ወደ ላይ የመውጣት መዝሙር።
130 ይሖዋ ሆይ፣ ከጥልቅ ውስጥ አንተን እጣራለሁ።+
2 ይሖዋ ሆይ፣ ድምፄን ስማ።
ጆሮዎችህ እርዳታ ለማግኘት የማቀርበውን ልመና በትኩረት ያዳምጡ።
3 ያህ ሆይ፣ አንተ ስህተትን የምትከታተል ቢሆን ኖሮ፣
ይሖዋ ሆይ፣ ማን ሊቆም ይችል ነበር?+
4 በአንተ ዘንድ በእርግጥ ይቅርታ አለና፤+
ይህም ሰዎች አንተን እንዲፈሩ ያደርጋል።+
5 ይሖዋን ተስፋ አደርጋለሁ፤ ሁለንተናዬ በእሱ ተስፋ ያደርጋል፤
ቃሉን በትዕግሥት እጠብቃለሁ።
6 ንጋትን ከሚጠባበቁ፣
አዎ፣ ንጋትን ከሚጠባበቁ ጠባቂዎች ይበልጥ
ይሖዋን በጉጉት እጠባበቃለሁ።+
7 እስራኤል ይሖዋን በትዕግሥት ይጠባበቅ፤
ይሖዋ በፍቅሩ ታማኝ ነውና፤+
ሕዝቡንም ለመዋጀት ታላቅ ኃይል አለው።
8 እስራኤልን ከበደላቸው ሁሉ ይዋጃል።