ዘኁልቁ
7 ሙሴ የማደሪያ ድንኳኑን ተክሎ በጨረሰበት ቀን+ የማደሪያ ድንኳኑን ከቁሳቁሶቹ ሁሉና ከመሠዊያው እንዲሁም ከዕቃዎቹ ሁሉ+ ጋር ቀባው፤+ ደግሞም ቀደሰው። እነዚህን ነገሮች በቀባቸውና በቀደሳቸው+ ጊዜ 2 የእስራኤል አለቆች+ ማለትም የአባቶቻቸው ቤት መሪዎች መባ አቀረቡ። ምዝገባውን በበላይነት ሲቆጣጠሩ የነበሩት እነዚህ የየነገዱ አለቆች 3 ስድስት ባለ ሽፋን ሠረገሎችንና 12 በሬዎችን ይኸውም ሁለት አለቆች አንድ ሠረገላ፣ እያንዳንዳቸውም አንድ አንድ በሬ መባ አድርገው ወደ ይሖዋ ፊት አመጡ፤ እነዚህንም በማደሪያ ድንኳኑ ፊት አቀረቡ። 4 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ 5 “በመገናኛ ድንኳኑ ለሚከናወነው አገልግሎት እንዲውሉ እነዚህን ከእነሱ ተቀበል፤ ለሌዋውያኑም ለእያንዳንዳቸው ለሥራቸው እንደሚያስፈልጋቸው ስጣቸው።”
6 ስለሆነም ሙሴ ሠረገሎቹንና ከብቶቹን ተቀብሎ ለሌዋውያኑ ሰጣቸው። 7 ለጌድሶን ወንዶች ልጆች ለሥራቸው እንደሚያስፈልጋቸው ሁለት ሠረገሎችና አራት በሬዎች ሰጣቸው፤+ 8 ለሜራሪ ወንዶች ልጆች ደግሞ በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታምር አመራር ሥር ሆነው ለሚያከናውኑት ሥራ እንደሚያስፈልጋቸው አራት ሠረገሎችና ስምንት በሬዎች ሰጣቸው።+ 9 ለቀአት ወንዶች ልጆች ግን ምንም አልሰጣቸውም፤ ምክንያቱም ሥራቸው በቅዱሱ ስፍራ ከሚቀርበው አገልግሎት ጋር የተያያዘ+ ሲሆን ቅዱስ የሆኑትን ነገሮች የሚሸከሙት ደግሞ በትከሻቸው ነበር።+
10 አለቆቹም መሠዊያው በተቀባበት ዕለት በምርቃቱ*+ ላይ መባቸውን አቀረቡ። አለቆቹ መባቸውን በመሠዊያው ፊት ባቀረቡ ጊዜ 11 ይሖዋ ሙሴን “በየቀኑ አንድ አንድ አለቃ ለመሠዊያው ምርቃት የሚሆነውን መባውን ያቅርብ” አለው።
12 በመጀመሪያው ቀን መባውን ያቀረበው ከይሁዳ ነገድ የሆነው የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን+ ነበር። 13 መባውም እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል*+ መሠረት 130 ሰቅል* የሚመዝን አንድ የብር ሳህንና 70 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ጎድጓዳ ሳህን ሲሆን እያንዳንዳቸው ለእህል መባ የሚሆን በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፤+ 14 እንዲሁም ዕጣን የተሞላ 10 ሰቅል የሚመዝን አንድ የወርቅ ጽዋ፣ 15 ለሚቃጠል መባ የሚሆን አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና አንድ ዓመት ገደማ የሆነው ተባዕት የበግ ጠቦት፣+ 16 ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ የፍየል ጠቦት+ 17 እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት+ የሚሆኑ ሁለት ከብቶች፣ አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ተባዕት ፍየሎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቀረበ። የአሚናዳብ+ ልጅ ነአሶን ያቀረበው መባ ይህ ነበር።
18 በሁለተኛውም ቀን የይሳኮር አለቃ የሆነው የጹአር ልጅ ናትናኤል+ መባ አቀረበ። 19 መባውም እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል+ መሠረት 130 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ሳህንና 70 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ጎድጓዳ ሳህን ሲሆን እያንዳንዳቸው ለእህል መባ የሚሆን በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፤+ 20 በተጨማሪም ዕጣን የተሞላ 10 ሰቅል የሚመዝን አንድ የወርቅ ጽዋ፣ 21 ለሚቃጠል መባ የሚሆን አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና አንድ ዓመት ገደማ የሆነው ተባዕት የበግ ጠቦት፣+ 22 ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ የፍየል ጠቦት+ 23 እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት+ የሚሆኑ ሁለት ከብቶች፣ አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ተባዕት ፍየሎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቀረበ። የጹአር ልጅ ናትናኤል ያቀረበው መባ ይህ ነበር።
