ኢሳይያስ
3 እነሆ፣ እውነተኛው ጌታ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ
ኢየሩሳሌምና ይሁዳ ማንኛውም ዓይነት ድጋፍና አቅርቦት
ይኸውም የምግብና የውኃ አቅርቦት ሁሉ እንዲቋረጥባቸው ያደርጋል፤+
2 ኃያሉን ሰውና ተዋጊውን፣
ዳኛውንና ነቢዩን፣+ ሟርተኛውንና ሽማግሌውን፣
3 የሃምሳ አለቃውን፣+ ባለሥልጣኑንና አማካሪውን፣
በአስማት የተካነውንና በድግምት የላቀ ችሎታ ያለውን ያስወግዳል።+
4 በእነሱ ላይ ልጆችን መኳንንት አድርጌ እሾማለሁ፤
ያልሰከነ* ሰውም ይገዛቸዋል።
ልጅ በሽማግሌ ላይ ጥቃት ይሰነዝራል፤
ተራው ሰውም የተከበረውን ይዳፈራል።+
6 እያንዳንዱ ሰው በአባቱ ቤት የሚኖረውን ወንድሙን ይዞ
“አንተ ካባ አለህ፤ ስለዚህ በእኛ ላይ አዛዥ ሁን።
ይህን የፍርስራሽ ክምር ግዛ” ይለዋል።
7 እሱ ግን በዚያ ቀን እንዲህ ሲል ይቃወማል፦
“እኔ ቁስላችሁን አላክምም፤*
በቤቴ ምግብም ሆነ ልብስ የለም።
በሕዝቡ ላይ አዛዥ አድርጋችሁ አትሹሙኝ።”
በራሳቸው ላይ ጥፋት ስለሚያመጡ ወዮላቸው!*
11 ለክፉ ሰው ወዮለት!
ጥፋት ይደርስበታል፤
በሌሎች ላይ ሲያደርግ የነበረው በራሱ ላይ ይደርሳልና!
12 የሕዝቤ አሠሪዎች ጨቋኞች ናቸው፤
ሴቶችም ይገዟቸዋል።
ሕዝቤ ሆይ፣ የሚመሯችሁ ሰዎች እንድትባዝኑና
በየትኛው መንገድ እንደምትሄዱ ግራ እንድትጋቡ እያደረጓችሁ ነው።+
13 ይሖዋ ለመክሰስ ተሰይሟል፤
በሕዝቦች ላይ ብያኔውን ለማሰማት ተነስቷል።
14 ይሖዋ የሕዝቡን ሽማግሌዎችና አለቆች ይፋረዳል።
“የወይኑን እርሻ አቃጥላችኋል፤
ከድሃው የዘረፋችሁት ንብረትም በቤታችሁ ይገኛል።+
16 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የጽዮን ሴቶች ልጆች ትዕቢተኛ ስለሆኑ፣
ራሳቸውን ቀና አድርገው* ስለሚራመዱ፣
በዓይናቸው እየተጣቀሱና እየተውረገረጉ በመሄድ
እግራቸው ላይ ያደረጉትን አልቦ ስለሚያቃጭሉ፣
17 ይሖዋ የጽዮንን ሴቶች አናት በቁስል ይመታል፤
ደግሞም ይሖዋ ግንባራቸውን ይገልጣል።+
18 በዚያ ቀን ይሖዋ ጌጦቻቸውን ሁሉ ይነጥቃል፦
አልቦውን፣ የፀጉር ጌጡን፣ የጨረቃ ቅርጽ ያለውን ጌጥ፣+
19 የጆሮ ጉትቻውን፣* አምባሩን፣ መከናነቢያውን፣
20 የራስ መሸፈኛውን፣ የሰንሰለት አልቦውን፣ ጌጠኛውን መቀነት፣*
የሽቶ ዕቃውን፣* ክታቡን፣
21 የጣት ቀለበቱን፣ የአፍንጫ ቀለበቱን፣
22 የክት ልብሱን፣ መደረቢያውን፣ ካባውን፣ የእጅ ቦርሳውን፣
ጥምጥሙንና መከናነቢያውን ይወስድባቸዋል።