መዝሙር የዳዊት ማህሌት። 23 ይሖዋ እረኛዬ ነው።+ የሚጎድልብኝ ነገር የለም።+ 2 በለመለመ መስክ ያሳርፈኛል፤ውኃ ወዳለበት የእረፍት ቦታም* ይመራኛል።+ 3 ኃይሌን* ያድሳል።+ ለስሙ ሲል በጽድቅ መንገድ ይመራኛል።+ 4 ድቅድቅ ጨለማ በዋጠው ሸለቆ ውስጥ ብሄድ እንኳ+አንተ ከእኔ ጋር ስለሆንክ፣+ጉዳት ይደርስብኛል ብዬ አልፈራም፤+በትርህና ምርኩዝህ ያበረታቱኛል።* 5 በጠላቶቼ ፊት ማዕድ አዘጋጀህልኝ።+ ራሴን በዘይት ቀባህ፤+ጽዋዬ ጢም ብሎ ሞልቷል።+ 6 ጥሩነትህና ታማኝ ፍቅርህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል፤+ዕድሜዬንም በሙሉ በይሖዋ ቤት እኖራለሁ።+