ኢዮብ
2 የእጃቸው ብርታት ለእኔ ምን ይፈይድልኝ ነበር?
እነሱ ጉልበት ከድቷቸዋል።
3 ከችጋርና ከረሃብ የተነሳ ዝለዋል፤
በወደመ እና ወና በሆነ ደረቅ ምድር
ያገኟትን ነገር ያላምጣሉ።
4 በቁጥቋጦዎች አጠገብ ያለውን ጨው ጨው የሚል ተክል ይሰበስባሉ፤
ምግባቸው የክትክታ ዛፍ ሥር ነው።
5 ከማኅበረሰቡ ተባረዋል፤+
ሰዎችም ሌባ ላይ እንደሚጮኹ ይጮኹባቸዋል።
6 በሸለቆዎች* ተዳፋት ላይ፣
መሬት ላይ ባሉ ጉድጓዶች ውስጥና በዓለቶች መካከል ይኖራሉ።
7 ከቁጥቋጦዎች ውስጥ ይጮኻሉ፤
በሳማዎችም መካከል ይከማቻሉ።
8 ማመዛዘን የጎደላቸውና የአልባሌ ሰዎች ልጆች ናቸው፤
ከምድሪቱ ላይ ተባረዋል።*
12 በቀኜ በኩል እንደ አድመኛ ተነስተውብኛል፤
እንድሸሽ አድርገውኛል፤
በመንገዴም ላይ ለጥፋት የሚዳርግ መሰናክል አስቀምጠዋል።
14 ሰፊ ክፍተት ባለው ቅጥር እንደሚመጣ ሰው መጡ፤
በፍርስራሹ መካከል እየገሰገሱ ገቡ።
15 በሽብር ተዋጥኩ፤
ክብሬ በነፋስ እንደሚወሰድ ተወስዷል፤
የመዳን ተስፋዬም እንደ ደመና እልም ብሎ ጠፍቷል።
18 ልብሴ በታላቅ ኃይል ተበላሸ፤*
እንደ ልብሴ አንገትጌ አንቆ ያዘኝ።
19 አምላክ ጭቃ ውስጥ ጥሎኛል፤
አፈርና አመድ ሆንኩ።
20 እርዳታ ለማግኘት ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ አንተ ግን አትመልስልኝም፤+
በፊትህ ቆምኩ፤ አንተ ግን ዝም ብለህ ታየኛለህ።
21 በጭካኔ በእኔ ላይ ተነሳህ፤+
በእጅህ ብርታት አጠቃኸኝ።
22 ወደ ላይ አንስተህ በነፋስ ወሰድከኝ፤
ከዚያም በአውሎ ነፋስ አንገላታኸኝ።*
23 በሕይወት ያለ ሁሉ ወደሚሰበሰብበት ቤት፣
ወደ ሞት እንደምታወርደኝ አውቃለሁና።
25 መከራ ላይ ለወደቁ ሰዎች* አላለቀስኩም?
26 መልካም ነገር በተስፋ ብጠባበቅም ክፉ ነገር ደረሰ፤
ብርሃን ብጠባበቅም ጨለማ መጣ።
27 ውስጤ ያለማቋረጥ ተናወጠ፤
የጉስቁልናም ዘመን መጣብኝ።
28 በሐዘን ተውጬ እመላለሳለሁ፤+ የፀሐይ ብርሃንም የለም።
በጉባኤ መካከል ቆሜ እርዳታ ለማግኘት እጮኻለሁ።
29 የቀበሮዎች ወንድም፣
የሰጎንም ሴቶች ልጆች ባልንጀራ ሆንኩ።+
31 በገናዬ ለሐዘን ብቻ ዋለ፤
ዋሽንቴም* ለለቅሶ ሆነ።