በመንፈስ መሪነት የተጻፉ መጻሕፍት እና የኋላ ታሪካቸው ጥናት
ጥናት ቁጥር 3—በጊዜ ሂደት ውስጥ የተለያዩ ክስተቶች የተፈጸሙበትን ዘመን ማስላት
የመጽሐፍ ቅዱስ የዘመናት አቆጣጠር እንዲሁም በዕብራይስጥና በግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ ጎላ ብለው የሚታዩ ክንውኖች ስለተፈጸሙባቸው ዓመታት አቆጣጠር ማብራሪያ
የይሖዋ መልአክ ስለ ‘ሰሜኑ ንጉሥ’ እና ስለ ‘ደቡቡ ንጉሥ’ የሚገልጸውን ራእይ ለዳንኤል ባሳየው ጊዜ ‘የተወሰነው ጊዜ’ የሚለውን ሐረግ በተደጋጋሚ ተጠቅሟል። (ዳን. 11:6, 27, 29, 35) ይሖዋ ጊዜ አክባሪ እንደሆነና ዓላማውን ልክ በጊዜው የሚፈጽም አምላክ እንደሆነ የሚያመለክቱ ሌሎች በርካታ ጥቅሶችም አሉ። (ሉቃስ 21:24፤ 1 ተሰ. 5:1, 2) በቃሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አስፈላጊ የሆኑ ክንውኖች የተፈጸሙባቸውን ጊዜያት ለይተን እንድናውቅ የሚያስችሉ “ጠቋሚዎችን” ሰጥቶናል። የመጽሐፍ ቅዱስን የዘመናት አቆጣጠር በመረዳት ረገድ ብዙ እድገት ተደርጓል። የከርሰ ምድር ጥናት ተመራማሪዎችና ሌሎች ሊቃውንት፣ ባደረጓቸው ምርምሮች ለተለያዩ ችግሮች መልስ በማግኘታቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተመዝግበው የሚገኙ ቁልፍ ክንውኖች የተፈጸሙባቸውን ዓመታት ለይተን እንድናውቅ አስችለውናል።—ምሳሌ 4:18
2 ኦርዲናል እና ካርዲናል ቁጥሮች፦ ከዚህ በፊት በነበረው ጥናት (አንቀጽ 24 እና 25 ላይ) ኦርዲናል (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወዘተ) በሚባሉት ቁጥሮችና ካርዲናል ወይም ሙሉ ቁጥር (አንድ፣ ሁለት ወዘተ) በሚባሉት ቁጥሮች መካከል ልዩነት እንዳለ ተምረናል። የመጽሐፍ ቅዱስ ዘመናትን ከጊዜያችን የዘመን አቆጣጠር ጋር አስማምተን በምንለካበት ጊዜ ይህን መዘንጋት አይገባንም። ለምሳሌ ያህል “የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን በግዞት በተወሰደ በ37ኛው ዓመት” በሚልበት ጊዜ “37ኛው” የሚለው ቁጥር ኦርዲናል ነው። የሚያመለክተውም 36 ሙሉ ዓመታትንና ከ36ኛው ዓመት በኋላ ያለፉትን ጥቂት ቀናት፣ ሳምንታት ወይም ወራት ነው።—ኤር. 52:31
3 የግዛት ዘመንና የሽግግር ዘመን፦ የይሁዳና የእስራኤል መንግሥታት እንዲሁም የባቢሎንና የፋርስ መንግሥታት ታሪካቸውን የሚዘግቡ መዛግብት የነበሯቸው ሲሆን መጽሐፍ ቅዱስም እነዚህን መዛግብት እንደ ዋቢ አድርጎ ይጠቅሳል። እነዚህ አራት መንግሥታት ነገሥታቶቻቸው የገዙበትን ትክክለኛ የግዛት ዘመን በጥንቃቄ ያሰፈሩ ሲሆን እነሱ ከተጠቀሙበት የአቆጣጠር ዘዴ ጋር የሚመሳሰል አቆጣጠርም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይገኛል። አብዛኛውን ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ መረጃው