ነህምያ
12 ከሰላትያል+ ልጅ ከዘሩባቤልና+ ከየሆሹዋ+ ጋር የወጡት ካህናትና ሌዋውያን የሚከተሉት ነበሩ፦ ሰራያህ፣ ኤርምያስ፣ ዕዝራ፣ 2 አማርያህ፣ ማሉክ፣ ሃጡሽ፣ 3 ሸካንያህ፣ ረሁም፣ መሬሞት፣ 4 ኢዶ፣ ጊነቶአይ፣ አቢያህ፣ 5 ሚያሚን፣ ማአድያህ፣ ቢልጋ፣ 6 ሸማያህ፣ ዮያሪብ፣ የዳያህ፣ 7 ሳሉ፣ አሞቅ፣ ኬልቅያስ እና የዳያህ። እነዚህ በየሆሹዋ ዘመን የካህናቱና የወንድሞቻቸው መሪዎች ነበሩ።
8 ሌዋውያኑ ደግሞ የሹዋ፣ ቢኑይ፣ ቃድሚኤል፣+ ሸረበያህ፣ ይሁዳ እና ከወንድሞቹ ጋር ሆኖ የምስጋና መዝሙሮቹን የሚመራው ማታንያህ+ ነበሩ። 9 ወንድሞቻቸው ባቅቡቅያ እና ዑኒ ከእነሱ ትይዩ ለጥበቃ ቆመው ነበር።* 10 የሹዋ ዮአቂምን ወለደ፤ ዮአቂምም ኤልያሺብን+ ወለደ፤ ኤልያሺብም ዮያዳን+ ወለደ። 11 ዮያዳም ዮናታንን ወለደ፤ ዮናታንም ያዱአን ወለደ።
12 በዮአቂም ዘመን የአባቶች ቤት መሪዎች የሆኑት ካህናት የሚከተሉት ነበሩ፦ ከሰራያህ+ መራያህ፣ ከኤርምያስ ሃናንያህ፣ 13 ከዕዝራ+ መሹላም፣ ከአማርያህ የሆሃናን፣ 14 ከማሉኪ ዮናታን፣ ከሸባንያህ ዮሴፍ፣ 15 ከሃሪም+ አድና፣ ከመራዮት ሄልቃይ፣ 16 ከኢዶ ዘካርያስ፣ ከጊነቶን መሹላም፣ 17 ከአቢያህ+ ዚክሪ፣ ከሚንያሚን . . . ፣* ከሞአድያህ ፒልጣይ፣ 18 ከቢልጋ+ ሻሙአ፣ ከሸማያህ የሆናታን፣ 19 ከዮያሪብ ማቴናይ፣ ከየዳያህ+ ዑዚ፣ 20 ከሳላይ ቃላይ፣ ከአሞቅ ኤቤር፣ 21 ከኬልቅያስ ሃሻብያህ፣ ከየዳያህ ናትናኤል ተወክለው ነበር።
22 በኤልያሺብ፣ በዮያዳ፣ በዮሃናን እና በያዱአ+ ዘመን የነበሩት የሌዋውያኑ የአባቶች ቤት መሪዎች ልክ እንደ ካህናቱ ሁሉ እስከ ፋርሳዊው ዳርዮስ የንግሥና ዘመን ድረስ ተመዘገቡ።
23 የአባቶች ቤት መሪዎች የነበሩት ሌዋውያን የኤልያሺብ ልጅ እስከሆነው እስከ ዮሃናን ዘመን ድረስ በዘመኑ በነበረው የታሪክ መጽሐፍ ላይ ተመዝግበው ነበር። 24 የሌዋውያኑ መሪዎች ሃሻብያህ፣ ሸረበያህና የቃድሚኤል+ ልጅ የሹዋ+ ነበሩ፤ ወንድሞቻቸውም ከእነሱ ትይዩ ቆመው ይኸውም አንዱ የጥበቃ ቡድን ከሌላው የጥበቃ ቡድን ጎን ለጎን ሆኖ የእውነተኛው አምላክ ሰው ዳዊት በሰጠው መመሪያ መሠረት+ ለአምላክ ውዳሴና ምስጋና ያቀርቡ ነበር። 25 ማታንያህ፣+ ባቅቡቅያ፣ አብድዩ፣ መሹላም፣ ታልሞን እና አቁብ+ እንደ በር ጠባቂዎች+ ዘብ በመቆም በበሮቹ አጠገብ ያሉትን ግምጃ ቤቶች ይጠብቁ ነበር። 26 እነዚህም በዮጻዴቅ ልጅ፣ በየሆሹዋ+ ልጅ በዮአቂም ዘመን እንዲሁም በገዢው በነህምያና የቅዱሳን መጻሕፍት ገልባጭ* በሆነው በካህኑ ዕዝራ+ ዘመን አገለገሉ።
