ኢሳይያስ
ሁልጊዜ ጨቋኝ ድንጋጌዎችን የሚያረቁ ወዮላቸው!
2 የድሆችን አቤቱታ ላለመስማት፣
በሕዝቤም መካከል የሚገኙትን ምስኪኖች ፍትሕ ለመንፈግ ሕግ የሚያወጡ ወዮላቸው!+
መበለቶችን ይበዘብዛሉ፤
4 በእስረኞች መካከል ተኮራምታችሁ ከመቀመጥና
በሞቱ ሰዎች መካከል ከመውደቅ በስተቀር የምታተርፉት ነገር የለም።
ከዚህ ሁሉ የተነሳ ቁጣው አልተመለሰም፤
ይልቁንም እጁ ለመምታት ገና እንደተዘረጋ ነው።+
6 ከሃዲ በሆነው ብሔር ላይ፣
እጅግ ባስቆጣኝም ሕዝብ ላይ እልከዋለሁ፤+
ብዙ ምርኮ እንዲወስድ፣ ብዙ ሀብት እንዲዘርፍና
ሕዝቡን በጎዳናዎች ላይ እንዳለ ጭቃ እንዲረጋግጥ አዘዋለሁ።+
12 “ይሖዋ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም የሚያከናውነውን ሥራ ሁሉ ሲያጠናቅቅ በእብሪተኛ ልቡ፣ በኩራቱና በትዕቢተኛ ዓይኑ የተነሳ የአሦርን ንጉሥ ይቀጣዋል።*+ 13 እሱ እንዲህ ይላልና፦
‘በእጄ ብርታትና በጥበቤ
ይህን አደርጋለሁ፤ እኔ ጥበበኛ ነኝና።
ክንፎቹን የሚያራግብ ወይም አፉን የሚከፍት አሊያም የሚጮኽ አይኖርም።’”
15 መጥረቢያ፣ በሚቆርጥበት ሰው ላይ ይኩራራል?
መጋዝ፣ በሚገዘግዝበት ሰው ላይ ራሱን ከፍ ከፍ ያደርጋል?
በትር፣+ የሚያነሳውን ሰው ወዲያና ወዲህ ማንቀሳቀስ ይችላል?
ወይስ ዱላ፣ ከእንጨት ያልተሠራውን ሰው ወደ ላይ ከፍ ማድረግ ይችላል?
19 በደኑ ውስጥ የሚተርፉት ዛፎች
ጥቂት ከመሆናቸው የተነሳ አንድ ትንሽ ልጅ ቆጥሮ ሊመዘግባቸው ይችላል።
20 በዚያ ቀን ከእስራኤላውያን መካከል የሚቀሩት፣
ከያዕቆብም ቤት የሚተርፉት ሰዎች
ከእንግዲህ ወዲህ፣ በመታቸው ላይ ፈጽሞ አይታመኑም፤+
ከዚህ ይልቅ የእስራኤል ቅዱስ በሆነው በይሖዋ ላይ
በታማኝነት ይደገፋሉ።
24 ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በጽዮን የምትኖር ሕዝቤ ሆይ፣ በበትር+ ይመታህና ግብፅ እንዳደረገብህ+ ዱላውን በአንተ ላይ ያነሳ የነበረውን አሦርን አትፍራ። 25 ከጥቂት ጊዜ በኋላ ውግዘቱ ያበቃልና፤ ቁጣዬም እስኪጠፉ ድረስ በእነሱ ላይ ይነድዳል።+ 26 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ በኦሬብ ዓለት ምድያምን ድል እንዳደረገ+ ሁሉ ጅራፉን በእሱ ላይ ያወዛውዛል።+ በትሩም በባሕሩ ላይ ይሆናል፤ በግብፅ ላይ እንዳደረገውም በትሩን ያነሳዋል።+
30 የጋሊም ሴት ልጅ ሆይ፣ እሪታሽን አቅልጪው!
ላይሻ ሆይ፣ አዳምጪ!
ምስኪኗ አናቶት+ ሆይ፣ ጩኺ!
31 ማድመና ሸሽታለች።
የጌቢም ነዋሪዎች መሸሸጊያ ፈለጉ።
በጽዮን ሴት ልጅ ተራራ፣
በኢየሩሳሌም ኮረብታ ላይ እጁን በዛቻ ያወዛውዛል።
34 በደን ውስጥ ያለውን ጥሻ በብረት መሣሪያ* ይቆራርጣል፤
ሊባኖስም በኃያሉ እጅ ይወድቃል።