ኢያሱ
12 እንግዲህ እስራኤላውያን ድል ያደረጓቸውና ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ የሚገኘውን ምድራቸውን ይኸውም ከአርኖን ሸለቆ*+ አንስቶ እስከ ሄርሞን ተራራ+ ድረስ ያለውን እንዲሁም በስተ ምሥራቅ የሚገኘውን አረባን በሙሉ የወረሱባቸው ነገሥታት እነዚህ ናቸው፦+ 2 በሃሽቦን የሚኖረውና በአርኖን ሸለቆ* ዳርቻ ላይ በምትገኘው በአሮዔር+ ሆኖ የሚገዛው የአሞራውያን ንጉሥ ሲሖን፤+ እሱም በአርኖን ሸለቆ+ መሃል ካለው ስፍራ አንስቶ የአሞናውያን ወሰን እስከሆነው እስከ ያቦቅ ሸለቆ* ድረስ ያለውን የጊልያድን እኩሌታ ይገዛ ነበር። 3 በተጨማሪም ምሥራቃዊ አረባን እስከ ኪኔሬት ባሕር*+ ድረስ፣ በስተ ምሥራቅ በቤትየሺሞት አቅጣጫ እስካለው የአረባ ባሕር ይኸውም እስከ ጨው ባሕር* ድረስና በስተ ደቡብ እስከ ጲስጋ+ ሸንተረር ድረስ ያለውን አካባቢ ይገዛ ነበር።
4 እንዲሁም በአስታሮትና በኤድራይ ይኖር የነበረውንና ከመጨረሻዎቹ የረፋይም+ ወገኖች አንዱ የሆነውን የባሳንን ንጉሥ የኦግን+ ግዛት፤ 5 እሱም የሄርሞንን ተራራ፣ ሳልካን፣ ባሳንን+ በሙሉ እስከ ገሹራውያንና እስከ ማአካታውያን+ ወሰን ድረስ እንዲሁም እስከ ሃሽቦን+ ንጉሥ እስከ ሲሖን ግዛት ድረስ ያለውን የጊልያድን እኩሌታ ይገዛ ነበር።
6 የይሖዋ አገልጋይ ሙሴና እስራኤላውያን እነዚህን ነገሥታት ድል አደረጓቸው፤+ ከዚያም የይሖዋ አገልጋይ ሙሴ ምድራቸውን ለሮቤላውያን፣ ለጋዳውያንና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ርስት አድርጎ ሰጠ።+
7 ኢያሱና እስራኤላውያን ድል ያደረጓቸው ከዮርዳኖስ በስተ ምዕራብ ያሉት የምድሪቱ ነገሥታት እነዚህ ናቸው፤ ግዛታቸውም በሊባኖስ ሸለቆ+ ከሚገኘው ከበዓልጋድ+ አንስቶ ወደ ሴይር+ ሽቅብ እስከሚወጣው እስከ ሃላቅ ተራራ+ ድረስ ነው፤ ከዚያም ኢያሱ ምድራቸውን ለእስራኤል ነገዶች እንደየድርሻቸው ርስት አድርጎ ሰጠ፤+ 8 ይህም በተራራማው አካባቢ፣ በሸፌላ፣ በአረባ፣ በሸንተረሮቹ ላይ፣ በምድረ በዳውና በኔጌብ+ የሚኖሩት የሂታውያን፣ የአሞራውያን፣+ የከነአናውያን፣ የፈሪዛውያን፣ የሂዋውያንና የኢያቡሳውያን+ ምድር ነው፤ ነገሥታቱም የሚከተሉት ናቸው፦
9 የኢያሪኮ ንጉሥ፣+ አንድ፤ በቤቴል አጠገብ የነበረችው የጋይ ንጉሥ፣+ አንድ፤
10 የኢየሩሳሌም ንጉሥ፣ አንድ፤ የኬብሮን ንጉሥ፣+ አንድ፤
11 የያርሙት ንጉሥ፣ አንድ፤ የለኪሶ ንጉሥ፣ አንድ፤
12 የኤግሎን ንጉሥ፣ አንድ፤ የጌዜር ንጉሥ፣+ አንድ፤
13 የደቢር ንጉሥ፣+ አንድ፤ የጌዴር ንጉሥ፣ አንድ፤
14 የሆርማ ንጉሥ፣ አንድ፤ የአራድ ንጉሥ፣ አንድ፤
15 የሊብና ንጉሥ፣+ አንድ፤ የአዱላም ንጉሥ፣ አንድ፤
16 የመቄዳ ንጉሥ፣+ አንድ፤ የቤቴል ንጉሥ፣+ አንድ፤
17 የታጱአ ንጉሥ፣ አንድ፤ የሄፌር ንጉሥ፣ አንድ፤
18 የአፌቅ ንጉሥ፣ አንድ፤ የላሻሮን ንጉሥ፣ አንድ፤
19 የማዶን ንጉሥ፣ አንድ፤ የሃጾር ንጉሥ፣+ አንድ፤
20 የሺምሮንመሮን ንጉሥ፣ አንድ፤ የአክሻፍ ንጉሥ፣ አንድ፤
21 የታአናክ ንጉሥ፣ አንድ፤ የመጊዶ ንጉሥ፣ አንድ፤
22 የቃዴሽ ንጉሥ፣ አንድ፤ በቀርሜሎስ የምትገኘው የዮቅነአም ንጉሥ፣+ አንድ፤
23 በዶር+ ሸንተረሮች የምትገኘው የዶር ንጉሥ፣ አንድ፤ በጊልጋል የምትገኘው የጎይም ንጉሥ፣ አንድ፤
24 የቲርጻ ንጉሥ፣ አንድ፤ በአጠቃላይ 31 ነገሥታት ናቸው።