ኢሳይያስ
ነገር ግን በእስራኤል ቅዱስ ተስፋ አያደርጉም፤
ይሖዋንም አይሹም።
2 ይሁንና እሱም ጥበበኛ ነው፤ ጥፋትም ያመጣል፤
ቃሉንም አያጥፍም።
በክፉ አድራጊዎች ቤት ላይ፣
እንዲሁም መጥፎ ነገር የሚሠሩ ሰዎችን በሚረዱ ላይ ይነሳል።+
ይሖዋ እጁን ሲዘረጋ፣
እርዳታ የሚሰጥ ሁሉ ይሰናከላል፤
እርዳታ ተቀባዩም ሁሉ ይወድቃል፤
ሁሉም አንድ ላይ ይጠፋሉ።
4 ይሖዋ እንዲህ ብሎኛልና፦
“አንበሳ ይኸውም ደቦል አንበሳ ባደነው እንስሳ ላይ ቆሞ እንደሚያገሳ፣
ብዙ እረኞች ተጠራርተው ሲመጡበትም
ጩኸታቸው እንደማያሸብረው፣
የሚያሰሙትም ሁካታ እንደማያስፈራው ሁሉ
የሠራዊት ጌታ ይሖዋም ለጽዮን ተራራና ለኮረብታዋ ሲል
ለመዋጋት ይወርዳል።
5 ተወርውረው እንደሚወርዱ ወፎች፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋም እንዲሁ ኢየሩሳሌምን ይከልላታል።+
ይከልላታል፤ ደግሞም ያድናታል።
ከአደጋ ያስጥላታል፤ እንዲሁም ይታደጋታል።”
6 “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ እጅግ ወዳመፃችሁበት አምላክ ተመለሱ።+ 7 በዚያ ቀን እያንዳንዱ ሰው በገዛ እጆቻችሁ በኃጢአት የሠራችኋቸውን የማይረቡ የብር አማልክቱንና ከንቱ የሆኑ የወርቅ አማልክቱን ያስወግዳልና።
እሱም ሰይፉን ፈርቶ ይሸሻል፤
ወጣቶቹም የግዳጅ ሥራ ይሠራሉ።