ኤርምያስ
3 ሰዎች እንዲህ ብለው ይጠይቃሉ፦ “አንድ ሰው ሚስቱን ቢያሰናብታት፣ እሷም ተለይታው ብትሄድና የሌላ ሰው ሚስት ብትሆን፣ ዳግመኛ ወደ እሷ መመለስ ይኖርበታል?”
ይህች ምድር ጨርሶ ተበክላ የለም?+
“አንቺ ከብዙ ወዳጆችሽ ጋር አመነዘርሽ፤+
ታዲያ አሁን ወደ እኔ መመለስ ይገባሻል?” ይላል ይሖዋ።
2 “ዓይንሽን አንስተሽ የተራቆቱትን ኮረብቶች ተመልከቺ።
አንቺ ያልተደፈርሽበት ቦታ ይገኛል?
በምድረ በዳ እንዳለ ዘላን*
አንቺም በመንገዶቹ ዳር ተቀምጠሽ ጠበቅሻቸው።
በዝሙትሽና በክፋትሽ
ምድሪቱን በከልሽ።+
3 ስለዚህ ዝናብ እንዳይዘንብ ተከልክሏል፤+
የኋለኛው ዝናብም አልዘነበም።
4 አሁን ግን ወደ እኔ ተጣርተሽ እንዲህ ትያለሽ፦
‘አባቴ፣ አንተ ከልጅነቴ ጀምሮ ወዳጄ ነህ!+
5 ለዘላለም ቅር ትሰኛለህ?
ወይስ ቂም እንደያዝክ ትኖራለህ?’
አንቺ እንዲህ ትያለሽ፤
ይሁንና የቻልሽውን ያህል ክፉ ነገር መሥራትሽን ቀጥለሻል።”+
6 በንጉሥ ኢዮስያስ+ ዘመን ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “‘ታማኝነቷን ያጎደለችው እስራኤል ያደረገችውን አይተሃል? ከፍ ባለው ተራራ ሁሉ ላይና ቅጠሉ ከተንዠረገገው ዛፍ ሁሉ በታች ለማመንዘር ሄዳለች።+ 7 ይህን ሁሉ ነገር ካደረገች በኋላ እንኳ ወደ እኔ እንድትመለስ መወትወቴን ቀጠልኩ፤+ እሷ ግን አልተመለሰችም፤ ይሁዳም ከሃዲ የሆነችውን እህቷን ተመለከተች።+ 8 ይህን ባየሁ ጊዜ፣ በማመንዘሯ የተነሳ+ ታማኝነቷን ላጎደለችው ለእስራኤል የፍችዋን የምሥክር ወረቀት ሰጥቼ አሰናበትኳት።+ ያም ሆኖ ከሃዲ የሆነችው እህቷ ይሁዳ አልፈራችም፤ እሷም ሄዳ አመነዘረች።+ 9 አመንዝራነቷን አቅልላ ተመለከተችው፤ ምድሪቱን መበከሏን እንዲሁም ከድንጋዮችና ከዛፎች ጋር ማመንዘሯን ቀጠለች።+ 10 ይህም ሁሉ ሆኖ ከሃዲ የሆነችው እህቷ ይሁዳ ለይስሙላ እንጂ በሙሉ ልቧ ወደ እኔ አልተመለሰችም’ ይላል ይሖዋ።”
11 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “ታማኝነቷን ያጎደለችው እስራኤል፣ ከሃዲ ከሆነችው ይሁዳ ይልቅ ጻድቅ ሆና* ተገኝታለች።+ 12 ሂድና እነዚህን ቃላት ወደ ሰሜን+ አውጅ፦
“‘“ከዳተኛይቱ እስራኤል ሆይ፣ ተመለሽ” ይላል ይሖዋ።’+ ‘“እኔ ታማኝ ስለሆንኩ እናንተን በቁጣ አልመለከትም”*+ ይላል ይሖዋ።’ ‘“ለዘላለም ቅር አልሰኝም። 13 ብቻ የሠራሽውን በደል አምነሽ ተቀበይ፤ በአምላክሽ በይሖዋ ላይ ዓምፀሻልና። ቅጠሉ በተንዠረገገ ዛፍ ሁሉ ሥር ከእንግዶች* ጋር አመነዘርሽ፤* ቃሌንም አትታዘዢም” ይላል ይሖዋ።’”
14 “እናንተ ከዳተኛ ልጆች፣ ተመለሱ” ይላል ይሖዋ። “እኔ እውነተኛ ጌታችሁ* ሆኛለሁና፤ ከአንድ ከተማ አንድ፣ ከአንድ ነገድም ሁለት እያደረግኩ እወስዳችኋለሁ፤ ወደ ጽዮንም አመጣችኋለሁ።+ 15 እንደ ልቤ የሆኑ እረኞችም እሰጣችኋለሁ፤+ እነሱም በእውቀትና በጥልቅ ማስተዋል ይመግቧችኋል። 16 በዚያ ዘመን በምድሪቱ ላይ ትበዛላችሁ፤ ፍሬያማም ትሆናላችሁ” ይላል ይሖዋ።+ “ከእንግዲህ ‘የይሖዋ የቃል ኪዳን ታቦት!’ አይሉም፤ ስለ እሱ አያስቡም፤ ጨርሶ አያስታውሱትም ወይም እንዳጎደላቸው ሆኖ አይሰማቸውም፤ ታቦቱም ዳግመኛ አይሠራም። 17 በዚያን ጊዜ ኢየሩሳሌምን የይሖዋ ዙፋን ብለው ይጠሯታል፤+ ብሔራትም ሁሉ በአንድነት የይሖዋን ስም ለማወደስ ወደ ኢየሩሳሌም ይመጣሉ፤+ ከዚያ በኋላ ግትር ሆነው የገዛ ክፉ ልባቸውን አይከተሉም።”
18 “በዚያ ዘመን የይሁዳ ቤትና የእስራኤል ቤት አብረው ይሄዳሉ፤+ በአንድነት ከሰሜን ምድር ተነስተው ለአባቶቻችሁ ርስት አድርጌ ወደሰጠኋት ምድር ይመጣሉ።+ 19 እኔም እንዲህ ብዬ አሰብኩ፦ ‘በወንዶች ልጆች መካከል ባስቀምጥሽ፣ የተወደደችውንም ምድር፣ በብሔራት መካከል የምትገኘውን እጅግ ያማረች ርስት ብሰጥሽ ምንኛ ደስ ባለኝ!’+ በተጨማሪም እናንተ ‘አባቴ!’ ብላችሁ ትጠሩኛላችሁ፤ እኔንም ከመከተል አትመለሱም ብዬ አስቤ ነበር። 20 ‘የእስራኤል ቤት ሆይ፣ እናንተ ግን ባሏን* ክዳ እንደምትሄድ ሚስት በእኔ ላይ ክህደት ፈጽማችኋል’+ ይላል ይሖዋ።”
22 “እናንተ ከዳተኛ ልጆች፣ ተመለሱ።
ከዳተኝነታችሁን እፈውሳለሁ።”+
“እነሆ፣ እኛ ወደ አንተ መጥተናል!
ይሖዋ ሆይ፣ አንተ አምላካችን ነህና።+
23 ኮረብቶቹና በተራሮቹ ላይ የሚሰማው ሁካታ የሐሰት ናቸው።+
በእርግጥ የእስራኤል መዳን በአምላካችን በይሖዋ ነው።+
የአምላካችንን የይሖዋን ድምፅም አልታዘዝንም።”