የተገኘበትን ሰነድ ይገልጻል። ለምሳሌ “በሰለሞን ታሪክ መጽሐፍ” ይላል። (1 ነገ. 11:41) አንድ ንጉሥ ዘውድ ከጫነበት ጊዜ አንስቶ ንጉሥ እንደሆነ ተደርጎ ቢቆጠርም የንግሥና ዘመኑ የሚቆጠረው ግን ከኒሳን እስከ ኒሳን ወይም ከጸደይ እስከ ጸደይ ነው። አንድ አዲስ ንጉሥ ዙፋን ላይ በሚቀመጥበት ጊዜ እስከ መጪው ጸደይ ወይም ኒሳን ያሉት ወራት የሽግግር ዘመን ተብለው የሚጠሩ ሲሆን እነዚህ ጊዜያት ከቀደመው ንጉሥ የግዛት ዘመን ጋር ይደመራሉ። የራሱ የንግሥና ዘመን ግን የሚቆጠረው ከመጪው ኒሳን 1 ጀምሮ ነው።
4 ለምሳሌ ያህል ሰለሞን መግዛት የጀመረው ዳዊት በሕይወት እያለ ከኒሳን 1037 ዓ.ዓ. ቀደም ብሎ ይመስላል። ከዚያ ብዙም ሳይቆይ ዳዊት ሞተ። (1 ነገ. 1:39, 40፤ 2:10) ይሁን እንጂ የዳዊት የግዛት ዘመን እስከ 1037 ዓ.ዓ. የጸደይ ወራት ድረስ የቀጠለ ሲሆን የ40 ዓመት የግዛት ዘመኑ ያበቃው በዚህ ጊዜ ነበር። ሰለሞን ከነገሠበት ጊዜ አንስቶ እስከ 1037 ዓ.ዓ. የጸደይ ወራት ድረስ ያለው ከፊል ዓመት የሰለሞን የሽግግር ዘመን ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ገና የአባቱን የግዛት ዘመን እየጨረሰ ስለሆነ ይህ ጊዜ ከራሱ የግዛት ዘመን ጋር አይቆጠርም። ስለዚህ የሰለሞን ሙሉ የግዛት ዘመን የጀመረው በ1037 ዓ.ዓ. ኒሳን ወር ነው። (1 ነገ. 2:12) ከዚያ በኋላ ሰለሞን በንግሥና የቆየበት ዘመን 40 ዓመት እንደሆነ ተገልጿል። (1 ነገ. 11:42) የንግሥና ዘመንንና የሽግግር ዘመንን በዚህ መንገድ ለይተን ማወቅ ከቻልን የመጽሐፍ ቅዱስን የዘመናት አቆጣጠር በትክክል ማስላት እንችላለን።a
አዳም የተፈጠረበትን ጊዜ ወደኋላ ማስላት
5 ከጠቋሚው ዓመት መነሳት፦ አዳም የተፈጠረበትን ጊዜ ወደኋላ ለማስላት አንድ ጠቋሚ ዓመት ማግኘት ይኖርብናል። ለዚህም ቂሮስ የባቢሎንን ሥርወ መንግሥት የገለበጠበት ጊዜ ይኸውም 539 ዓ.ዓ. እንደ ጠቋሚ ዓመት ሆኖ ሊያገለግለን ይችላል።b ቂሮስ አይሁዳውያን ነፃ መውጣታቸውን ያወጀው በነገሠበት በመጀመሪያው ዓመት ማለትም ከ537 ዓ.ዓ. የጸደይ ወራት ቀደም ብሎ ነው። ዕዝራ 3:1 የእስራኤል ልጆች በመስከረምና በጥቅምት መካከል ባለው ጊዜ ውስጥ በሚውለው ቲሽሪ በሚባለው በሰባተኛው ወር ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው እንደነበረ ይገልጻል። ስለዚህ የይሖዋ አምልኮ በኢየሩሳሌም ዳግመኛ የተቋቋመው በ537 ዓ.ዓ. ባለው የበልግ ወቅት ነው።
6 በ537 ዓ.ዓ. የይሖዋ አምልኮ ተመልሶ የተቋቋመባቸው እነዚህ የበልግ ወራት የአንድ ትንቢታዊ ዘመን ማለቂያ ናቸው። የየትኛው ዘመን? ተስፋይቱ ምድር ባድማ ሆና የምትቆይበትና ይሖዋ “በባቢሎን የምትኖሩበት 70 ዓመት ሲፈጸም ትኩረቴን ወደ እናንተ አዞራለሁ፤ ወደዚህም ስፍራ መልሼ በማምጣት፣ የገባሁትን ቃል እፈጽማለሁ” ሲል የተናገረለት ዘመን ነው። (ኤር. 25:11, 12፤ 29:10) ይህን ትንቢት በሚገባ የሚያውቀው ዳንኤል ‘70ው ዓመት’ ሲፈጸም ከጊዜው ጋር የሚስማማ ነገር አድርጓል። (ዳን. 9:1-3) በ537 ዓ.