ኤርምያስ
3 ይሖዋ ለይሁዳ ሰዎችና ለኢየሩሳሌም እንዲህ ይላልና፦
“ያልለማውን መሬት እረሱ፤
በእሾህ መካከልም አትዝሩ።+
4 እናንተ የይሁዳ ሰዎችና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች፣
ለይሖዋ ተገረዙ፤
የልባችሁንም ሸለፈት አስወግዱ፤+
አለዚያ በክፉ ሥራችሁ የተነሳ
ቁጣዬ እንደ እሳት ይነድዳል፤
ማንም ሊያጠፋው አይችልም።”+
5 ይህን በይሁዳ ተናገሩ፤ በኢየሩሳሌምም አውጁ።
ጩኹ፤ በምድሪቱም ሁሉ ላይ ቀንደ መለከት ንፉ።+
ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ እንዲህ በሉ፦ “አንድ ላይ ተሰብሰቡ፤
ወደተመሸጉት ከተሞችም እንሽሽ።+
6 ወደ ጽዮን የሚጠቁም ምልክት* አቁሙ።
መጠለያ ፈልጉ፤ ዝም ብላችሁም አትቁሙ።”
ከሰሜን ጥፋት ብሎም ታላቅ መዓት አመጣለሁና።+
ምድርሽን አስፈሪ ቦታ ሊያደርግ ከቦታው ወጥቷል።
ከተሞችሽ አንድም ሰው የማይኖርባቸው የፍርስራሽ ክምር ይሆናሉ።+
10 ከዚያም እንዲህ አልኩ፦ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ወዮ! ሰይፍ አንገታችን ላይ ተጋድሞ* እያለ ‘ሰላም ታገኛላችሁ’+ ብለህ ይህን ሕዝብና ኢየሩሳሌምን ፈጽሞ አታለሃል።”+
11 በዚያን ጊዜ ለዚህ ሕዝብና ለኢየሩሳሌም እንዲህ ይባላል፦
12 በእኔ ትእዛዝ ኃይለኛው ነፋስ ከእነዚህ ስፍራዎች ይመጣል።
አሁን በእነሱ ላይ ፍርድ አስተላልፋለሁ።
13 እነሆ፣ እሱ ዝናብ እንዳዘሉ ደመናት ይመጣል፤
ሠረገሎቹም እንደ አውሎ ነፋስ ናቸው።+
ፈረሶቹ ከንስር ይበልጥ ፈጣኖች ናቸው።+
ጠፍተናልና ወዮልን!
14 ኢየሩሳሌም ሆይ፣ እንድትድኚ ልብሽን ከክፋት ሁሉ አጥሪ።+
እስከ መቼ በውስጥሽ ክፉ ሐሳብ ይዘሽ ትኖሪያለሽ?
15 አንድ ድምፅ ከዳን ዜናውን ይናገራልና፤+
ከኤፍሬም ተራሮችም ጥፋትን ያውጃል።
16 ይህን አሳውቁ፤ አዎ ለብሔራት ተናገሩ፤
በኢየሩሳሌም ላይ አውጁ።”
“ጠባቂዎች* ከሩቅ አገር እየመጡ ነው፤
በይሁዳ ከተሞችም ላይ ይጮኻሉ።
18 “ለተከተልሽው መንገድና ለፈጸምሽው ተግባር ዋጋሽን ትቀበያለሽ።+
የሚደርስብሽ ጥፋት ምንኛ መራራ ነው፤
ወደ ልብሽ ዘልቆ ይገባልና!”
ልቤን ሥቃይ ቀስፎታል።
ልቤ በውስጤ በኃይል ይመታል።
20 በጥፋት ላይ ጥፋት መድረሱ ተወርቷል፤
ምድሪቱ በሙሉ ወድማለችና።
የገዛ ድንኳኖቼ በድንገት፣
የድንኳን ሸራዎቼም በቅጽበት ጠፍተዋል።+
22 “ሕዝቤ ሞኝ ነውና፤+
እነሱ ለእኔ ትኩረት አይሰጡም።
ማስተዋል የሌላቸው ቂል ልጆች ናቸው።
ክፉ ነገር ለማድረግ ብልሃተኞች* ናቸው፤
መልካም ነገር ማድረግ ግን አያውቁም።”
23 ምድሪቱን አየሁ፤ እነሆም፣ ባዶና ወና ነበረች።+
ወደ ሰማያት ተመለከትኩ፤ ብርሃናቸው ጠፍቶ ነበር።+
24 ተራሮቹን አየሁ፤ እነሆ፣ ይናወጡ ነበር፤
ኮረብቶቹም ይንቀጠቀጡ ነበር።+
26 እኔም አየሁ፤ እነሆ፣ የፍራፍሬ እርሻው ምድረ በዳ ሆኖ ነበር፤
ከተሞቹም ሁሉ ፈራርሰው ነበር።+
ይህም የሆነው በይሖዋ፣
በሚነደውም ቁጣው የተነሳ ነው።
ጥሻ ውስጥ ይገባሉ፤
ዓለቶቹም ላይ ይወጣሉ።+
ከተሞቹ ሁሉ ተትተዋል፤
የሚኖርባቸውም ሰው የለም።”
30 ለጥፋት ተዳርገሻል፤ ታዲያ ምን ታደርጊ ይሆን?
ደማቅ ቀይ ልብስ ትጎናጸፊ፣
በወርቅ ጌጣጌጦች ታጌጪና
ዓይኖችሽን ትኳዪ ነበር።
31 እንደታመመች ሴት ድምፅ፣
የመጀመሪያ ልጇንም ለመውለድ እንደምታምጥ ሴት ያለ የጭንቅ ድምፅ፣
ደግሞም ትንፋሽ አጥሯት ቁና ቁና የምትተነፍሰውን የጽዮን ሴት ልጅ ድምፅ ሰምቻለሁና።
እሷም እጆቿን ዘርግታ+
“ወዮልኝ! ከገዳዮች የተነሳ ዝያለሁና”* ትላለች።