ኤርምያስ
5 በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ ወዲያና ወዲህ ተመላለሱ።
ዙሪያውን ተመልከቱ፤ ልብ በሉ።
2 “ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ!” ቢሉም
የሚምሉት ሐሰት ለሆነ ነገር ነው።+
3 ይሖዋ ሆይ፣ ዓይኖችህ የሚመለከቱት ታማኝ የሆኑ ሰዎችን ለማግኘት አይደለም?+
አንተ መተሃቸዋል፤ በእነሱ ላይ ግን ያመጣው ለውጥ የለም።*
አንተ አድቅቀሃቸዋል፤ እነሱ ግን አልታረሙም።+
4 እኔ ግን ለራሴ እንዲህ አልኩ፦ “በእርግጥ እነዚህ ምስኪኖች ናቸው።
የይሖዋን መንገድ፣ የአምላካቸውንም ፍርድ ባለማወቃቸው
የሞኝነት ድርጊት ይፈጽማሉ።
ነገር ግን ሁሉም ቀንበሩን ሰብረዋል፤
ማሰሪያውንም በጥሰዋል።”
6 ስለዚህ ከጫካ የወጣ አንበሳ ይሰባብራቸዋል፤
የበረሃ ተኩላም ይቦጫጭቃቸዋል፤
ነብር በከተሞቻቸው አቅራቢያ አድብቶ ይጠብቃል።
ከዚያ የሚወጣውንም ሁሉ ይዘነጣጥላል።
በደላቸው በዝቷልና፤
የክህደት ሥራቸው ተበራክቷል።+
7 ታዲያ ይህን ነገር እንዴት ይቅር እልሻለሁ?
ወንዶች ልጆችሽ ትተውኛል፤
አምላክ ባልሆነውም ይምላሉ።+
እኔም የሚያስፈልጋቸውን ነገር አሟላሁላቸው፤
እነሱ ግን ምንዝር መፈጸማቸውን ቀጠሉ፤
ወደ ዝሙት አዳሪ ቤትም እየተንጋጉ ሄዱ።
8 እንደሚቅበጠበጡ፣ ብርቱ ፈረሶች ናቸው፤
እያንዳንዱ የሌላውን ሰው ሚስት ተከትሎ ያሽካካል።+
9 “ታዲያ በእነዚህ ነገሮች የተነሳ ተጠያቂ ላደርጋቸው አይገባም?” ይላል ይሖዋ።
“እንዲህ ዓይነቱን ሕዝብ ልበቀል* አይገባም?”+
10 “የወይን እርሻዋን እርከኖች ሄዳችሁ አበላሹ፤
ሆኖም ሙሉ በሙሉ አታጥፉት።+
የተንሰራፉ ቅርንጫፎቿን አስወግዱ፤
የይሖዋ አይደሉምና።
11 የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት
በእኔ ላይ ከፍተኛ ክህደት ፈጽመዋልና” ይላል ይሖዋ።+
በእኛ ላይ ምንም ጥፋት አይመጣም፤
ሰይፍም ሆነ ረሃብ አናይም’ ይላሉ።+
13 ነቢያቱ በነፋስ የተሞሉ ናቸው፤
ቃሉም* በውስጣቸው የለም።
ይህ በእነሱ ላይ ይድረስ!”
14 ስለዚህ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
15 “የእስራኤል ቤት ሆይ፣ እነሆ፣ በሩቅ ቦታ ያለን ብሔር አመጣባችኋለሁ”+ ይላል ይሖዋ።
“እሱም ለረጅም ጊዜ የኖረ ብሔር ነው።
16 የፍላጻ ኮሮጇቸው እንደተከፈተ መቃብር ነው፤
ሁሉም ተዋጊዎች ናቸው።
17 እነሱ አዝመራህንና ምግብህን ይበላሉ።+
ወንዶችና ሴቶች ልጆችህን ይበላሉ።
መንጎችህንና ከብቶችህን ይበላሉ።
የወይን ተክሎችህንና የበለስ ዛፎችህን ይበላሉ።
የምትታመንባቸውን የተመሸጉ ከተሞችህን በሰይፍ ያወድማሉ።”
18 “ይሁንና በእነዚያ ቀናት እንኳ” ይላል ይሖዋ፣ “ሙሉ በሙሉ አላጠፋችሁም።+ 19 ‘አምላካችን ይሖዋ እነዚህን ሁሉ ነገሮች ያደረገብን ለምንድን ነው?’ ብለው ሲጠይቁ ደግሞ ‘በምድራችሁ ላይ ባዕድ አምላክን ለማገልገል ስትሉ እኔን እንደተዋችሁኝ ሁሉ የራሳችሁ ባልሆነ ምድር ባዕዳንን ታገለግላላችሁ’ ትላቸዋለህ።”+
20 ይህን በያዕቆብ ቤት ተናገሩ፤
በይሁዳም እንዲህ ብላችሁ አውጁ፦
21 “እናንተ ሞኞችና የማመዛዘን ችሎታ የጎደላችሁ ሰዎች* ይህን ስሙ፦+
22 ‘እኔን አትፈሩም?’ ይላል ይሖዋ፤
‘በፊቴስ ልትሸበሩ አይገባም?
ውኃው አልፎ እንዳይሄድ፣ በማይሻር ድንጋጌ
አሸዋውን የባሕሩ ወሰን አድርጌ የሠራሁት እኔ ነኝ።
ሞገዶቹ ቢናወጡም ጥሰው መሄድ አይችሉም፤
ቢያስገመግሙም ከዚያ አልፈው መሄድ አይችሉም።+
23 ነገር ግን ይህ ሕዝብ ልቡ ግትርና ዓመፀኛ ነው፤
ጀርባቸውን ሰጥተው በራሳቸው መንገድ ሄደዋል።+
24 እነሱም በልባቸው
“እንግዲያው፣ ዝናቡን ይኸውም የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ
በወቅቱ የሚሰጠንን፣
የተወሰኑትን የአዝመራ ሳምንታት የሚጠብቅልንን
አምላካችንን ይሖዋን እንፍራ” አላሉም።+
25 የገዛ ራሳችሁ በደል እነዚህ ነገሮች እንዲቀሩ አድርጓል፤
የገዛ ኃጢአታችሁ መልካም የሆነ ነገር አሳጥቷችኋል።+
26 በሕዝቤ መካከል ክፉ ሰዎች አሉና።
አድብተው እንደሚጠብቁ ወፍ አዳኞች፣ በዓይነ ቁራኛ ይመለከታሉ።
ገዳይ ወጥመድ ይዘረጋሉ።
ሰዎችን ያጠምዳሉ።
27 በወፎች እንደተሞላ የወፍ ጎጆ፣
ቤቶቻቸው በማታለያ የተሞሉ ናቸው።+
ኃያላንና ሀብታም የሆኑት ለዚህ ነው።
28 ወፍረዋል፤ ቆዳቸውም ለስልሷል፤
በክፋት ተሞልተዋል።
29 “ታዲያ በእነዚህ ነገሮች የተነሳ ተጠያቂ ላደርጋቸው አይገባም?” ይላል ይሖዋ።
“እንዲህ ዓይነቱን ሕዝብ ልበቀል* አይገባም?
30 በምድሪቱ ላይ የሚያስደነግጥና የሚያሰቅቅ ነገር ተከስቷል፦
31 ነቢያቱ የሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤+
ካህናቱም በራሳቸው ሥልጣን በኃይል ይገዛሉ።
የገዛ ሕዝቤም ይህን ወዶታል።+
ይሁንና መጨረሻው ሲመጣ ምን ታደርጉ ይሆን?”