114 እስራኤል ከግብፅ ሲወጣ፣+
የያዕቆብ ቤት ባዕድ ቋንቋ ከሚናገር ሕዝብ ተለይቶ ሲሄድ፣
2 ይሁዳ መቅደሱ፣
እስራኤልም ግዛቱ ሆነ።+
3 ባሕሩ ይህን አይቶ ሸሸ፤+
ዮርዳኖስ ወደ ኋላ ተመለሰ።+
4 ተራሮች እንደ አውራ በግ፣
ኮረብቶች እንደ ጠቦት ፈነጩ።+
5 አንተ ባሕር ሆይ፣ የሸሸኸው ምን ሆነህ ነው?+
ዮርዳኖስ ሆይ፣ ወደ ኋላ የተመለስከው ለምንድን ነው?+
6 ተራሮች ሆይ፣ እንደ አውራ በግ የዘለላችሁት፣
እናንተ ኮረብቶች፣ እንደ ጠቦት የፈነጫችሁት ለምንድን ነው?
7 ምድር ሆይ፣ ከጌታ የተነሳ፣
ከያዕቆብም አምላክ የተነሳ ተንቀጥቀጪ፤+
8 እሱ ዓለቱን ቄጠማ ወደሞላበት ኩሬ፣
ጠንካራውንም ዓለት ወደ ውኃ ምንጮች ይለውጣል።+