ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የይሖዋ አገልጋይ የሆነው ዳዊት፣ ይሖዋ ከጠላቶቹ ሁሉ እጅና ከሳኦል እጅ ባዳነው ቀን ለይሖዋ የዘመረው መዝሙር፦+
18 ብርታቴ ይሖዋ ሆይ፣+ እወድሃለሁ።
2 ይሖዋ ቋጥኜ፣ ምሽጌና ታዳጊዬ ነው።+
አምላኬ የምሸሸግበት ዓለቴ ነው፤+
ጋሻዬ፣ የመዳኔ ቀንድና አስተማማኝ መጠጊያዬ ነው።+
3 ውዳሴ የሚገባውን ይሖዋን እጠራለሁ፤
ከጠላቶቼም እድናለሁ።+
4 የሞት ገመዶች ተተበተቡብኝ፤+
የማይረቡ ሰዎች የለቀቁት ድንገተኛ ጎርፍ አሸበረኝ።+
5 የመቃብር ገመድ ተጠመጠመብኝ፤
የሞት ወጥመድ ተጋረጠብኝ።+
6 በጭንቅ ውስጥ ሳለሁ ይሖዋን ጠራሁት፤
እርዳታ ለማግኘት አምላኬን አጥብቄ ተማጸንኩት።
በመቅደሱ ሆኖ ድምፄን ሰማ፤+
እርዳታ ለማግኘት የማሰማውም ጩኸት ወደ ጆሮው ደረሰ።+
7 ምድርም ትንቀጠቀጥና ትናወጥ ጀመር፤+
የተራሮች መሠረቶች ተንቀጠቀጡ፤
እሱ ስለተቆጣም ራዱ።+
8 ከአፍንጫው ጭስ ወጣ፤
የሚባላም እሳት ከአፉ ወጣ፤+
ፍምም ከእሱ ፈለቀ።
9 ወደ ታች ሲወርድ ሰማያት እንዲያጎነብሱ አደረገ፤+
ከእግሮቹም በታች ጥቅጥቅ ያለ ደመና ነበር።+
10 በኪሩብ ላይ ተቀምጦ እየበረረ መጣ።+
በመንፈስ ክንፎች በፍጥነት ወረደ።+
11 ከዚያም በጨለማ ራሱን ሸፈነ፤+
ጥቁር ውኃና ጥቅጥቅ ያለ ደመና+
እንደ መጠለያ በዙሪያው ነበር።
12 በፊቱ ካለው ብርሃን፣
ከደመናቱ መካከል በረዶና ፍም ወጣ።
13 ከዚያም ይሖዋ በሰማያት ያንጎደጉድ ጀመር፤+
ልዑሉ አምላክ ድምፁን አሰማ፤+
ደግሞም በረዶና ፍም ነበር።
14 ፍላጻዎቹን አስፈንጥሮ በታተናቸው፤+
መብረቁን አዥጎድጉዶ ግራ አጋባቸው።+
15 ይሖዋ ሆይ፣ ከተግሣጽህ፣ ከአፍንጫህም ከሚወጣው ኃይለኛ እስትንፋስ የተነሳ+
የጅረቶች ወለል ታየ፤+
የምድር መሠረቶችም ተገለጡ።
16 ከላይ ሆኖ እጁን ሰደደ፤
ከጥልቅ ውኃ ውስጥም አወጣኝ።+
17 ከብርቱ ጠላቴ አዳነኝ፤+
ከእኔ ይበልጥ ብርቱዎች ከሆኑት፣ ከሚጠሉኝ ሰዎች ታደገኝ።+
18 ችግር ላይ በወደቅኩበት ቀን ተነሱብኝ፤+
ይሖዋ ግን ድጋፍ ሆነልኝ።
19 ከዚያም ደህንነት ወደማገኝበት ስፍራ አመጣኝ፤
በእኔ ስለተደሰተ ታደገኝ።+
20 ይሖዋ እንደ ጽድቄ ወሮታ ይከፍለኛል፤+
እንደ እጄ ንጽሕና ብድራት ይመልስልኛል።+
21 የይሖዋን መንገድ ጠብቄአለሁና፤
አምላኬን በመተው ክፉ ድርጊት አልፈጸምኩም።
22 ፍርዱ ሁሉ በፊቴ ነው፤
ደንቦቹን ቸል አልልም።
23 በፊቱ እንከን የለሽ ሆኜ እኖራለሁ፤+
ራሴንም ከስህተት እጠብቃለሁ።+
24 ይሖዋ እንደ ጽድቄ፣+
በፊቱ ንጹሕ እንደሆኑት እጆቼ ብድራት ይመልስልኝ።+
25 ታማኝ ለሆነ ሰው ታማኝ ትሆናለህ፤+
እንከን የለሽ ለሆነ ሰው እንከን የለሽ ትሆናለህ፤+
