መዝሙር 32
ጸንታችሁ ቁሙ፣ አትነቃነቁ!
በወረቀት የሚታተመው
1. ብሔራት ፈርተዋል፣ ታውከዋል፤
‘ምን ሊመጣ ነው?’ ብለው ሰግተዋል።
ጠንክረን፣ ጸንተን መቆም አለብን፤
ለአምላክ ታማኝ ሆነን።
(አዝማች)
ከዓለም እድፍ ርቀን፣
ንጹሕ አቋም ጠብቀን፣
እውነትንም ታጥቀን፣ ጸንተን እንቆማለን።
2. ጤናማ አስተሳሰብ ካለን ነው፣
ፈተናዎችን ’ምንቋቋመው።
የአምላክን ቃል ከያዝን አጥብቀን፣
ከለላ ’ናገኛለን።
(አዝማች)
ከዓለም እድፍ ርቀን፣
ንጹሕ አቋም ጠብቀን፣
እውነትንም ታጥቀን፣ ጸንተን እንቆማለን።
3. በሙሉ ልብ እናምልክ ይሖዋን፤
በትጋት እናገልግለው ጌታን።
ምሥራቹን እንስበክ ሁልጊዜ፤
አጭር ነው ያለን ጊዜ።
(አዝማች)
ከዓለም እድፍ ርቀን፣
ንጹሕ አቋም ጠብቀን፣
እውነትንም ታጥቀን፣ ጸንተን እንቆማለን።