ኢዮብ
4 ሰዎች ከሚኖሩበት ክልል ርቆ በሚገኝ ስፍራ፣
ሰዎች ከሚመላለሱበት አካባቢ ርቀው በሚገኙ የተረሱ ቦታዎች ጥልቅ ጉድጓድ ይቆፍራል፤
አንዳንድ ሰዎች በገመድ ወደዚያ ይወርዳሉ፤ ተንጠልጥለውም ይሠራሉ።
5 በምድር ላይ እህል ይበቅላል፤
ከታች ግን ምድር በእሳት የሆነ ያህል ትታመሳለች።*
6 በዚያ በድንጋዮቹ ውስጥ ሰንፔር ይገኛል፤
በአፈሩም ውስጥ ወርቅ አለ።
7 ወደዚያ የሚወስደውን መንገድ የትኛውም አዳኝ አሞራ አያውቀውም፤
የጥቁር ጭልፊትም ዓይን አላየውም።
8 ግርማ የተላበሱ አራዊት አልረገጡትም፤
ብርቱ አንበሳም በዚያ አላደባም።
9 ሰው የባልጩት ድንጋይ በእጁ ይመታል፤
ተራሮችንም ከሥር መሠረታቸው ይገለብጣል።
10 በዓለት ውስጥ የውኃ ቦዮች ይሠራል፤+
ዓይኑም ውድ የሆኑ ነገሮችን ሁሉ ያያል።
11 ወንዞች የሚፈልቁባቸውን ቦታዎች ይገድባል፤
የተሰወረውንም ነገር ወደ ብርሃን ያወጣል።
13 ማንም ሰው ዋጋዋን አይገነዘብም፤+
በሕያዋንም ምድር ልትገኝ አትችልም።
14 ጥልቁ ውኃ ‘እኔ ውስጥ የለችም!’ ይላል፤
ባሕሩም ‘በእኔ ዘንድ አይደለችም!’ ይላል።+
15 እሷን በንጹሕ ወርቅ መግዛት አይቻልም፤
በብርም ልትለወጥ አትችልም።+
16 በኦፊር ወርቅም+ ሆነ
ብርቅ በሆነው ኦኒክስና በሰንፔር ልትገዛ አትችልም።
20 ታዲያ ጥበብ ከየት ትመጣለች?
ማስተዋል የሚገኘውስ ከየት ነው?+
21 ከሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ዓይን ተሰውራለች፤+
በሰማያት ከሚበርሩ ወፎችም ተሸሽጋለች።
22 ጥፋትና ሞት፣
‘ወሬዋን ብቻ በጆሯችን ሰምተናል’ ይላሉ።
23 ወደ እሷ የሚወስደውን መንገድ የሚረዳው አምላክ ነው፤
መኖሪያዋን የሚያውቀው እሱ ብቻ ነው፤+
24 እሱ እስከ ምድር ዳርቻ ይመለከታልና፤
ከሰማያትም በታች ያለውን ሁሉ ያያል።+
ውኃዎችንም በለካ ጊዜ፣+
26 ለዝናብ ሥርዓትን ባወጣ ጊዜ፣+
ነጎድጓድ ለቀላቀለ ጥቁር ደመና መንገድን ባዘጋጀ ጊዜ፣+
27 ያኔ ጥበብን አያት፤ ደግሞም ገለጻት፤
መሠረታት፤ እንዲሁም መረመራት።
28 ሰውንም እንዲህ አለው፦