24 በሦስተኛውም ቀን የዛብሎን ልጆች አለቃ የሆነው የሄሎን ልጅ ኤልያብ+ 25 መባ አቀረበ፤ መባውም እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል+ መሠረት 130 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ሳህንና 70 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ጎድጓዳ ሳህን ሲሆን እያንዳንዳቸው ለእህል መባ የሚሆን በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፤+ 26 በተጨማሪም ዕጣን የተሞላ 10 ሰቅል የሚመዝን አንድ የወርቅ ጽዋ፣ 27 ለሚቃጠል መባ የሚሆን አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና አንድ ዓመት ገደማ የሆነው ተባዕት የበግ ጠቦት፣+ 28 ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ የፍየል ጠቦት+ 29 እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት+ የሚሆኑ ሁለት ከብቶች፣ አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ተባዕት ፍየሎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቀረበ። የሄሎን ልጅ ኤልያብ+ ያቀረበው መባ ይህ ነበር።
30 በአራተኛውም ቀን የሮቤል ልጆች አለቃ የሆነው የሸደኡር ልጅ ኤሊጹር+ 31 መባ አቀረበ፤ መባውም እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል+ መሠረት 130 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ሳህንና 70 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ጎድጓዳ ሳህን ሲሆን እያንዳንዳቸው ለእህል መባ የሚሆን በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፤+ 32 በተጨማሪም ዕጣን የተሞላ 10 ሰቅል የሚመዝን አንድ የወርቅ ጽዋ፣ 33 ለሚቃጠል መባ የሚሆን አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና አንድ ዓመት ገደማ የሆነው ተባዕት የበግ ጠቦት፣+ 34 ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ የፍየል ጠቦት+ 35 እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት+ የሚሆኑ ሁለት ከብቶች፣ አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ተባዕት ፍየሎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቀረበ። የሸደኡር ልጅ ኤሊጹር+ ያቀረበው መባ ይህ ነበር።
36 በአምስተኛውም ቀን የስምዖን ልጆች አለቃ የሆነው የጹሪሻዳይ ልጅ ሸሉሚኤል+ 37 መባ አቀረበ፤ መባውም እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል+ መሠረት 130 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ሳህንና 70 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ጎድጓዳ ሳህን ሲሆን እያንዳንዳቸው ለእህል መባ የሚሆን በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፤+ 38 በተጨማሪም ዕጣን የተሞላ 10 ሰቅል የሚመዝን አንድ የወርቅ ጽዋ፣ 39 ለሚቃጠል መባ የሚሆን አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና አንድ ዓመት ገደማ የሆነው ተባዕት የበግ ጠቦት፣+ 40 ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ የፍየል ጠቦት+ 41 እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት+ የሚሆኑ ሁለት ከብቶች፣ አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ተባዕት ፍየሎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቀረበ። የጹሪሻዳይ ልጅ ሸሉሚኤል+ ያቀረበው መባ ይህ ነበር።
42 በስድስተኛውም ቀን የጋድ ልጆች አለቃ የሆነው የደኡዔል ልጅ ኤሊያሳፍ+ 43 መባ አቀረበ፤ መባውም እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል+ መሠረት 130 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ሳህንና 70 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ጎድጓዳ ሳህን ሲሆን እያንዳንዳቸው ለእህል መባ የሚሆን በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፤+ 44 በተጨማሪም ዕጣን የተሞላ 10 ሰቅል የሚመዝን አንድ የወርቅ ጽዋ፣ 45 ለሚቃጠል መባ የሚሆን አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና አንድ ዓመት ገደማ የሆነው ተባዕት የበግ ጠቦት፣+ 46 ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ የፍየል ጠቦት+ 47 እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት+ የሚሆኑ ሁለት ከብቶች፣ አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ተባዕት ፍየሎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቀረበ። የደኡዔል ልጅ ኤሊያሳፍ+ ያቀረበው መባ ይህ ነበር።
