ሁለተኛ ሳሙኤል የመጽሐፉ ይዘት 1 ዳዊት፣ ሳኦል መሞቱን ሰማ (1-16) ዳዊት ለሳኦልና ለልጁ ለዮናታን የተቀኘው የሐዘን እንጉርጉሮ (17-27) 2 ዳዊት በይሁዳ ላይ ነገሠ (1-7) ኢያቡስቴ በእስራኤል ላይ ነገሠ (8-11) በዳዊት ቤትና በሳኦል ቤት መካከል ውጊያ ተካሄደ (12-32) 3 የዳዊት ቤት እየበረታ ሄደ (1) የዳዊት ወንዶች ልጆች (2-5) አበኔር ለዳዊት ወገነ (6-21) ኢዮዓብ አበኔርን ገደለው (22-30) ዳዊት ለአበኔር የሐዘን እንጉርጉሮ ተቀኘ (31-39) 4 ኢያቡስቴ ተገደለ (1-8) ዳዊት የኢያቡስቴን ገዳዮች አስገደላቸው (9-12) 5 ዳዊት በመላው እስራኤል ላይ ነገሠ (1-5) ኢየሩሳሌም ተያዘች (6-16) የዳዊት ከተማ ተብላ የምትጠራው ጽዮን (7) ዳዊት ፍልስጤማውያንን ድል አደረገ (17-25) 6 ታቦቱ ወደ ኢየሩሳሌም ተወሰደ (1-23) ዖዛ ታቦቱን በመያዙ ተቀሰፈ (6-8) ሜልኮል ዳዊትን ናቀችው (16, 20-23) 7 ዳዊት ቤተ መቅደሱን እንደማይሠራ ተነገረው (1-7) ለዳዊት የመንግሥት ቃል ኪዳን ተገባለት (8-17) ዳዊት ያቀረበው የምስጋና ጸሎት (18-29) 8 ዳዊት የተቀዳጃቸው ድሎች (1-14) የዳዊት አስተዳደር (15-18) 9 ዳዊት ለሜፊቦስቴ ታማኝ ፍቅር አሳየው (1-13) 10 በአሞናውያንና በሶርያውያን ላይ የተገኘ ድል (1-19) 11 ዳዊት ከቤርሳቤህ ጋር ምንዝር ፈጸመ (1-13) ዳዊት ኦርዮን ለማስገደል ሁኔታውን አመቻቸ (14-25) ዳዊት ቤርሳቤህን አገባ (26, 27) 12 ናታን ዳዊትን ገሠጸው (1-15ሀ) የቤርሳቤህ ልጅ ሞተ (15ለ-23) ቤርሳቤህ ሰለሞንን ወለደች (24, 25) የአሞናውያን ከተማ የሆነችው ራባ ተያዘች (26-31) 13 አምኖን ትዕማርን አስነወራት (1-22) አቢሴሎም አምኖንን ገደለው (23-33) አቢሴሎም ወደ ገሹር ሸሸ (34-39) 14 ኢዮዓብና ተቆአዊቷ ሴት (1-17) ዳዊት ተቆአዊቷን ሴት የላካት ኢዮዓብ መሆኑን ደረሰበት (18-20) አቢሴሎም ወደ ቤቱ እንዲመለስ ተፈቀደለት (21-33) 15 የአቢሴሎም ሴራና ዓመፅ (1-12) ዳዊት ከኢየሩሳሌም ሸሸ (13-30) አኪጦፌል ከአቢሴሎም ጋር አበረ (31) ኩሲ የአኪጦፌልን ምክር ውድቅ እንዲያደርግ ተላከ (32-37) 16 ሲባ የሜፊቦስቴን ስም አጠፋ (1-4) ሺምአይ ዳዊትን ረገመው (5-14) አቢሴሎም ኩሲን ተቀበለው (15-19) የአኪጦፌል ምክር (20-23) 17 ኩሲ የአኪጦፌልን ምክር ውድቅ አደረገ (1-14) ዳዊት እንዲጠነቀቅ ተነገረው፤ ከአቢሴሎም አመለጠ (15-29) ቤርዜሊና አብረውት ያሉት ሰዎች ለንጉሡ ስንቅ አቀበሉ (27-29) 18 አቢሴሎም ለሽንፈትና ለሞት ተዳረገ (1-18) ዳዊት፣ አቢሴሎም መሞቱ ተነገረው (19-33) 19 ዳዊት ለአቢሴሎም አለቀሰ (1-4) ኢዮዓብ ዳዊትን ገሠጸው (5-8ሀ) ዳዊት ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ (8ለ-15) ሺምአይ ይቅርታ ጠየቀ (16-23) ሜፊቦስቴ በዳዊት ላይ የፈጸመው በደል እንደሌለ ተረጋገጠ (24-30) ቤርዜሊ የንጉሡን አክብሮት አተረፈ (31-40) በእስራኤልና በይሁዳ ሰዎች መካከል ውዝግብ ተፈጠረ (41-43) 20 ሳባ ዓመፀ፤ ኢዮዓብ አሜሳይን ገደለው (1-13) ሳባን አሳደው ደረሱበት፤ እንዲሁም ተገደለ (14-22) የዳዊት አስተዳደር (23-26) 21 ገባኦናውያን የሳኦልን ቤት ተበቀሉ (1-14) ከፍልስጤማውያን ጋር የተደረጉ ጦርነቶች (15-22) 22 ዳዊት፣ ይሖዋ ከጠላቶቹ ስለታደገው ውዳሴ አቀረበ (1-51) “ይሖዋ ቋጥኜ፣ ምሽጌና ታዳጊዬ ነው” (2) ይሖዋ ታማኝ ለሆነ ሰው ታማኝ ይሆናል (26) 23 የዳዊት የመጨረሻ ቃላት (1-7) የዳዊት ኃያላን ተዋጊዎች የፈጸሙት ጀብዱ (8-39) 24 ዳዊት ሕዝቡን በመቁጠር የፈጸመው ኃጢአት (1-14) ይሖዋ በላከው ቸነፈር 70,000 ሰዎች ሞቱ (15-17) ዳዊት መሠዊያ ሠራ (18-25) ‘ምንም ያልከፈልኩበትን ነገር መሥዋዕት አድርጌ አላቀርብም’ (24)