ስለ መሲሑ የተነገሩት ትንቢቶች ኢየሱስ መሲሕ እንደሆነ ያረጋግጣሉ?
መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
አዎ፣ ያረጋግጣሉ። ኢየሱስ ምድር ላይ በኖረበት ወቅት “የዓለም አዳኝ” ስለሚሆነው “መሪ የሆነው መሲሕ” የተነገሩ በርካታ ትንቢቶች እንዲፈጸሙ አድርጓል። (ዳንኤል 9:25፤ 1 ዮሐንስ 4:14) ኢየሱስ፣ ከሞተ በኋላም እንኳ ስለ መሲሑ የተነገሩ ትንቢቶች እንዲፈጸሙ ማድረጉን ቀጥሎ ነበር።—መዝሙር 110:1፤ የሐዋርያት ሥራ 2:34-36
“መሲሕ” የሚለው ቃል ምን ትርጉም አለው?
ማሺያክ (መሲሕ) የሚለው የዕብራይስጥ ቃል እንዲሁም ክሪስቶስ (ክርስቶስ) የሚለው የግሪክኛ ቃል ተመሳሳይ ፍቺ ያላቸው ሲሆን ሁለቱም “የተቀባ” የሚል ትርጉም አላቸው። በመሆኑም “ኢየሱስ ክርስቶስ” ማለት “የተቀባው ኢየሱስ” አሊያም “መሲሑ ኢየሱስ” ማለት ነው።
በጥንት ዘመን አንድ ሰው ለአንድ ልዩ ሥልጣን ሲሾም ብዙውን ጊዜ በራሱ ላይ ዘይት በማፍሰስ ይቀባ ነበር። (ዘሌዋውያን 8:12፤ 1 ሳሙኤል 16:13) ኢየሱስን መሲሕ አድርጎ በመሾም ከፍተኛ ሥልጣን የሰጠው አምላክ ነው። (የሐዋርያት ሥራ 2:36) ሆኖም አምላክ ኢየሱስን የቀባው በዘይት ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ ነው።—ማቴዎስ 3:16
ስለ መሲሑ የተነገሩ ትንቢቶች በተለያዩ ሰዎች ላይ ሊፈጸሙ ይችላሉ?
አይችሉም። የጣት አሻራ አንድን ግለሰብ ብቻ ለይቶ እንደሚያሳውቅ ሁሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተነገሩት ትንቢቶችም ፍጻሜያቸውን የሚያገኙት በአንድ መሲሕ ወይም ክርስቶስ ላይ ብቻ ነው። ያም ቢሆን መጽሐፍ ቅዱስ የሚከተለውን ማስጠንቀቂያ ይዟል፦ “ሐሰተኛ ክርስቶሶችና ሐሰተኛ ነቢያት ይነሳሉ፤ ቢቻላቸው የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክቶችና አስደናቂ ነገሮች ያደርጋሉ።”—ማቴዎስ 24:24
ወደፊት የሚመጣ መሲሕ ሊኖር ይችላል?
በፍጹም። መጽሐፍ ቅዱስ መሲሑ የእስራኤል ንጉሥ የነበረው የዳዊት ዘር እንደሚሆን አስቀድሞ ተናግሯል። (መዝሙር 89:3, 4) ይሁንና የዳዊትን የዘር ሐረግ የያዙ ጥንታዊ የአይሁዳውያን መዝገቦች በአሁኑ ጊዜ አይገኙም፤ ምናልባትም እነዚህ መዝገቦች የጠፉት ሮማውያን በ70 ዓ.ም. ኢየሩሳሌምን ድል ባደረጉበት ወቅት ሊሆን ይችላል።a ከዚያ ጊዜ አንስቶ፣ ማንም ሰው የዳዊት ንጉሣዊ ቤተሰብ አባል መሆኑን በማስረጃ ማረጋገጥ አልቻለም። በኢየሱስ ዘመን ግን እነዚህ መዝገቦች ስለነበሩ ጠላቶቹ እንኳ ኢየሱስ የዳዊት ዘር ስለመሆኑ ጥያቄ አላነሱም።—ማቴዎስ 22:41-46
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ መሲሑ የሚናገሩ ምን ያህል ትንቢቶች ይገኛሉ?
