዳናዬንም በጨለማ ጋረደ።+
9 ክብሬን ገፎኛል፤
አክሊሉንም ከራሴ ላይ አንስቷል።
10 እስክጠፋ ድረስ በሁሉም አቅጣጫ አፈራረሰኝ፤
ተስፋዬን እንደ ዛፍ ነቀለው።
11 ቁጣው በእኔ ላይ ነደደ፤
እንደ ጠላቱም ቆጠረኝ።+
12 ሠራዊቱ በአንድነት መጥተው ከበቡኝ፤
በድንኳኔም ዙሪያ ሰፈሩ።
13 የገዛ ወንድሞቼን ከእኔ አራቀ፤
የሚያውቁኝም ሰዎች ጥለውኝ ሄዱ።+
15 በቤቴ ያሉ እንግዶችና+ ሴቶች ባሪያዎቼ እንደ መጤ ቆጠሩኝ፤
እንደ ባዕድ አገር ሰው ተመለከቱኝ።
16 አገልጋዬን ጠራሁት፤ እሱ ግን አልመለሰልኝም፤
እንዲራራልኝ በአንደበቴ ለመንኩት።
18 ትናንሽ ልጆች እንኳ ናቁኝ፤
ስነሳ በእኔ ላይ ያላግጣሉ።
21 ወዳጆቼ ሆይ፣ ማሩኝ፤ እባካችሁ ማሩኝ፤
የአምላክ እጅ መታኛለችና።+
23 ምነው ቃሌ በተጻፈ!
ምነው በመጽሐፍ ላይ በሰፈረ!
24 ምነው በብረት ብዕርና በእርሳስ፣
በዓለቱ ላይ ለዘላለም በተቀረጸ!
ይሁንና በውስጤ እንደዛልኩ ይሰማኛል!*
28 የችግሩ መንስኤ እኔ ጋ እያለ፣
‘የምናሳድደው እንዴት ነው?’ ትላላችሁና።+