ዓ. የበልግ ወራት ያለቀው ይህ “70 ዓመት” የጀመረው በ607 ዓ.ዓ. የበልግ ወራት ነበር ማለት ነው። የተፈጸሙት ሁኔታዎችም ይህን ያረጋግጣሉ። ኤርምያስ ምዕራፍ 52 ኢየሩሳሌም የተከበበችበትን እንዲሁም በ607 ዓ.ዓ. ባቢሎናውያን ሰብረው የገቡበትንና ንጉሥ ሴዴቅያስ የተያዘበትን ሁኔታ ይገልጻል። ከዚያም ኤርምያስ 52 ቁጥር 12 “በአምስተኛው ወር፣ ከወሩም በአሥረኛው ቀን” ማለትም በአብ ወር አሥረኛ ቀን (በሐምሌና በነሐሴ መካከል ይውላል) ባቢሎናውያን ቤተ መቅደሱንና ከተማይቱን እንዳቃጠሉ ይናገራል። ይሁን እንጂ ‘70ው ዓመት’ የጀመረው በዚህ ጊዜ አልነበረም። የባቢሎን ንጉሥ ጎዶልያስን በቀሩት የአይሁዳውያን መንደሮች ላይ ሾሞት ስለነበረ የአይሁዳውያን ግዛት ፈጽሞ አልጠፋም ነበር። ‘በሰባተኛው ወር’ ጎዶልያስና አንዳንድ ሰዎች ስለተገደሉ የቀሩት አይሁዳውያን ፈርተው ወደ ግብፅ ሸሹ። ስለዚህ ምድሪቱ “70 ዓመት እስኪፈጸም ድረስ” ሙሉ በሙሉ ባድማ የሆነችበት ዘመን የጀመረው በጥቅምት ወር 607 ዓ.ዓ. በመጀመሪያው ቀን ነው።—2 ነገ. 25:22–26፤ 2 ዜና 36:20, 21
7 ከ607 እስከ 997 ዓ.ዓ.፦ ኢየሩሳሌም ከጠፋችበት ጊዜ አንስቶ ሰለሞን ሞቶ ግዛቱ እስከተከፈለበት ዓመት ድረስ ወደኋላ ስንቆጥር ብዙ ችግሮች ያጋጥሙናል። ይሁን እንጂ በአንደኛና በሁለተኛ ነገሥት ላይ ተመዝግቦ የሚገኘውን የእስራኤልና የይሁዳ ታሪክ ስናነጻጽር ይህ ዘመን የ390 ዓመት ርዝመት እንዳለው እንረዳለን። ይህ ቁጥር ትክክል መሆኑን ሕዝቅኤል 4:1-13 በማያሻማ ሁኔታ ያረጋግጣል። ይህ ትንቢት የሚያመለክተው ኢየሩሳሌም በአሕዛብ የምትወረርበትንና ነዋሪዎቿም ወደ ግዞት የሚወሰዱበትን ጊዜ ሲሆን ይህ ደግሞ የተፈጸመው በ607 ዓ.ዓ. ነው። ስለዚህ ስለ ይሁዳ የተነገረው 40 ዓመት ያለቀው ኢየሩሳሌም ስትጠፋ ነው። ይሁን እንጂ ስለ እስራኤል የተነገረው 390 ዓመት ያለቀው ሰማርያ በጠፋችበት ጊዜ አልነበረም። ምክንያቱም ሕዝቅኤል ትንቢቱን በተናገረበት ጊዜ ሰማርያ ከጠፋች ብዙ ዓመት ሆኗታል። ትንቢቱም በግልጽ የሚናገረው ስለ ኢየሩሳሌም መከበብና መጥፋት ነው። ስለዚህ ‘የእስራኤል ቤት በደል’ ያበቃው በ607 ዓ.ዓ. ነው። ከዚህ ዓመት ተነስተን ወደኋላ ስንቆጥር 390ው ዓመት የጀመረው በ997 ዓ.ዓ. እንደሆነ እንመለከታለን። በዚህ ዓመት ኢዮርብዓም (ሰለሞን ከሞተ በኋላ) ከዳዊት ቤት ተገንጥሎ “እስራኤላውያን ይሖዋን ከመከተል ዞር እንዲሉና ከባድ ኃጢአት እንዲሠሩ አደረገ።”—2 ነገ. 17:21