27 የኢየሩሳሌም ቅጥሮች በሚመረቁበት ጊዜ የምረቃውን በዓል በምስጋና መዝሙር፣+ በሲምባል፣* በባለ አውታር መሣሪያዎችና በበገና በደስታ እንዲያከብሩ ሌዋውያኑን ከሚኖሩበት ስፍራ ሁሉ ፈልገው ወደ ኢየሩሳሌም አመጧቸው። 28 የዘማሪዎቹ ወንዶች ልጆችም* ከአውራጃው፣* በኢየሩሳሌም ዙሪያ ካሉት ቦታዎች ሁሉና ነጦፋውያን+ ከሰፈሩባቸው መንደሮች ተሰበሰቡ፤ 29 እንዲሁም ከቤትጊልጋል፣+ ከጌባ+ የእርሻ ቦታዎችና ከአዝማዌት+ ተሰበሰቡ፤ ምክንያቱም ዘማሪዎቹ በኢየሩሳሌም ዙሪያ ለራሳቸው የሰፈራ መንደሮችን መሥርተው ነበር። 30 ካህናቱና ሌዋውያኑም ራሳቸውን አነጹ፤+ ሕዝቡን፣ በሮቹንና+ ቅጥሩንም+ አነጹ።
31 ከዚያም የይሁዳን መኳንንት አምጥቼ በቅጥሩ አናት ላይ እንዲቆሙ አደረግኩ። በተጨማሪም ምስጋና የሚያቀርቡ ሁለት ትላልቅ የዘማሪ ቡድኖችን እንዲሁም እነሱን የሚያጅቡ ቡድኖችን መደብኩ፤ አንደኛው ቡድን በስተ ቀኝ በኩል በቅጥሩ አናት ላይ ወደ አመድ ቁልል በር+ ሄደ። 32 ሆሻያህ እና ከይሁዳ መኳንንት ግማሾቹ ከኋላ ተከተሏቸው፤ 33 ከእነሱም ጋር አዛርያስ፣ ዕዝራ፣ መሹላም፣ 34 ይሁዳ፣ ቢንያም፣ ሸማያህ እና ኤርምያስ ነበሩ። 35 መለከት ከሚነፉት+ ካህናት ወንዶች ልጆች መካከል የተወሰኑት አብረዋቸው ነበሩ፤ እነሱም የአሳፍ+ ልጅ፣ የዛኩር ልጅ፣ የሚካያህ ልጅ፣ የማታንያህ ልጅ፣ የሸማያህ ልጅ፣ የዮናታን ልጅ ዘካርያስ 36 እንዲሁም ወንድሞቹ ሸማያህ፣ አዛርዔል፣ ሚላላይ፣ ጊላላይ፣ ማአይ፣ ናትናኤል፣ ይሁዳ እና ሃናኒ ናቸው፤ እነሱም የእውነተኛውን አምላክ ሰው የዳዊትን የሙዚቃ መሣሪያዎች+ ይዘው ነበር፤ የቅዱሳን መጻሕፍት ገልባጭ* የሆነው ዕዝራም+ ከፊታቸው ይሄድ ነበር። 37 ከዚያም፣ ምንጭ በር+ ጋ ሲደርሱ ሽቅብ የሚወጣውን ቅጥር ይዘው ፊት ለፊት ቀጥ ብለው በመሄድ በዳዊት ከተማ+ ደረጃ+ ላይ አልፈው ከዳዊት ቤት በላይ ወዳለው ስፍራና በስተ ምሥራቅ ወዳለው ወደ ውኃ በር+ አቀኑ።