48 በሰባተኛውም ቀን የኤፍሬም ልጆች አለቃ የሆነው የአሚሁድ ልጅ ኤሊሻማ+ 49 መባ አቀረበ፤ መባውም እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል+ መሠረት 130 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ሳህንና 70 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ጎድጓዳ ሳህን ሲሆን እያንዳንዳቸው ለእህል መባ የሚሆን በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፤+ 50 በተጨማሪም ዕጣን የተሞላ 10 ሰቅል የሚመዝን አንድ የወርቅ ጽዋ፣ 51 ለሚቃጠል መባ የሚሆን አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና አንድ ዓመት ገደማ የሆነው ተባዕት የበግ ጠቦት፣+ 52 ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ የፍየል ጠቦት+ 53 እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት+ የሚሆኑ ሁለት ከብቶች፣ አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ተባዕት ፍየሎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቀረበ። የአሚሁድ ልጅ ኤሊሻማ+ ያቀረበው መባ ይህ ነበር።
54 በስምንተኛውም ቀን የምናሴ ልጆች አለቃ የሆነው የፐዳጹር ልጅ ገማልያል+ 55 መባ አቀረበ፤ መባውም እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል+ መሠረት 130 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ሳህንና 70 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ጎድጓዳ ሳህን ሲሆን እያንዳንዳቸው ለእህል መባ የሚሆን በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፤+ 56 በተጨማሪም ዕጣን የተሞላ 10 ሰቅል የሚመዝን አንድ የወርቅ ጽዋ፣ 57 ለሚቃጠል መባ የሚሆን አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና አንድ ዓመት ገደማ የሆነው ተባዕት የበግ ጠቦት፣+ 58 ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ የፍየል ጠቦት+ 59 እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት+ የሚሆኑ ሁለት ከብቶች፣ አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ተባዕት ፍየሎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቀረበ። የፐዳጹር ልጅ ገማልያል+ ያቀረበው መባ ይህ ነበር።
60 በዘጠነኛውም ቀን የቢንያም ልጆች አለቃ+ የሆነው የጊድኦኒ ልጅ አቢዳን+ 61 መባ አቀረበ፤ መባውም እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል+ መሠረት 130 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ሳህንና 70 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ጎድጓዳ ሳህን ሲሆን እያንዳንዳቸው ለእህል መባ የሚሆን በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፤+ 62 በተጨማሪም ዕጣን የተሞላ 10 ሰቅል የሚመዝን አንድ የወርቅ ጽዋ፣ 63 ለሚቃጠል መባ የሚሆን አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና አንድ ዓመት ገደማ የሆነው ተባዕት የበግ ጠቦት፣+ 64 ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ የፍየል ጠቦት+ 65 እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት+ የሚሆኑ ሁለት ከብቶች፣ አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ተባዕት ፍየሎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቀረበ። የጊድኦኒ ልጅ አቢዳን+ ያቀረበው መባ ይህ ነበር።
66 በአሥረኛውም ቀን የዳን ልጆች አለቃ የሆነው የአሚሻዳይ ልጅ አሂዔዜር+ 67 መባ አቀረበ፤ መባውም እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል+ መሠረት 130 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ሳህንና 70 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ጎድጓዳ ሳህን ሲሆን እያንዳንዳቸው ለእህል መባ የሚሆን በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፤+ 68 በተጨማሪም ዕጣን የተሞላ 10 ሰቅል የሚመዝን አንድ የወርቅ ጽዋ፣ 69 ለሚቃጠል መባ የሚሆን አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና አንድ ዓመት ገደማ የሆነው ተባዕት የበግ ጠቦት፣+ 70 ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ የፍየል ጠቦት+ 71 እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት+ የሚሆኑ ሁለት ከብቶች፣ አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ተባዕት ፍየሎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቀረበ። የአሚሻዳይ ልጅ አሂዔዜር+ ያቀረበው መባ ይህ ነበር።
