ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት ማህሌት።
19 ሰማያት የአምላክን ክብር ይናገራሉ፤+
ጠፈርም የእጆቹን ሥራ ያውጃል።+
2 በየዕለቱ ንግግራቸው ይሰማል፤
በእያንዳንዱም ሌሊት እውቀትን ይገልጣሉ።
3 ንግግር የለም፤ ቃልም የለም፤
ድምፃቸው አይሰማም።
4 ይሁንና ጩኸታቸው ወደ መላው ምድር ወጣ፤
መልእክታቸውም እስከ ዓለም ዳርቻዎች ተሰማ።+
እሱ በሰማያት ለፀሐይ ድንኳን ተክሏል፤
5 ፀሐይም ከጫጉላ ቤት እንደሚወጣ ሙሽራ ነው፤
በጎዳናው ላይ እንደሚሮጥ ብርቱ ሰው ደስ ይለዋል።
6 ከአንደኛው የሰማያት ዳርቻ ይወጣል፤
ዞሮም ወደ ሌላኛው ዳርቻ ይሄዳል፤+
ከሙቀቱም የሚሰወር አንዳች ነገር የለም።
7 የይሖዋ ሕግ ፍጹም ነው፤+ ኃይልን ያድሳል።+
የይሖዋ ማሳሰቢያ አስተማማኝ ነው፤+ ተሞክሮ የሌለውን ጥበበኛ ያደርጋል።+
8 የይሖዋ መመሪያዎች ትክክል ናቸው፤ ልብን ደስ ያሰኛሉ፤+
የይሖዋ ትእዛዝ ንጹሕ ነው፤ ዓይንን ያበራል።+
9 ይሖዋን መፍራት+ ንጹሕ ነው፤ ለዘላለም ይኖራል።
የይሖዋ ፍርዶች እውነት ናቸው፤ ሙሉ በሙሉ ትክክል ናቸው።+
10 ከወርቅ እንዲያውም ብዛት ካለው ምርጥ ወርቅ
የበለጠ የሚወደዱ ናቸው፤+
ደግሞም ከማርና ከማር እንጀራ ከሚንጠባጠብ ወለላ ይበልጥ ይጣፍጣሉ።+
11 ለአገልጋይህ ማስጠንቀቂያ ሆነውለታል፤+
እነሱን መጠበቅ ትልቅ ወሮታ አለው።+
12 የራሱን ስህተት ማን ሊያስተውል ይችላል?+
ሳላውቅ የሠራኋቸውን ኃጢአቶች አትቁጠርብኝ።
13 አገልጋይህንም ከእብሪት ድርጊቶች ጠብቀው፤+
እንዲቆጣጠሩኝም አትፍቀድ።+
ያን ጊዜ እንከን የሌለብኝ እሆናለሁ፤+
ዓይን ካወጣ ኃጢአትም ነፃ እሆናለሁ።
14 ዓለቴና+ አዳኜ+ ይሖዋ ሆይ፣ የአፌ ቃልና በልቤ የማሰላስለው ነገር
አንተን ደስ የሚያሰኝ ይሁን።+