መዝሙር
95 ኑ፣ ለይሖዋ እልል እንበል!
አዳኛችን ለሆነው ዓለት በድል አድራጊነት ስሜት እልል እንበል።+
2 ምስጋና ይዘን በፊቱ እንቅረብ፤+
በድል አድራጊነት ስሜት ለእሱ እንዘምር፤ ደግሞም እልል እንበል።
3 ይሖዋ ታላቅ አምላክ ነውና፤
በሌሎች አማልክት ሁሉ ላይ ታላቅ ንጉሥ ነው።+
4 ጥልቅ የሆኑት የምድር ክፍሎች በእጁ ናቸው፤
የተራሮችም ጫፍ የእሱ ነው።+
6 ኑ፣ እናምልክ፤ እንስገድም፤
ሠሪያችን በሆነው በይሖዋ ፊት እንንበርከክ።+
10 ያን ትውልድ ለ40 ዓመት ተጸየፍኩት፤
እኔም “ይህ ሕዝብ ሁልጊዜ ልቡ ይስታል፤
መንገዴን ሊያውቅ አልቻለም” አልኩ።
11 በመሆኑም “ወደ እረፍቴ አይገቡም” ብዬ
በቁጣዬ ማልኩ።+