72 በ11ኛውም ቀን የአሴር ልጆች አለቃ የሆነው የኦክራን ልጅ ፓጊኤል+ 73 መባ አቀረበ፤ መባውም እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል+ መሠረት 130 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ሳህንና 70 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ጎድጓዳ ሳህን ሲሆን እያንዳንዳቸው ለእህል መባ የሚሆን በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፤+ 74 በተጨማሪም ዕጣን የተሞላ 10 ሰቅል የሚመዝን አንድ የወርቅ ጽዋ፣ 75 ለሚቃጠል መባ የሚሆን አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና አንድ ዓመት ገደማ የሆነው ተባዕት የበግ ጠቦት፣+ 76 ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ የፍየል ጠቦት+ 77 እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት+ የሚሆኑ ሁለት ከብቶች፣ አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ተባዕት ፍየሎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቀረበ። የኦክራን ልጅ ፓጊኤል+ ያቀረበው መባ ይህ ነበር።
78 በ12ኛውም ቀን የንፍታሌም ልጆች አለቃ የሆነው የኤናን ልጅ አሂራ+ 79 መባ አቀረበ፤ መባውም እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል+ መሠረት 130 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ሳህንና 70 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ጎድጓዳ ሳህን ሲሆን እያንዳንዳቸው ለእህል መባ የሚሆን በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፤+ 80 በተጨማሪም ዕጣን የተሞላ 10 ሰቅል የሚመዝን አንድ የወርቅ ጽዋ፣ 81 ለሚቃጠል መባ የሚሆን አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና አንድ ዓመት ገደማ የሆነው ተባዕት የበግ ጠቦት፣+ 82 ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ የፍየል ጠቦት+ 83 እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት+ የሚሆኑ ሁለት ከብቶች፣ አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ተባዕት ፍየሎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቀረበ። የኤናን ልጅ አሂራ+ ያቀረበው መባ ይህ ነበር።
84 የእስራኤል አለቆች መሠዊያው በተቀባበት ጊዜ ያቀረቡት የመሠዊያው ምርቃት መባ+ የሚከተለው ነው፦ 12 የብር ሳህኖች፣ 12 የብር ጎድጓዳ ሳህኖች፣ 12 የወርቅ ጽዋዎች፣+ 85 እያንዳንዱ የብር ሳህን 130 ሰቅል፣ እያንዳንዱም ጎድጓዳ ሳህን 70 ሰቅል ይመዝን ነበር፤ ዕቃዎቹ የተሠሩበት ብር በአጠቃላይ፣ እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል+ መሠረት 2,400 ሰቅል ነበር፤ 86 ዕጣን የተሞሉት 12 የወርቅ ጽዋዎች ሲመዘኑ እያንዳንዱ ጽዋ እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል መሠረት 10 ሰቅል ነበር፤ ጽዋዎቹ የተሠሩበት ወርቅ በአጠቃላይ 120 ሰቅል ነበር። 87 የእህል መባዎቻቸውን ጨምሮ ለሚቃጠል መባ የቀረቡት ከብቶች በአጠቃላይ 12 በሬዎች፣ 12 አውራ በጎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው 12 ተባዕት የበግ ጠቦቶች ነበሩ፤ ለኃጢአት መባ የቀረቡት 12 የፍየል ጠቦቶች ነበሩ፤ 88 ለኅብረት መሥዋዕት የቀረቡት ከብቶች በአጠቃላይ 24 በሬዎች፣ 60 አውራ በጎች፣ 60 ተባዕት ፍየሎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው 60 ተባዕት የበግ ጠቦቶች ነበሩ። መሠዊያው ከተቀባ+ በኋላ የቀረበው የመሠዊያው ምርቃት መባ+ ይህ ነበር።
89 ሙሴ ከአምላክ* ጋር ለመነጋገር ወደ መገናኛ ድንኳኑ በሚገባበት ጊዜ+ ሁሉ ከምሥክሩ ታቦት መክደኛ በላይ ድምፅ ሲያነጋግረው ይሰማ ነበር፤+ እሱም ከሁለቱ ኪሩቦች መካከል ያነጋግረው ነበር።+