ኢሳይያስ
ማጥፋትህን እንዳጠናቀክ አንተም ትጠፋለህ።+
ክህደት መፈጸምህን እንዳበቃህ ትካዳለህ።
በአንተ ተስፋ አድርገናል።
3 የድምፅህን ነጎድጓድ ሲሰሙ ሕዝቦች ይሸሻሉ።
በምትነሳበት ጊዜ ብሔራት ይበታተናሉ።+
4 የማይጠግቡ አንበጦች በሚሰበሰቡበት ጊዜ እንደሚሆነው ከእናንተም የሚወሰደው ምርኮ እንዲሁ ይሰበሰባል፤
ሰዎች እንደ አንበጣ መንጋ ምርኮውን ይቀራመቱታል።
5 ይሖዋ ከፍ ከፍ ይላል፤
በከፍታ ቦታ ይኖራልና።
ጽዮንን በፍትሕና በጽድቅ ይሞላል።
7 እነሆ፣ ጀግኖቻቸው በጎዳና ላይ ይጮኻሉ፤
የሰላም መልእክተኞቹም አምርረው ያለቅሳሉ።
8 አውራ ጎዳናዎቹ ጭር ብለዋል፤
በመንገድ ላይ የሚጓዝ ሰው የለም።
ሊባኖስ ተዋረደ፤+ እንዲሁም በሰበሰ።
ሳሮን እንደ በረሃ ሆነች፤
ባሳንና ቀርሜሎስም ቅጠላቸውን አረገፉ።+
11 ደረቅ ሣር ትፀንሳላችሁ፤ ገለባንም ትወልዳላችሁ።
የገዛ መንፈሳችሁም እንደ እሳት ይበላችኋል።+
12 ሕዝቦችም እንደተቃጠለ ኖራ ይሆናሉ።
እንደተቆረጠ እሾህ በእሳት ይጋያሉ።+
13 እናንተ በሩቅ ያላችሁ፣ የማደርገውን ስሙ!
እናንተም በቅርብ ያላችሁ፣ ለኃይሌ እውቅና ስጡ!
‘ከእኛ መካከል የሚባላ እሳት ባለበት ቦታ መኖር የሚችል ማን ነው?+
ከእኛስ መካከል ከማይጠፋ የእሳት ነበልባል ጋር መኖር የሚችል ማን ነው?’
ቅን+ የሆነውን ነገር የሚናገር፣
በማታለልና በማጭበርበር የሚገኝን ጥቅም የሚጠላ፣
ጉቦ ከመቀበል እጁን የሚሰበስብ፣+
ደም ለማፍሰስ የሚጠነሰስን ሴራ ላለመስማት ጆሮውን የሚደፍን
እንዲሁም ክፉ የሆነውን ላለማየት ዓይኑን የሚጨፍን ሰው፣
16 በከፍታ ቦታዎች ይኖራል፤
ዓለታማ ምሽጎች አስተማማኝ መጠጊያው ይሆናሉ፤
ምግቡም ይቀርብለታል፤
የውኃ አቅርቦትም ፈጽሞ አይቋረጥበትም።”+
17 ዓይኖችህ ንጉሡን ግርማ ተላብሶ ያዩታል፤
በሩቅ ያለችውን ምድር ያያሉ።
18 ሽብር የነበረበትን ወቅት በልብህ ታስታውሳለህ፦*
“ጸሐፊው የት አለ?
ግብር የመዘነው የት አለ?+
ማማዎቹንስ የቆጠረው የት አለ?”
20 በዓሎቻችንን+ የምናከብርባትን ከተማ ጽዮንን ተመልከት!
ጸጥታ የሰፈነባት መኖሪያ፣
የማትነቃነቅ ድንኳን+ የሆነችውን ኢየሩሳሌምን ዓይኖችህ ያያሉ።
የድንኳን ካስማዎቿ ፈጽሞ አይነቀሉም፤
ከገመዶቿም አንዱ እንኳ አይበጠስም።
21 ይልቁንም ግርማ ሞገስ የተላበሰው ይሖዋ
በዚያ ስፍራ እንደ ወንዞችና እንደ ሰፋፊ ቦዮች ሆኖ ይጠብቀናል፤
በእነሱም ላይ ጠላት የሚያሰልፋቸው ባለ መቅዘፊያ ጀልባዎችም ሆኑ
ትላልቅ መርከቦች አያልፉም።
23 ገመዶችህ ይላላሉ፤
የመርከቡን ምሰሶ አጽንተው ማቆምም ሆነ ሸራውን ወጥረው መያዝ አይችሉም።
በዚያን ጊዜ ብዛት ያለው ምርኮ ይከፋፈላል፤
አንካሶችም እንኳ ብዙ የሚበዘበዝ ነገር ያገኛሉ።+
24 በዚያም የሚቀመጥ* ማንኛውም ሰው “ታምሜአለሁ” አይልም።+
በምድሪቱ ላይ የሚቀመጡ በደላቸው ይቅር ይባልላቸዋል።+