መዝሙር
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በጊቲት።* የቆሬ ልጆች+ መዝሙር። ማህሌት።
ልቤም ሆነ ሥጋዬ ሕያው ለሆነው አምላክ እልል ይላል።
3 ንጉሤና አምላኬ የሆንከው የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣
ታላቁ መሠዊያህ ባለበት አቅራቢያ፣
ወፍ እንኳ በዚያ ቤት ታገኛለች፤
ወንጭፊትም ጫጩቶቿን የምታሳድግበት ጎጆ
ለራሷ ትሠራለች።
4 በቤትህ የሚኖሩ ደስተኞች ናቸው!+
እነሱ ሁልጊዜ ያወድሱሃል።+ (ሴላ)
7 በብርታት ላይ ብርታት እያገኙ ይሄዳሉ፤+
እያንዳንዳቸውም በጽዮን፣ በአምላክ ፊት ይቀርባሉ።
8 የሠራዊት አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ ጸሎቴን ስማ፤
የያዕቆብ አምላክ ሆይ፣ አዳምጠኝ። (ሴላ)
10 በሌላ ቦታ አንድ ሺህ ቀን ከመኖር በቅጥር ግቢዎችህ አንዲት ቀን መዋል ይሻላልና!+
በክፉዎች ድንኳን ከመኖር፣
በአምላኬ ቤት ደጃፍ ላይ መቆም እመርጣለሁ።
ንጹሕ አቋም ይዘው የሚመላለሱትን
ይሖዋ አንዳች መልካም ነገር አይነፍጋቸውም።+