91 በልዑል አምላክ ሚስጥራዊ ቦታ የሚኖር ሰው+
ሁሉን ቻይ በሆነው አምላክ ጥላ ሥር ይቀመጣል።+
2 ይሖዋን “አንተ መጠጊያዬና ምሽጌ፣+
የምታመንብህም አምላኬ ነህ”+ እለዋለሁ።
3 እሱ ከወፍ አዳኙ ወጥመድ፣
ከአውዳሚ ቸነፈርም ይታደግሃልና።
4 በላባዎቹ ይከልልሃል፤
በክንፎቹም ሥር መጠጊያ ታገኛለህ።+
ታማኝነቱ+ ትልቅ ጋሻና+ መከላከያ ቅጥር ይሆንልሃል።
5 በሌሊት የሚያሸብሩ ነገሮችን፣
በቀንም የሚወነጨፍ ፍላጻን አትፈራም፤+
6 በጨለማ የሚያደባ ቸነፈርም ሆነ
በቀትር የሚረፈርፍ ጥፋት አያስፈራህም።
7 በአጠገብህ ሺህ፣
በቀኝህም አሥር ሺህ ይወድቃሉ፤
ወደ አንተ ግን አይደርስም።+
8 በክፉዎች ላይ የሚደርሰውን ቅጣት ትመለከታለህ፤
በዓይንህ ብቻ ታየዋለህ።
9 ምክንያቱም “ይሖዋ መጠጊያዬ ነው” ብለሃል፤
ልዑሉን አምላክ መኖሪያህ አድርገኸዋል፤+
10 ምንም ዓይነት አደጋ አይደርስብህም፤+
አንዳችም መቅሰፍት ወደ ድንኳንህ አይጠጋም።
11 በመንገድህ ሁሉ እንዲጠብቁህ+
መላእክቱን ስለ አንተ ያዛልና።+
12 እግርህን እንቅፋት እንዳይመታው+
በእጃቸው ያነሱሃል።+
13 የአንበሳውን ግልገልና ጉበናውን ትረግጣለህ፤
ደቦል አንበሳውንና ትልቁን እባብ ከእግርህ ሥር ትጨፈልቃለህ።+
14 አምላክ እንዲህ ብሏል፦ “ስለወደደኝ፣ እታደገዋለሁ።+
ስሜን ስለሚያውቅ እጠብቀዋለሁ።+
15 ይጠራኛል፤ እኔም እመልስለታለሁ።+
በተጨነቀ ጊዜ ከእሱ ጋር እሆናለሁ።+
እታደገዋለሁ እንዲሁም አከብረዋለሁ።
16 ረጅም ዕድሜን አጠግበዋለሁ፤+
የማዳን ሥራዎቼንም እንዲያይ አደርገዋለሁ።”+