የዳዊት መዝሙር።
26 ይሖዋ ሆይ፣ በንጹሕ አቋም ተመላልሻለሁና ፍረድልኝ፤+
ያለምንም ማወላወል በይሖዋ ታምኛለሁ።+
2 ይሖዋ ሆይ፣ መርምረኝ፤ ፈትነኝም፤
በውስጤ ያለውን ሐሳብና ልቤን አጥራልኝ።+
3 ታማኝ ፍቅርህ ምንጊዜም በፊቴ ነውና፤
በእውነትህም እመላለሳለሁ።+
4 አታላይ ከሆኑ ሰዎች ጋር አልቀራረብም፤+
ማንነታቸውን ከሚደብቁም እርቃለሁ።
5 ከክፉ ሰዎች ጋር መሆን እጠላለሁ፤+
ከክፉዎችም ጋር መቀራረብ አልፈልግም።+
6 ንጹሕ መሆኔን ለማሳየት እጆቼን እታጠባለሁ፤
ይሖዋ ሆይ፣ መሠዊያህን እዞራለሁ፤
7 ይህም የምስጋናን ድምፅ አሰማ ዘንድ፣+
ድንቅ ሥራዎችህንም ሁሉ አውጅ ዘንድ ነው።
8 ይሖዋ ሆይ፣ የምትኖርበትን ቤት፣+
የክብርህንም ማደሪያ ቦታ እወዳለሁ።+
9 ከኃጢአተኞች ጋር አታጥፋኝ፤+
ሕይወቴንም ከዓመፀኞች ጋር አታስወግድ፤
10 እጆቻቸው አሳፋሪ ድርጊት ይፈጽማሉ፤
ቀኝ እጃቸውም በጉቦ የተሞላ ነው።
11 እኔ ግን ንጹሕ አቋሜን ጠብቄ እመላለሳለሁ።
ታደገኝ፤ ሞገስም አሳየኝ።
12 እግሬ በደልዳላ ስፍራ ቆሟል፤+
በታላቅ ጉባኤ መካከል ይሖዋን አወድሳለሁ።+