ለተሰሎንቄ ሰዎች የተጻፈ የመጀመሪያው ደብዳቤ
4 በመጨረሻም ወንድሞች፣ አምላክን ማስደሰት እንድትችሉ እንዴት መመላለስ እንዳለባችሁ አስተምረናችኋል፤+ ደግሞም በዚሁ መንገድ እየተመላለሳችሁ ነው፤ በመሆኑም ይህንኑ ይበልጥ በተሟላ ሁኔታ ማድረጋችሁን እንድትቀጥሉ በጌታ ኢየሱስ ስም እንጠይቃችኋለን እንዲሁም እንለምናችኋለን። 2 በጌታ ኢየሱስ ስም የሰጠናችሁን መመሪያዎች ታውቃላችሁና።
3 የአምላክ ፈቃድ እንድትቀደሱና+ ከፆታ ብልግና* እንድትርቁ ነው።+ 4 ከእናንተ እያንዳንዱ የገዛ ራሱን አካል* በመቆጣጠር+ እንዴት በቅድስናና+ በክብር መያዝ እንዳለበት ሊያውቅ ይገባል። 5 ይህም አምላክን እንደማያውቁት አሕዛብ+ ስግብግብነት በሚንጸባረቅበት ልቅ የፍትወት ስሜት አይሁን።+ 6 ማንም ሰው በዚህ ጉዳይ ከገደቡ ማለፍና ወንድሙን መጠቀሚያ ማድረግ አይኖርበትም፤ ምክንያቱም አስቀድመን እንደነገርናችሁና በጥብቅ እንዳስጠነቀቅናችሁ ይሖዋ* በእነዚህ ነገሮች ሁሉ የተነሳ የቅጣት እርምጃ ይወስዳል። 7 አምላክ የጠራን ለቅድስና ነው እንጂ ለርኩሰት አይደለም።+ 8 እንግዲህ ለዚህ ንቀት የሚያሳይ ሰው የሚንቀው ሰውን ሳይሆን ቅዱስ መንፈሱን የሚሰጣችሁን+ አምላክ ነው።+
9 ይሁን እንጂ እናንተ ራሳችሁ እርስ በርስ እንድትዋደዱ ከአምላክ ስለተማራችሁ+ የወንድማማች ፍቅርን በተመለከተ+ እንድንጽፍላችሁ አያስፈልግም። 10 ደግሞም በመላው መቄዶንያ ለሚገኙ ወንድሞች ሁሉ ይህን እያደረጋችሁ ነው። ሆኖም ወንድሞች፣ ይህን ይበልጥ በተሟላ ሁኔታ ማድረጋችሁን እንድትቀጥሉ እናሳስባችኋለን። 11 ከዚህ በፊት እንዳዘዝናችሁ በሰላም ለመኖር፣+ በሌሎች ሰዎች ጉዳይ ጣልቃ ላለመግባትና+ በገዛ እጃችሁ ለመሥራት ተጣጣሩ፤+ 12 ይህም በውጭ ባሉት* ሰዎች ፊት ሥርዓት ባለው መንገድ እንድትመላለሱና+ ምንም ነገር የሚጎድላችሁ እንዳትሆኑ ነው።
13 በተጨማሪም ወንድሞች፣ ተስፋ እንደሌላቸው+ እንደ ሌሎቹ ሰዎች እንዳታዝኑ በሞት አንቀላፍተው ስላሉት+ ሳታውቁ እንድትቀሩ አንፈልግም። 14 ኢየሱስ እንደሞተና ከሞት እንደተነሳ የምናምን ከሆነ+ ከኢየሱስ ጋር አንድነት ኖሯቸው በሞት ያንቀላፉትንም አምላክ ሕይወት ሰጥቶ ከእሱ ጋር እንዲሆኑ ያደርጋል።+ 15 የይሖዋን* ቃል መሠረት አድርገን የምንነግራችሁ ይህ ነውና፤ ጌታ እስከሚገኝበት ጊዜ ድረስ በሕይወት የምንኖር በሞት አንቀላፍተው ያሉትን በምንም መንገድ አንቀድምም፤ 16 ምክንያቱም ጌታ ራሱ በትእዛዝ ድምፅ፣ በመላእክት አለቃ+ ድምፅና በአምላክ መለከት ድምፅ ከሰማይ ይወርዳል፤ ከክርስቶስ ጋር አንድነት ኖሯቸው የሞቱትም ቀድመው ይነሳሉ።+ 17 ከዚያም በሕይወት ቆይተን የምንተርፈው እኛ በአየር ላይ ከጌታ ጋር ለመገናኘት+ ከእነሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤+ በዚህም መንገድ ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።+ 18 ስለሆነም በእነዚህ ቃላት ሁልጊዜ እርስ በርሳችሁ ተጽናኑ።