ወደ አምላክ ያደርሳል የተባለ የተወሳሰበ መንገድ
“እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ። በኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም” በማለት ኢየሱስ ክርስቶስ ተናገረ። ጨምሮም “እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፤ አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል።”—ዮሐንስ 14:6፤ 16:23
ይሁን እንጂ የሕዝበ ክርስትና ሃይማኖቶች፤ በተለይም የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በሲኦል እሳት፤ በሥላሴና በመንጽሔ መሰረተ ትምህርቶችዋ “መንገዱን” ግራ የሚያጋባ አድርጋዋለች። ኢየሱስ ለኃጢአተኛ የሰው ልጆች በፈቃደኝነት እንደሚሰራ አማላጅ ሳይሆን በእቅፍ ውስጥ እንዳለ ሕጻን ወይም ኃጢአተኞችን ከማዳን ይልቅ በአመዛኙ ሰዎችን መኮነንና መቅጣት እንደሚወድ አስፈሪ ዳኛ ሆኖ ይገለጻል። ታዲያ አንድ ኃጢአተኛ ወደ አምላክ ሊቀርብ የሚችለው እንዴት ነው?
የማርያም ገናናነት (1750) የተሰኘው መጽሐፍ የሚሰጠው ማብራሪያ አለው። መጽሐፉ ኢየሱስን ከሚያቃጥል የፍርድ ፀሐይ ጋር በማመሳሰል የ13ኛው መቶ ዘመን ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ኢኖሰንት ሶስተኛ እንዲህ በማለት እንደተናገሩ ይገልጻል፦ “በኃጢአት ጨለማ ውስጥ ያለ ሁሉ ዐይኑን በጨረቃ ላይ ይጣል፤ ማርያምንም ይለምን።” በኢየሱስ እናት በማርያም የሚሆን ሌላ አማላጅነት ተፈለሰፈ። በእናትነትዋ ተጽእኖ አማካኝነት ከኢየሱስና ከአምላክ ሞገስ ይገኝ ይሆናል ተብሎ ተገመተ። ስለዚህ በ15ኛው መቶ ዘመን ይኖሩ በነበሩት በቄስ ሎውረንስ ጀስቲኒያን አባባል ማርያም “ወደ ገነት መውጫ መሰላል፤ የሰማይ በር፤ ትልቋ የሰውና የአምላክ መካከለኛ” ሆነች።
ከተሰጣት ብዙ ሙገሳ የተነሣ እንደ “ድንግል ማርያም” ብቻ መታየቷ ቀርቶ እጅግ ንጽሕትና ከፍ ያለች ተደርጋ ስለተቆጠረች ወደ እርስዋ በቀጥታ ለመቅረብ እስከማይቻል ድረስ እጅግ ቅድስትና “ቅድስት ንግስት፤ የምህረት እናት” ተባለች። ታዲያ ወደርሷ የሚያቀርብ ሌላ አማላጅ ይገኝ ይሆን? የማርያምስ እናት?
መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ርዕስ ላይ ምንም ሐሳብ ስለማይሰጥ መልሱ ከሌላ ቦታ መፈለግ ነበረበት። የያዕቆብ ፕሮትኤቫንጀልየም የተባለው የአዋልድ መጽሐፍ ስለ ሐና ይናገራል። ሐና ለብዙ ዓመታት መካን ሆና የኖረች የኢያቄም ሚስት ነበረች። በመጨረሻም መልአክ ተገለጠላትና ልጅ እንደምትወልድ አበሰራት። ልክ በተነገራት ጊዜ “ድንግል ማርያምን” ወለደች ይባላል።
በዚህ መንገድ የቅድስት ሐና አምልኮ ተጀመረ። እርሷንም ለማክበር ቅዱሳን ሥፍራዎችና ቤተ መቅደሶች ተሠሩ። በ14ኛው መቶ ዘመን “ቅድስት ሐናን” ማክበር በአውሮፓ በሙሉ የተስፋፋ ሆኖ ነበር።
የተሐድሶ ታሪክ (ዘ ስቶሪ ኦቭ ሪፎርሜሽን) የተሰኘው መጽሐፍ ጉዳዩን በመጥቀስ “ሃይማኖት ምን ያህል በጣም የተወሳሰበ ሆኖአል!” ብሎአል። በመቀጠልም “ሰዎች ስለ ኃጢአታቸው ሐናን ከልጅዋ ከማርያም እንድታማልዳቸውና ማርያም ደግሞ ከልጅዋ ከኢየሱስ አማልዳ ኢየሱስ ከአምላክ ጋር እንዲያስታርቃቸው መለመን ጀመሩ። ጨርሶ የማይታመን ነገር ነበር። ይህ የሰዎች ነፍሳት የተመገቡት በአጉል እምነት ላይ የተመሰረተ እምነት አንዱ ክፍል ብቻ ነበር“ ይላል። ስለዚህ “ባስተላለፋችሁትም ወግ የእግዚአብሔርን ቃል ትሽራላችሁ” የሚሉት የኢየሱስ ቃላት በግልጽ እውነት የሆኑበትን ሌላው ጉዳይ ነው።—ማርቆስ 7:13
[በገጽ 21 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]
The Metropolitan Museum of Art, Bequest of Benjamin Altman, 1913. (14.40.633)