38 ምስጋና የሚያቀርበው ሌላኛው የዘማሪዎች ቡድን ደግሞ በተቃራኒ አቅጣጫ ሄደ፤ እኔም ከግማሹ ሕዝብ ጋር በመሆን ቡድኑን ተከትዬ በቅጥሩ አናት ላይ በመሄድ የመጋገሪያ ምድጃ ማማን+ አልፌ ወደ ሰፊ ቅጥር+ ተጓዝኩ፤ 39 ከዚያም በኤፍሬም በርና+ በአሮጌው ከተማ በር+ አድርጌ ወደ ዓሣ በር፣+ ወደ ሃናንኤል ማማና+ ወደ መአህ ማማ፣ በኋላም ወደ በግ በር+ ሄድኩ፤ እነሱም የጠባቂው በር ጋ ሲደርሱ ቆሙ።
40 በመጨረሻም ምስጋና የሚያቀርቡት ሁለቱም የዘማሪ ቡድኖች በእውነተኛው አምላክ ቤት ፊት ለፊት ቆሙ፤ እኔም እንዲሁ አደረግኩ፤ በተጨማሪም ከእኔ ጋር የነበሩት ግማሾቹ የበታች ገዢዎች፣ 41 ካህናት የሆኑት ኤልያቄም፣ ማአሴያህ፣ ሚንያሚን፣ ሚካያህ፣ ኤሊዮዔናይ፣ ዘካርያስና ሃናንያህ ከነመለከታቸው 42 እንዲሁም ማአሴያህ፣ ሸማያህ፣ አልዓዛር፣ ዑዚ፣ የሆሃናን፣ ማልኪያህ፣ ኤላም እና ኤጼር አብረውኝ ቆሙ። ዘማሪዎቹም በይዝራህያህ መሪነት ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ዘመሩ።
43 እውነተኛው አምላክ እጅግ እንዲደሰቱ ስላደረጋቸው በዚያን ቀን ብዙ መሥዋዕት አቀረቡ፤ ሐሴትም አደረጉ።+ ሴቶችና ልጆችም ጭምር በጣም ተደሰቱ፤+ ስለዚህ የኢየሩሳሌም ደስታ ከሩቅ ይሰማ ነበር።+
44 በዚያን ቀን መዋጮዎች፣+ የእህል በኩራትና+ አሥራት+ በሚቀመጡባቸው ግምጃ ቤቶች+ ላይ ሰዎች ተሾሙ። እነሱም በሕጉ ላይ በታዘዘው መሠረት ለካህናቱና ለሌዋውያኑ የሚሰጠውን ድርሻ ከየከተሞቹ እርሻዎች እየሰበሰቡ ወደዚያ ማስገባት ነበረባቸው፤+ ምክንያቱም በሚያገለግሉት ካህናትና ሌዋውያን+ የተነሳ በይሁዳ ውስጥ ታላቅ ደስታ ነበር። 45 ዘማሪዎቹና በር ጠባቂዎቹ እንዳደረጉት ሁሉ ካህናቱና ሌዋውያኑም አምላካቸው የሚጠብቅባቸውን ግዴታም ሆነ ከመንጻት ጋር በተያያዘ የተጣለባቸውን ኃላፊነት ዳዊትና ልጁ ሰለሞን በሰጡት መመሪያ መሠረት መወጣት ጀመሩ። 46 ጥንት በዳዊትና በአሳፍ ዘመን ዘማሪዎቹን እንዲሁም ለአምላክ የሚቀርቡትን የውዳሴና የምስጋና መዝሙሮች የሚመሩ ሰዎች ነበሩ።+ 47 እንዲሁም በዘሩባቤል+ ዘመንና በነህምያ ዘመን እስራኤላውያን በሙሉ ለዘማሪዎቹና+ ለበር ጠባቂዎቹ+ በየዕለቱ የሚያስፈልጋቸውን ያህል ድርሻ ይሰጧቸው ነበር። በተጨማሪም ለሌዋውያኑ የሚገባውን ድርሻ+ ለይተው ያስቀምጡ የነበረ ሲሆን ሌዋውያኑ ደግሞ ለአሮን ዘሮች የሚገባውን ድርሻ ለይተው ያስቀምጡ ነበር።