ኢዮብ
39 “የተራራ ፍየሎች የሚወልዱበትን ጊዜ ታውቃለህ?+
2 የእርግዝናቸው ወራት ምን ያህል እንደሆነ መቁጠር ትችላለህ?
የሚወልዱበትን ጊዜስ ታውቃለህ?
3 ግልገሎቻቸውን ተንበርክከው ይወልዳሉ፤
ከምጣቸውም ይገላገላሉ።
4 ግልገሎቻቸው ይጠነክራሉ፤ በሜዳም ያድጋሉ፤
ይሄዳሉ፤ ወደ እነሱም አይመለሱም።
5 የዱር አህያውን ነፃ የለቀቀው፣+
የዱር አህያውን ከእስራቱ የፈታውስ ማን ነው?
6 በረሃማው ሜዳ ቤቱ፣
ጨዋማውም ምድር መኖሪያው እንዲሆን አደረግኩ።
7 በከተማ ሁካታ ያፌዛል፤
የነጂውንም ጩኸት አይሰማም።
8 መሰማሪያ ለማግኘት በኮረብቶች ላይ ይቅበዘበዛል፤
ማንኛውንም አረንጓዴ ተክል ይፈልጋል።
9 የዱር በሬ አንተን ለማገልገል ፈቃደኛ ነው?+
በጋጣህ ውስጥ ያድራል?
10 የዱር በሬ ትልም እንዲያወጣልህ ልትጠምደው ትችላለህ?
ወይስ እየተከተለህ ሸለቆውን ያርሳል?*
11 በብርቱ ጉልበቱ ትታመናለህ?
ደግሞስ ከባዱን ሥራህን እንዲሠራልህ ታደርጋለህ?
12 እህልህን እንዲሰበስብልህ፣
በአውድማህም ላይ እንዲያከማችልህ በእሱ ትታመናለህ?
14 እንቁላሎቿን መሬት ላይ ትጥላለች፤
በአፈርም ውስጥ ታሞቃቸዋለች።
15 እግር ሊሰብራቸው፣
የዱር አውሬም ሊረግጣቸው እንደሚችል አታስብም።
16 ልጆቿ የራሷ ያልሆኑ ይመስል ትጨክንባቸዋለች፤+
ድካሜ ሁሉ ከንቱ ይሆናል የሚል ስጋት አያድርባትም።
18 ተነስታ ክንፎቿን በምታርገበግብበት ጊዜ ግን፣
በፈረሱና በፈረሰኛው ላይ ትስቃለች።
19 ለፈረስ ጉልበት የምትሰጠው አንተ ነህ?+
አንገቱንስ የሚርገፈገፍ ጋማ ታለብሰዋለህ?
20 እንደ አንበጣ እንዲዘል ልታደርገው ትችላለህ?
የፉርፉርታው ግርማ አስፈሪ ነው።+
22 በፍርሃት ላይ ይስቃል፤ የሚያስፈራውም ነገር የለም።+
ሰይፍ አይቶም ወደኋላ አይልም።
23 ኮሮጆው በጎኑ ይንኳኳል፤
ጭሬውና ጦሩ ያብረቀርቃል።
25 ቀንደ መለከቱ ሲነፋ ‘እሰይ!’ ይላል፤
ጦርነቱን ከሩቅ ያሸታል፤
ደግሞም የጦር አዛዦችን ጩኸትና ቀረርቶውን ይሰማል።+
26 ሲላ ክንፎቹን ወደ ደቡብ ዘርግቶ
ወደ ላይ የሚወነጨፈው በአንተ ማስተዋል ነው?