13 ጥበበኛ ልጅ የአባቱን ተግሣጽ ይቀበላል፤+
ፌዘኛ ግን ተግሣጽን አይሰማም።+
2 ሰው ከአፉ ፍሬ መልካም ነገር ይበላል፤+
ከዳተኞች ግን ዓመፅን ይመኛሉ።
3 አፉን የሚጠብቅ ሕይወቱን ይጠብቃል።+
አፉን የሚከፍት ግን ይጠፋል።+
4 ሰነፍ ሰው ይመኛል፤ ነገር ግን ምንም አያገኝም፤+
ትጉ ሰው ግን በሚገባ ይጠግባል።+
5 ጻድቅ ውሸትን ይጠላል፤+
የክፉ ሰው ድርጊት ግን ኀፍረትና ውርደት ያመጣበታል።
6 በመንገዱ ነቀፋ የሌለበትን ሰው ጽድቅ ትጠብቀዋለች፤+
ክፋት ግን ኃጢአተኛውን ትጥለዋለች።
7 ምንም ሳይኖረው ባለጸጋ መስሎ ለመታየት የሚሞክር ሰው አለ፤+
ሌላው ደግሞ ብዙ ሀብት እያለው ድሃ መስሎ ይኖራል።
8 የሰው ሀብት ለሕይወቱ ቤዛ ነው፤+
ድሃ ግን ምንም ዓይነት ስጋት የለበትም።+
9 የጻድቃን ብርሃን ደምቆ ይበራል፤+
የክፉዎች መብራት ግን ይጠፋል።+
10 እብሪተኝነት ጠብ ከመፍጠር ውጭ የሚያመጣው ነገር የለም፤+
ምክር በሚሹ ዘንድ ግን ጥበብ ትገኛለች።+
11 በፍጥነት የተገኘ ሀብት ይመናመናል፤+
ጥቂት በጥቂት የሚያጠራቅም ሰው ግን ሀብቱ ይጨምራል።
12 የዘገየ ተስፋ ልብን ያሳምማል፤+
የተሳካ ምኞት ግን የሕይወት ዛፍ ነው።+
13 መመሪያን የሚንቅ ሁሉ ይቀጣል፤+
ትእዛዝን የሚያከብር ግን ብድራት ያገኛል።+
14 የጥበበኛ ሰው ትምህርት የሕይወት ምንጭ ነው፤+
ሰውን ከሞት ወጥመድ እንዲያመልጥ ይረዳዋል።
15 ጥልቅ ማስተዋል ሞገስ ያስገኛል፤
የከዳተኞች መንገድ ግን አስቸጋሪ ነው።
16 ብልህ ሰው ተግባሩን በእውቀት ያከናውናል፤+
ሞኝ ሰው ግን የገዛ ራሱን ሞኝነት ይገልጣል።+
17 ክፉ መልእክተኛ ችግር ውስጥ ይወድቃል፤+
ታማኝ መልእክተኛ ግን ፈውስ ያመጣል።+
18 ተግሣጽን ችላ የሚል ሁሉ ይደኸያል፤ ይዋረዳልም፤
እርማትን የሚቀበል ግን ይከበራል።+
19 ሰው የተመኘው ነገር ሲፈጸም ደስ ይለዋል፤+
ሞኞች ግን ከክፋት መራቅን ይጸየፋሉ።+
20 ከጥበበኞች ጋር የሚሄድ ጥበበኛ ይሆናል፤+
ከሞኞች ጋር የሚገጥም ግን ጉዳት ይደርስበታል።+
21 ኃጢአተኞችን ጥፋት ያሳድዳቸዋል፤+
ጻድቃንን ግን ብልጽግና ይክሳቸዋል።+
22 ጥሩ ሰው ለልጅ ልጆቹ ውርስ ይተዋል፤
የኃጢአተኛ ሀብት ግን ለጻድቅ ይከማቻል።+
23 የድሃ እርሻ ብዙ እህል ያስገኛል፤
ሆኖም ከፍትሕ መጓደል የተነሳ ተጠራርጎ ይጠፋል።
24 ልጁን በበትር ከመምታት ወደኋላ የሚል ይጠላዋል፤+
የሚወደው ግን ተግቶ ይገሥጸዋል።+
25 ጻድቅ ይበላል፤ የምግብ ፍላጎቱንም ያረካል፤+
የክፉ ሰው ሆድ ግን ባዶ ነው።+