ኢዮብ
27 ኢዮብ ንግግሩን* በመቀጠል እንዲህ አለ፦
2 “ፍትሕ በነፈገኝ ሕያው በሆነው አምላክ፣+
እንድመረር ባደረገኝ*+ ሁሉን ቻይ በሆነው አምላክ እምላለሁ፤
3 እስትንፋሴ በውስጤ፣
ከአምላክ ያገኘሁትም መንፈስ በአፍንጫዬ ውስጥ እስካለ ድረስ፣+
4 ከንፈሮቼ ክፋት አይናገሩም፤
ምላሴም ፈጽሞ የማታለያ ቃል አይወጣውም!
5 በእኔ በኩል እናንተን ጻድቅ አድርጎ መቁጠር የማይታሰብ ነገር ነው!
7 ጠላቴ እንደ ክፉ ሰው ይሁን፤
እኔን የሚያጠቁኝ ሰዎች እንደ ዓመፀኛ ይሁኑ።
9 መከራ ሲደርስበት
አምላክ ጩኸቱን ይሰማዋል?+
10 ወይስ ሁሉን ቻይ በሆነው አምላክ ደስ ይሰኛል?
ሁልጊዜስ ወደ አምላክ ይጣራል?
11 እኔ ስለ አምላክ ኃይል* አስተምራችኋለሁ፤
ሁሉን ቻይ ስለሆነው አምላክ ምንም የምደብቀው ነገር የለም።
12 ሁላችሁም ራእይ ካያችሁ፣
ንግግራችሁ ጨርሶ ባዶ የሆነው ለምንድን ነው?
13 ክፉ ሰው ከአምላክ የሚያገኘው ድርሻ፣+
ጨቋኞችም ሁሉን ቻይ ከሆነው አምላክ የሚወርሱት ውርሻ ይህ ነው።
14 ልጆቹ ቢበዙ በሰይፍ ይወድቃሉ፤+
ዘሮቹም በቂ ምግብ አያገኙም።
15 ከእሱ በኋላ የተረፉት ወገኖቹ በመቅሰፍት ይቀበራሉ፤
መበለቶቻቸውም አያለቅሱላቸውም።
18 የሚሠራው ቤት ብል እንደሠራው ሽፋን፣
ጠባቂም እንደቀለሰው መጠለያ+ በቀላሉ የሚፈርስ ነው።
19 ባለጸጋ ሆኖ ይተኛል፤ ሆኖም ምንም የሚሰበስበው ነገር የለም፤
ዓይኑን ሲገልጥ በዚያ ምንም ነገር አይኖርም።
20 ሽብር እንደ ጎርፍ ድንገት ያጥለቀልቀዋል፤
አውሎ ነፋስ በሌሊት ይዞት ይሄዳል።+
21 የምሥራቅ ነፋስ ይወስደዋል፤ እሱም አይገኝም፤
ከቦታው ጠርጎ ይወስደዋል።+