ስለ መሲሑ የሚገልጹ ምን ያህል ትንቢቶች እንደሚገኙ በትክክል መናገር አይቻልም። ስለ መሲሑ የሚናገሩ መሆናቸው በእርግጠኝነት የሚታወቁ ትንቢቶች እንኳ የሚቆጠሩበት መንገድ የተለያየ ነው። ለምሳሌ በኢሳይያስ 53:2-7 ላይ ስለ መሲሑ የሚናገሩ በርካታ ትንቢታዊ መግለጫዎችን እናገኛለን። አንዳንዶች ሙሉውን ሐሳብ እንደ አንድ ትንቢት ይቆጥሩታል፤ ሌሎች ደግሞ እያንዳንዱ መግለጫ እንደ አንድ ትንቢት መቆጠር እንዳለበት ያስባሉ።
በኢየሱስ ላይ ፍጻሜያቸውን ያገኙ ስለ መሲሑ የሚናገሩ አንዳንድ ትንቢቶች
ትንቢት |
የሚገኝበት ጥቅስ |
ፍጻሜ |
---|---|---|
የአብርሃም ዘር ይሆናል |
||
የአብርሃም ልጅ የይስሐቅ ዘር ይሆናል |
||
ከይሁዳ ነገድ ይወለዳል |
||
በንጉሥ ዳዊት የንግሥና መስመር በኩል ይመጣል |
||
ከድንግል ይወለዳል |
||
በቤተልሔም ይወለዳል |
||
አማኑኤል ተብሎ ይጠራልb |
||
በድሃ ቤተሰብ ውስጥ ይወለዳል |
||
ከተወለደ በኋላ ሕፃናት ይገደላሉ |
||
ከግብፅ ይጠራል |
||
የናዝሬት ሰውc ይባላል |
||
ከእሱ አስቀድሞ መልእክተኛ ይመጣል |
||
በ29 ዓ.ም.d መሲሕ ሆኖ ይቀባል |
||
የአምላክ ልጅ እንደሆነ አምላክ ራሱ ይመሠክርለታል |
||
ለአምላክ ቤት ቅንዓት ይኖረዋል |
||
ምሥራቹን ያውጃል |
||
ምሥክርነት በመስጠት በገሊላ ታላቅ ብርሃን ያበራል |
||
እንደ ሙሴ ተአምራትን ይፈጽማል |
||
እንደ ሙሴ የአምላክን ሐሳብ ይናገራል |
||
በርካታ የታመሙ ሰዎችን ይፈውሳል |
||
ወደ ራሱ ትኩረት አይስብም |
||
ለተጎሳቆሉ ሰዎች ርኅራኄ ያሳያል |
||
የአምላክን ፍትሕ ይገልጣል |
||
ድንቅ መካሪ ይሆናል |
||
የይሖዋን ስም ያሳውቃል |
||
በምሳሌ ተጠቅሞ ይናገራል |
||
መሪ ይሆናል |
||
ብዙዎች አያምኑበትም |
||
የሚያሰናክል ድንጋይ ይሆናል |
||
በሰዎች ይናቃል |
||
ያለምክንያት ይጠላል |
||
በአህያ ላይ ተቀምጦ እንደ ድል አድራጊ ወደ ኢየሩሳሌም ይገባል |
||
ልጆች ያመሰግኑታል |
||
በይሖዋ ስም ይመጣል |
||
እምነት የጣለበት ወዳጁ ይከዳዋል |
||
በ30 የብር ሳንቲሞች አልፎ ይሰጣልe |
||
ወዳጆቹ ትተውት ይሄዳሉ |
||
በሐሰት ይመሠከርበታል |
||
በከሳሾቹ ፊት ዝም ይላል |
||
ይተፋበታል |
||
ራሱ ይመታል |
||
ይገረፋል |
||
ሰዎች ሲመቱት ራሱን አይከላከልም |
||
ባለሥልጣናት ያሴሩበታል |
||
እጆቹና እግሮቹ ላይ ምስማር ተመቶ በእንጨት ላይ ይቸነከራል |
||
ሰዎች በልብሱ ላይ ዕጣ ይጣጣላሉ |
||
ከኃጢአተኞች ጋር ይቆጠራል |
||
ይሰደባል እንዲሁም ይፌዝበታል |
||
ለኃጢአተኞች ሲል መከራ ይቀበላል |
||
አምላክ የተወው ይመስላል |
||
ኮምጣጤና ሐሞት እንዲጠጣ ይሰጡታል |
||
ከመሞቱ በፊት ይጠማል |
||
መንፈሱን ለአምላክ ይሰጣል |
||
ይሞታል |
||
ኃጢአትን ለማስወገድ ሲል ሕይወቱን ቤዛ አድርጎ ይሰጣል |
||
አጥንቶቹ አይሰበሩም |
||
ይወጋል |
||
ከሀብታሞች ጋር ይቀበራል |
||
ከሞት ይነሳል |
||
አሳልፎ በሰጠው ሰው ቦታ ሌላ ሰው ይተካል |
||
በአምላክ ቀኝ ይቀመጣል |
a በማክሊንቶክ እና ስትሮንግ የተዘጋጀው ሳይክሎፒዲያ እንዲህ ይላል፦ “የአይሁዳውያን ነገዶችና ቤተሰቦች የትውልድ መዝገብ የጠፋው ኢየሩሳሌም በወደመችበት ጊዜ እንጂ ከዚያ በፊት እንዳልሆነ ጥርጥር የለውም።”
b አማኑኤል የሚለው የዕብራይስጥ ስም “አምላክ ከእኛ ጋር ነው” የሚል ትርጉም ያለው ሲሆን ይህም ኢየሱስ መሲሕ በመሆን የሚጫወተውን ሚና በሚገባ ይገልጻል። ኢየሱስ በምድር ላይ መኖሩና ያከናወናቸው ነገሮች አምላክ ከአገልጋዮቹ ጋር እንደሆነ የሚያረጋግጡ ናቸው።—ሉቃስ 2:27-32፤ 7:12-16
c “የናዝሬት ሰው” የሚለው አጠራር የመጣው “ቀንበጥ” የሚል ትርጉም ካለው ኔሰር የሚል የዕብራይስጥ ቃል ሳይሆን አይቀርም።
d መሲሑ የመጣው በ29 ዓ.ም. እንደሆነ ስለሚጠቁመው የመጽሐፍ ቅዱስ የዘመን አቆጣጠር ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት “የዳንኤል ትንቢት መሲሑ የሚመጣበትን ጊዜ አስቀድሞ የተናገረው እንዴት ነው?” የሚለውን ርዕስ ተመልከት።