የዳዊት መዝሙር።
103 ይሖዋን ላወድስ፤
ሁለንተናዬ ቅዱስ ስሙን ያወድስ።
2 ይሖዋን ላወድስ፤
ያደረጋቸውን ነገሮች ሁሉ ፈጽሞ አልርሳ።+
3 እሱ በደልሽን ሁሉ ይቅር ይላል፤+
ሕመምሽንም ሁሉ ይፈውሳል፤+
4 ሕይወትሽን ከጉድጓድ ያወጣል፤+
ታማኝ ፍቅሩንና ምሕረቱን ያጎናጽፍሻል፤+
5 የወጣትነት ዕድሜሽ እንደ ንስር እንዲታደስ፣+
በሕይወት ዘመንሽ ሁሉ መልካም ነገሮች ያጠግብሻል።+
6 ይሖዋ ለተጨቆኑ ሁሉ
በጽድቅና በፍትሕ እርምጃ ይወስዳል።+
7 መንገዶቹን ለሙሴ፣
ያከናወናቸውንም ነገሮች ለእስራኤል ልጆች አሳወቀ።+
8 ይሖዋ መሐሪና ሩኅሩኅ፣+
ለቁጣ የዘገየ እንዲሁም ታማኝ ፍቅሩ የበዛ ነው።+
9 እሱ ሁልጊዜ ስህተት አይፈላልግም፤+
ለዘላለምም ቂም አይዝም።+
10 እንደ ኃጢአታችን አላደረገብንም፤+
ለበደላችን የሚገባውንም ብድራት አልከፈለንም።+
11 ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፣
እሱ ለሚፈሩት የሚያሳየው ታማኝ ፍቅር ታላቅ ነውና።+
12 ምሥራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ፣
በደላችንን ከእኛ አራቀ።+
13 አባት ለልጆቹ ምሕረት እንደሚያሳይ፣
ይሖዋም ለሚፈሩት ምሕረት አሳይቷል።+
14 እሱ እንዴት እንደተሠራን በሚገባ ያውቃልና፤+
አፈር መሆናችንን ያስታውሳል።+
15 ሟች የሆነ የሰው ልጅ የሕይወት ዘመኑ እንደ ሣር ነው፤+
እንደ ሜዳ አበባ ያብባል።+
16 ይሁንና ነፋስ ሲነፍስበት ደብዛው ይጠፋል፤
በዚያ ስፍራ ያልነበረ ያህል ይሆናል።
17 ይሖዋ ግን እሱን ለሚፈሩት
ታማኝ ፍቅሩን ከዘላለም እስከ ዘላለም ያሳያል፤+
ጽድቁንም ለልጅ ልጆቻቸው ይገልጣል፤+
18 ይህን የሚያደርገው ቃል ኪዳኑን ለሚጠብቁ፣+
መመሪያዎቹን ለመፈጸም ለሚተጉ ነው።
19 ይሖዋ ዙፋኑን በሰማያት አጽንቶ መሥርቷል፤+
በሁሉም ላይ ንጉሥ ሆኖ ይገዛል።+
20 ትእዛዛቱን በማክበር ቃሉን የምትፈጽሙ፣+
እናንተ ብርቱዎችና ኃያላን መላእክቱ ሁሉ፣+ ይሖዋን አወድሱ።
21 ፈቃዱን የምታደርጉ አገልጋዮቹ፣+
ሠራዊቱ ሁሉ፣ ይሖዋን አወድሱ።+
22 በግዛቱ ሁሉ ያላችሁ፣
ፍጥረታቱ ሁሉ፣ ይሖዋን አወድሱ።
ሁለንተናዬ ይሖዋን ያወድስ።