26 ከንጹሕ ሰው ጋር ንጹሕ ሆነህ ትገኛለህ፤+
ጠማማ ለሆነ ሰው ግን ብልህ መሆንህን ታሳያለህ።+
27 ችግረኞችን ታድናለህና፤+
ትዕቢተኛውን ግን ታዋርዳለህ።+
28 ይሖዋ ሆይ፣ መብራቴን የምታበራው አንተ ነህና፤
አምላኬ ሆይ፣ ጨለማዬን ብርሃን የምታደርገው አንተ ነህ።+
29 በአንተ እርዳታ ወራሪውን ቡድን መጋፈጥ እችላለሁ፤+
በአምላክ ኃይል ቅጥር መውጣት እችላለሁ።+
30 የእውነተኛው አምላክ መንገድ ፍጹም ነው፤+
የይሖዋ ቃል የነጠረ ነው።+
እሱ መጠጊያ ለሚያደርጉት ሁሉ ጋሻቸው ነው።+
31 ደግሞስ ከይሖዋ ሌላ አምላክ ማን ነው?+
ከአምላካችንስ ሌላ ዓለት ማን ነው?+
32 ብርታትን የሚያስታጥቀኝ እውነተኛው አምላክ ነው፤+
መንገዴንም ፍጹም ያደርግልኛል።+
33 እግሮቼን እንደ ዋልያ እግሮች ያደርጋል፤
በከፍታ ቦታዎች ላይ ያቆመኛል።+
34 እጆቼን ለጦርነት ያሠለጥናል፤
ክንዶቼ የመዳብ ደጋን ማጠፍ ይችላሉ።
35 የመዳን ጋሻህን ትሰጠኛለህ፤+
ቀኝ እጅህ ይደግፈኛል፤
ትሕትናህም ታላቅ ያደርገኛል።+
36 ለእርምጃዬ መንገዱን ታሰፋልኛለህ፤
እግሮቼ አያዳልጣቸውም።+
37 ጠላቶቼን አሳድጄ እደርስባቸዋለሁ፤
ተጠራርገው እስኪጠፉ ድረስ ወደ ኋላ አልመለስም።
38 እንዳያንሰራሩ አድርጌ አደቃቸዋለሁ፤+
እግሬ ሥር ይወድቃሉ።
39 ለውጊያው ብርታት ታስታጥቀኛለህ፤
ጠላቶቼ ሥሬ እንዲወድቁ ታደርጋለህ።+
40 ጠላቶቼ ከእኔ እንዲሸሹ ታደርጋለህ፤
እኔም የሚጠሉኝን አጠፋቸዋለሁ።+
41 እርዳታ ለማግኘት ይጮኻሉ፤ ሆኖም የሚያድናቸው የለም፤
ወደ ይሖዋም ይጮኻሉ፤ እሱ ግን አይመልስላቸውም።
42 በነፋስ ፊት እንዳለ አቧራ ፈጽሜ አደቃቸዋለሁ፤
በመንገድ ላይ እንዳለ ጭቃ አውጥቼ እጥላቸዋለሁ።
43 ስህተት ከሚለቃቅሙ ሰዎች ታድነኛለህ።+
የብሔራት መሪ አድርገህ ትሾመኛለህ።+
የማላውቀው ሕዝብ ያገለግለኛል።+
44 ስለ እኔ በሰሙት ነገር ብቻ ይታዘዙኛል፤
የባዕድ አገር ሰዎችም አንገታቸውን ደፍተው ወደ ፊቴ ይቀርባሉ።+
45 የባዕድ አገር ሰዎች ወኔ ይከዳቸዋል፤
ከምሽጎቻቸው እየተንቀጠቀጡ ይወጣሉ።
46 ይሖዋ ሕያው ነው! ዓለቴ+ ይወደስ!
የመዳኔ አምላክ ከፍ ከፍ ይበል።+
47 እውነተኛው አምላክ ይበቀልልኛል፤+
ሕዝቦችንም ከበታቼ ያስገዛልኛል።
48 በቁጣ ከተሞሉ ጠላቶቼ ይታደገኛል፤
ከሚያጠቁኝ ሰዎች በላይ ከፍ ከፍ ታደርገኛለህ፤+
ከዓመፀኛ ሰው ታድነኛለህ።
49 ይሖዋ ሆይ፣ በብሔራት መካከል የማከብርህ ለዚህ ነው፤+
ለስምህም የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ።+
50 እሱ ለንጉሡ ታላላቅ የማዳን ሥራዎች ያከናውናል፤+
ለቀባውም ታማኝ ፍቅር ያሳያል፤+
ለዳዊትና ለዘሩ ለዘላለም ይህን ያደርጋል።+