የዳዊት መዝሙር።
27 ይሖዋ ብርሃኔና+ አዳኜ ነው።
ማንን እፈራለሁ?+
ይሖዋ የሕይወቴ ተገን ነው።+
ማን ያሸብረኛል?
2 ክፉዎች ሥጋዬን ለመብላት ባጠቁኝ ጊዜ፣+
ተሰናክለው የወደቁት ባላጋራዎቼና ጠላቶቼ ናቸው።
3 ሠራዊት በዙሪያዬ ቢሰፍርም፣
ልቤ በፍርሃት አይዋጥም።+
ጦርነት ቢከፈትብኝም እንኳ
በልበ ሙሉነት እመላለሳለሁ።
4 ይሖዋን አንድ ነገር ለመንኩት፤
ምኞቴም ይኸው ነው፦
በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በይሖዋ ቤት እኖር ዘንድ፣+
ይሖዋ ደስ የሚያሰኝ መሆኑን በትኩረት እመለከት ዘንድ፣
ቤተ መቅደሱንም በአድናቆት አይ ዘንድ ነው።+
5 በመዓት ቀን በመጠለያው ይሸሽገኛል፤+
ሚስጥራዊ ቦታ በሆነው ድንኳኑ ውስጥ ይሰውረኛል፤+
ከፍ ባለ ዓለት ላይ ያስቀምጠኛል።+
6 በመሆኑም ራሴ በዙሪያዬ ካሉ ጠላቶቼ በላይ ከፍ ብሏል፤
በድንኳኑ ውስጥ በእልልታ መሥዋዕት አቀርባለሁ፤
ለይሖዋ የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ።
7 ይሖዋ ሆይ፣ በምጮኽበት ጊዜ ስማኝ፤+
ሞገስ አሳየኝ፤ መልስም ስጠኝ።+
8 ልቤ በአንተ ቦታ ሆኖ ሲናገር
“ፊቴን ፈልጉ” ብሏል።
ይሖዋ ሆይ፣ ፊትህን እሻለሁ።+
9 ፊትህን ከእኔ አትሰውር።+
አገልጋይህን ተቆጥተህ ፊት አትንሳው።
አንተ ረዳቴ ነህ፤+
አዳኝ አምላኬ ሆይ፣ ከእኔ አትለይ፤ አትተወኝም።
10 የገዛ አባቴና እናቴ ቢተዉኝ እንኳ+
ይሖዋ ራሱ ይቀበለኛል።+
11 ይሖዋ ሆይ፣ መንገድህን አስተምረኝ፤+
ከጠላቶቼ ጥበቃ እንዳገኝ ቀና በሆነ መንገድ ምራኝ።
12 ለጠላቶቼ አሳልፈህ አትስጠኝ፤+
ሐሰተኛ ምሥክሮች በእኔ ላይ ተነስተዋልና፤+
ደግሞም እኔን ለማጥቃት ይዝቱብኛል።
13 በሕያዋን ምድር የይሖዋን ጥሩነት አያለሁ የሚል እምነት ባይኖረኝ ኖሮ
ምን ይውጠኝ ነበር!+
14 ይሖዋን ተስፋ አድርግ፤+
ደፋር ሁን፤ ልብህም ይጽና።+
አዎ፣ ይሖዋን ተስፋ አድርግ።