መዝሙር
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት ማህሌት።
31 ይሖዋ ሆይ፣ አንተን መጠጊያ አድርጌአለሁ።+
ፈጽሞ አልፈር።+
ከጽድቅህ የተነሳ ታደገኝ።+
2 ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል።*
ፈጥነህ ታደገኝ።+
እኔን ለማዳን በተራራ ላይ ያለ ምሽግ፣
የተመሸገ ስፍራም ሁንልኝ።+
የእውነት* አምላክ የሆንከው ይሖዋ ሆይ፣+ ዋጅተኸኛል።
6 የማይረቡና ከንቱ የሆኑ ጣዖቶችን የሚያመልኩ ሰዎችን እጠላለሁ፤
እኔ ግን በይሖዋ እታመናለሁ።
8 ለጠላት አሳልፈህ አልሰጠኸኝም፤
ይልቁንም ደህንነት በማገኝበት ስፍራ አቆምከኝ።*
9 ይሖዋ ሆይ፣ በጭንቀት ስለተዋጥኩ ሞገስ አሳየኝ።
መከራ ዓይኔንም ሆነ መላ ሰውነቴን አድክሞታል።*+
10 ሕይወቴ በሐዘን፣
ዕድሜዬም በመቃተት አልቋል።+
ከፈጸምኩት ኃጢአት የተነሳ ጉልበቴ ተሟጠጠ፤
አጥንቶቼ ደከሙ።+
11 ባላጋራዎቼ ሁሉ፣
በተለይ ደግሞ ጎረቤቶቼ ተሳለቁብኝ።+
የሚያውቁኝ ሰዎችም እጅግ ፈሩኝ፤
በአደባባይ ሲያዩኝ ከእኔ ይሸሻሉ።+
12 የሞትኩ ያህል ከልባቸው ወጣሁ፤* ደግሞም ተረሳሁ፤
እንደተሰበረ ማሰሮ ነኝ።
13 ብዙ መጥፎ ወሬ ሰምቻለሁ፤
ሽብር ከቦኛል።+
14 ይሖዋ ሆይ፣ እኔ ግን በአንተ እታመናለሁ።+
“አንተ አምላኬ ነህ” እላለሁ።+
15 የሕይወት ዘመኔ በእጅህ ነው።
ከጠላቶቼና ከሚያሳድዱኝ እጅ ታደገኝ።+
16 ፊትህ በአገልጋይህ ላይ እንዲበራ አድርግ።+
በታማኝ ፍቅርህ አድነኝ።
17 ይሖዋ ሆይ፣ አንተን በጠራሁ ጊዜ አልፈር።+
18 በትዕቢትና በንቀት በጻድቁ ላይ በእብሪት የሚናገሩ
ሐሰተኛ ከንፈሮች ዱዳ ይሁኑ።+
22 እኔ በድንጋጤ ተውጬ
“ከፊትህ መጥፋቴ ነው” አልኩ።+
አንተ ግን እርዳታ ለማግኘት በጮኽኩ ጊዜ ልመናዬን ሰማህ።+
23 እናንተ ለእሱ ታማኝ የሆናችሁ ሁሉ፣ ይሖዋን ውደዱ!+