ኤርምያስ
16 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2 “በዚህ ስፍራ ሚስት አታግባ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችም አትውለድ። 3 ይሖዋ በዚህ ስለሚወለዱ ወንዶችና ሴቶች ልጆች እንዲሁም በዚህች ምድር ስለሚወልዷቸው እናቶችና አባቶች እንዲህ ይላልና፦ 4 ‘በገዳይ በሽታዎች ይሞታሉ፤+ ይሁንና ማንም አያለቅስላቸውም ወይም አይቀብራቸውም፤ በምድር ላይ እንደ ፍግ ይሆናሉ።+ በሰይፍና በረሃብ ይጠፋሉ፤+ አስከሬናቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል።’
‘ሰላሜን ከዚህ ሕዝብ ወስጄአለሁና’ ይላል ይሖዋ፤
‘ታማኝ ፍቅሬና ምሕረቴ ከእነሱ እንዲርቅ አድርጌአለሁ።+
6 ታላላቆችም ሆኑ ታናናሾች በዚህች ምድር ላይ ይሞታሉ።
7 ሰው የሞተባቸውንም ለማጽናናት
የእዝን እንጀራ የሚወስድላቸው አይኖርም፤
አባት ወይም እናት ለሞተባቸውም
የመጽናኛ ጽዋ እንዲጠጡ የሚሰጣቸው አይኖርም።
8 ከእነሱ ጋር ተቀምጠህ ለመብላትና ለመጠጣት
ግብዣ ወደተዘጋጀበት ቤት አትግባ።’
9 “የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘በዚህ ስፍራ፣ በእናንተ ዘመን ዓይናችሁ እያየ የሐሴትንና የደስታን ድምፅ እንዲሁም የሙሽራንና የሙሽሪትን ድምፅ አስወግዳለሁ።’+
10 “ይህን ሁሉ ቃል ለዚህ ሕዝብ በምትነግርበት ጊዜ እንዲህ ብለው ይጠይቁሃል፦ ‘ይሖዋ ይህን ሁሉ ታላቅ ጥፋት በእኛ ላይ የተናገረው ለምንድን ነው? በአምላካችን በይሖዋ ላይ የፈጸምነው በደልና ኃጢአት ምንድን ነው?’+ 11 አንተም እንዲህ ብለህ ትመልስላቸዋለህ፦ ‘“አባቶቻችሁ እኔን ስለተዉ ነው”+ ይላል ይሖዋ፤ “ደግሞም ሌሎች አማልክትን ስለተከተሉና ስላገለገሉ እንዲሁም ስለሰገዱላቸው ነው።+ እኔን ግን ትተውኛል፤ ሕጌንም አልጠበቁም።+ 12 እናንተ ደግሞ አባቶቻችሁ ከፈጸሙት የባሰ ነገር አድርጋችኋል፤+ እያንዳንዳችሁም እኔን ከመታዘዝ ይልቅ ግትር የሆነውን ክፉ ልባችሁን ተከተላችሁ።+ 13 ስለዚህ ከዚህች ምድር አስወጥቼ እናንተም ሆነ አባቶቻችሁ ወደማታውቁት ምድር እጥላችኋለሁ፤+ በዚያም ሌሎች አማልክትን ቀን ከሌት ታገለግላላችሁ፤+ ምክንያቱም እኔ ምንም ምሕረት አላሳያችሁም።”’
14 “‘ይሁን እንጂ ከዚህ በኋላ “የእስራኤልን ሕዝብ ከግብፅ ምድር ባወጣው ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ” የማይሉበት ጊዜ ይመጣል’ ይላል ይሖዋ፤+ 15 ‘ከዚህ ይልቅ “እስራኤላውያንን ከሰሜን ምድርና እነሱን ከበተነባቸው አገሮች ሁሉ ሰብስቦ ባመጣቸው ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ” ይባላል፤ እኔም ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠኋት፣ ወደ ምድራቸው እመልሳቸዋለሁ።’+
16 ‘እነሆ፣ እኔ ብዙ ዓሣ አጥማጆችን እሰዳለሁ’ ይላል ይሖዋ፤
‘እነሱንም ያጠምዷቸዋል።
ከዚያም በኋላ ብዙ አዳኞችን እሰዳለሁ፤
እነሱም ከየተራራው፣ ከየኮረብታውና
ከየቋጥኙ ስንጣቂ አድነው ይይዟቸዋል።
17 ዓይኖቼ በሚያደርጉት ነገር ሁሉ* ላይ ነውና።
ከፊቴ አልተሸሸጉም፤
በደላቸውም ከዓይኔ አልተሰወረም።
18 በመጀመሪያ፣ ለሠሩት በደልና ኃጢአት የሚገባቸውን ሙሉ ዋጋ እከፍላቸዋለሁ፤+
ምድሬን አስጸያፊ በሆኑ ጣዖቶቻቸው በድን ምስሎች* አርክሰዋልና፤
ርስቴንም አስነዋሪ በሆኑ ነገሮች ሞልተዋል።’”+
19 ብርታቴና መጠጊያዬ፣
በጭንቀት ጊዜ መሸሸጊያዬ የሆንከው ይሖዋ ሆይ፣+
ብሔራት ከምድር ዳርቻዎች ወደ አንተ ይመጣሉ፤
እንዲህም ይላሉ፦ “አባቶቻችን ፍጹም ውሸትን፣
ከንቱ የሆኑና ምንም ጥቅም የሌላቸውን የማይረቡ ነገሮች ወርሰዋል።”+
20 ሰው ለራሱ አማልክት ሊሠራ ይችላል?
የሚሠራቸው አማልክት እውነተኛ አማልክት አይደሉም።+
21 “ስለዚህ አስተምራቸዋለሁ፤
በዚህ ጊዜ ኃይሌንና ብርታቴን እንዲያውቁ አደርጋለሁ፤
እነሱም ስሜ ይሖዋ መሆኑን ያውቃሉ።”