መዝሙር
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ “በአበቦች” የሚዘመር። የቆሬ ልጆች።+ ማስኪል።* የፍቅር መዝሙር።
45 መልካም የሆነ ነገር ልቤን አነሳስቶታል።
አንደበቴ የተዋጣለት ገልባጭ *+ እንደሚጠቀምበት ብዕር+ ይሁን።
2 አንተ ከሰው ልጆች ሁሉ ይልቅ ውብ ነህ።
ከከንፈሮችህ ጸጋ የተላበሱ ቃላት ይፈስሳሉ።+
አምላክ ለዘላለም የባረከህ ለዚህ ነው።+
ስለዚህ አምላክ ይኸውም አምላክህ ከባልንጀሮችህ ይበልጥ በደስታ ዘይት+ ቀባህ።+
8 ልብሶችህ ሁሉ የከርቤ፣ የእሬትና* የብርጉድ መዓዛ አላቸው፤
በዝሆን ጥርስ ካጌጠው ታላቅ ቤተ መንግሥት የሚወጣው የባለ አውታር መሣሪያዎች* ድምፅ ያስደስትሃል።
9 ከተከበሩት እመቤቶችህ መካከል የነገሥታት ልጆች ይገኛሉ።
እቴጌይቱ* በኦፊር ወርቅ+ አጊጣ በቀኝህ ቆማለች።
10 ልጄ ሆይ፣ አዳምጪ፣ ልብ በዪ፣ ጆሮሽንም አዘንብዪ፤
ሕዝብሽንና የአባትሽን ቤት እርሺ።
12 የጢሮስ ሴት ልጅ ስጦታ ይዛ ትመጣለች፤
እጅግ ባለጸጋ የሆኑትም በአንቺ ዘንድ ሞገስ ለማግኘት ጥረት ያደርጋሉ።
14 ያጌጠ ልብሷን* ለብሳ ወደ ንጉሡ ትወሰዳለች።
ወዳጆቿ የሆኑ ደናግል አጃቢዎቿን ወደ ፊትህ ያቀርቧቸዋል።
15 በደስታና በሐሴት ይመሯቸዋል፤
ወደ ንጉሡ ቤተ መንግሥት ይገባሉ።
16 በአባቶችህ ፋንታ ወንዶች ልጆችህ ይተካሉ።
በምድር ሁሉ ላይ መኳንንት አድርገህ ትሾማቸዋለህ።+
17 ለሚመጡት ትውልዶች ሁሉ ስምህን አሳውቃለሁ።+
በመሆኑም ሕዝቦች ለዘላለም ያወድሱሃል።