ኤርምያስ
20 በይሖዋ ቤት ዋና ሹም የነበረው የኢሜር ልጅ ካህኑ ጳስኮር፣ ኤርምያስ እነዚህን ነገሮች ሲተነብይ ሰማ። 2 ጳስኮርም ነቢዩ ኤርምያስን መታው፤ ከዚያም በይሖዋ ቤት ባለው በላይኛው የቢንያም በር በእግር ግንድ ጠረቀው።+ 3 ይሁንና በማግስቱ ጳስኮር ኤርምያስን ከእግር ግንዱ ውስጥ ፈታው፤ በዚህ ጊዜ ኤርምያስ እንዲህ አለው፦
“ይሖዋ፣ ማጎርሚሳቢብ*+ ብሎ ይጠራሃል እንጂ ጳስኮር አይልህም። 4 ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘አንተም ሆንክ ወዳጆችህ እንድትሸበሩ አደርጋለሁ፤ እነሱም ዓይንህ እያየ በጠላቶቻቸው ሰይፍ ይወድቃሉ፤+ ይሁዳንም ሁሉ ለባቢሎን ንጉሥ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እሱም በግዞት ወደ ባቢሎን ይወስዳቸዋል፤ በሰይፍም ይገድላቸዋል።+ 5 የዚህችን ከተማ ሀብት ሁሉ፣ ጥሪቷን ሁሉ፣ ውድ የሆኑትን ነገሮች ሁሉ እንዲሁም የይሁዳን ነገሥታት ውድ ሀብት ሁሉ በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ።+ እነሱም ይበዘብዟቸዋል፤ ወደ ባቢሎንም ያግዟቸዋል።+ 6 ጳስኮር ሆይ፣ አንተና በቤትህ የሚኖሩ ሁሉ በግዞት ትወሰዳላችሁ። ወደ ባቢሎን ትሄዳለህ፤ በዚያም ትሞታለህ፤ ከወዳጆችህም ሁሉ ጋር በዚያ ትቀበራለህ፤ ምክንያቱም ለእነሱ የሐሰት ትንቢት ተናግረሃል።’”+
7 ይሖዋ ሆይ፣ አሞኘኸኝ፤ እኔም ተሞኘሁ።
አንተ በእኔ ላይ በረታህ፤ አሸነፍክም።+
እኔም ቀኑን ሙሉ መሳለቂያ ሆንኩ፤
ሁሉም ያፌዙብኛል።+
8 በተናገርኩ ቁጥር እጮኻለሁና፤
“ዓመፅና ጥፋት!” ብዬ አውጃለሁ።
የይሖዋ ቃል ቀኑን ሙሉ ስድብና ፌዝ አስከትሎብኛል።+
10 ብዙ መጥፎ ወሬ ሰምቻለሁና፤
በዙሪያዬ ያለው ሁኔታ አሸብሮኛል።+
“አውግዙት፤ እናውግዘው!”
ሰላም የሚመኝልኝ ሰው ሁሉ የእኔን ውድቀት ይጠባበቃል፦+
“ምናልባት ይታለል ይሆናል፤
እኛም እናሸንፈዋለን፤ ደግሞም እንበቀለዋለን።”
11 ይሖዋ ግን እንደ አስፈሪ ተዋጊ ከእኔ ጋር ነበር።+
ከዚህም የተነሳ የሚያሳድዱኝ ሰዎች ይሰናከላሉ እንጂ አያሸንፉም።+
ስለማይሳካላቸውም ለከፍተኛ ኀፍረት ይዳረጋሉ።
የሚደርስባቸው ዘላለማዊ ውርደት ፈጽሞ አይረሳም።+
13 ለይሖዋ ዘምሩ! ይሖዋን አወድሱ!
እሱ ድሃውን* ከክፉ አድራጊዎች እጅ ታድጓልና።
14 የተወለድኩበት ቀን የተረገመ ይሁን!
እናቴ እኔን የወለደችበት ቀን አይባረክ!+
15 ለአባቴ “ልጅ፣ አዎ ወንድ ልጅ ተወልዶልሃል!”
የሚል ምሥራች አብስሮ እጅግ ደስ ያሰኘው
ሰው የተረገመ ይሁን።
16 ያ ሰው፣ ይሖዋ ያላንዳች ጸጸት እንደገለበጣቸው ከተሞች ይሁን።
በማለዳ ዋይታ፣ በቀትርም የጦርነት ሁካታ ይስማ።