አንደኛ መጽሐፍ
(መዝሙር 1-41)
1 በክፉዎች ምክር የማይሄድ፣
በኃጢአተኞች መንገድ+ የማይቆም፣
በፌዘኞችም+ ወንበር የማይቀመጥ ሰው ደስተኛ ነው።
2 ይልቁንም በይሖዋ ሕግ ደስ ይለዋል፤+
ሕጉንም በቀንና በሌሊት በለሆሳስ ያነበዋል።+
3 በጅረቶች ዳር እንደተተከለ፣
ፍሬውን በወቅቱ እንደሚሰጥ፣
ቅጠሉም እንደማይጠወልግ ዛፍ ይሆናል።
የሚሠራውም ሁሉ ይሳካለታል።+
4 ክፉዎች እንዲህ አይደሉም፤
ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስደው ገለባ ናቸው።
5 ከዚህም የተነሳ ክፉዎች በፍርድ ፊት ለዘለቄታው አይቆሙም፤+
ኃጢአተኞችም በጻድቃን ጉባኤ ጸንተው አይቆሙም።+
6 ይሖዋ የጻድቃንን መንገድ ያውቃልና፤+
የክፉዎች መንገድ ግን ይጠፋል።+