8 ከ997 እስከ 1513 ዓ.ዓ.፦ የሰለሞን ድፍን 40 ዓመት የግዛት ዘመን ያለቀው በ997 ዓ.ዓ. የጸደይ ወራት በመሆኑ የግዛቱ ዘመን የጀመረው በ1037 ዓ.ዓ. የጸደይ ወራት መሆን ይኖርበታል። (1 ነገ. 11:42) በ1 ነገሥት 6:1 ላይ የሚገኘው የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ ሰለሞን የይሖዋን ቤት በኢየሩሳሌም መሥራት የጀመረው በአራተኛው የግዛት ዘመኑ በሁለተኛው ወር እንደሆነ ይናገራል። ይህም ማለት ከግዛት ዘመኑ ሦስት ሙሉ ዓመትና አንድ ሙሉ ወር አልፈዋል ማለት ነው። ይህም የቤተ መቅደሱ ግንባታ የጀመረበትን ጊዜ ወደ ሚያዝያና ግንቦት 1034 ዓ.ዓ. ያመጣዋል። በተጨማሪም ‘እስራኤላውያን ከግብፅ ምድር ከወጡ 480ኛው ዓመት’ የሚሆነው በዚህ ወቅት እንደሆነ ይኸው ጥቅስ ያመለክታል። አራት መቶ ሰማንያኛ ዓመት ኦርዲናል ቁጥር በመሆኑ 479 ሙሉ ዓመታት አልፈዋል ማለት ነው። ስለዚህ 479ን 1034 ላይ ስንደምር እስራኤላውያን ከግብፅ የወጡበት ዓመት ማለትም 1513 ዓ.ዓ. ላይ ያደርሰናል። ጥናት ቁጥር 2 አንቀጽ 19 እንደሚገልጸው ከ1513 ዓ.ዓ. ጀምሮ ለእስራኤላውያን ‘የዓመቱ ወሮች መጀመሪያ’ የሚሆነው የአቢብ (ኒሳን) ወር ነው፤ (ዘፀ. 12:2) ከዚያ በፊት የዓመቱ የመጀመሪያ ወር የነበረው የበልግ ወቅት የሆነው ቲሽሪ ነበር። በ1957 የታተመው ዘ ኒው ሻፍ-ሄርዞግ ኢንሳይክሎፒዲያ ኦቭ ሪሊጅየስ ኖውሌጅ ጥራዝ 12 ገጽ 474 “የነገሥታቱ የግዛት ዘመን አቆጣጠር በጸደይ በሚጀምረው ዓመት ላይ የተመሠረተ ሲሆን ከባቢሎናውያኑ አቆጣጠር ጋር አንድ ዓይነት ነው” የሚል አስተያየት ሰጥቷል። ከበልግ የዓመት መጀመሪያ ወደ ጸደይ የዓመት መጀመሪያ መሸጋገር አስፈላጊ የሚሆንበት የመጽሐፍ ቅዱስ የዘመናት ስሌት በሚኖርበት ጊዜ ሁሉ የስድስት ወር ጭማሪ ወይም ቅናሽ ማድረግ አስፈላጊ ይሆናል።
9 ከ1513 እስከ 1943 ዓ.ዓ.፦ ሙሴ በዘፀአት 12:40, 41 ላይ “በግብፅ የኖሩት እስራኤላውያን የኖሩበት ዘመን 430 ዓመት ነበር” ሲል መዝግቧል። ይህ አነጋገር ራሱ በግብፅ የኖሩበት ዘመን በሙሉ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት አለመሆኑን ያመለክታል። ይህ ዘመን የጀመረው አብርሃም ወደ ከነዓን ሲጓዝ ኤፍራጥስን በተሻገረበትና ይሖዋ ከአብርሃም ጋር የገባው ቃል ኪዳን ሥራ ላይ በዋለበት ጊዜ ነው። የመጀመሪያውን 215 ዓመት የኖሩት በከነዓን ሲሆን ያንኑ ያህል ዓመት በግብፅ ከኖሩ በኋላ በ1513 ዓ.ዓ. ከግብፅ ተገዢነትና ጥገኝነት ሙሉ በሙሉ ነፃ ወጡ።c ባለማጣቀሻው አዲስ ዓለም ትርጉም (እንግሊዝኛ) በዘፀአት 12:40 የግርጌ ማስታወሻው ላይ ከማሶሬቲክ ቅጂዎች ቀዳሚነት ባለው የዕብራይስጥ ቅጂ ላይ የተመሠረተው የግሪክኛው ሴፕቱጀንት ትርጉም “በግብፅ” ከሚለው ቃል ቀጥሎ “እና በከነዓን ምድር” የሚሉትን ቃላት እንደሚጨምር ያመለክታል። የሳምራውያን ፔንታተችም ተመሳሳይ ጭማሪ አስገብቷል። አራት መቶ ሠላሳዎቹን ዓመታት የሚጠቅሰው ገላትያ 3:17ም ይህ ዘመን የሚጀምረው አብርሃም ወደ ከነዓን ሲጓዝ ኤፍራጥስን በተሻገረበትና የአብርሃም ቃል ኪዳን በጸደቀበት ጊዜ እንደሆነ ያረጋግጣል። ስለዚህ ይህ የሆነው አብርሃም 75 ዓመት በሆነው ጊዜ ይኸውም በ1943 ዓ.ዓ. ነው።—ዘፍ. 12:4
10 ይህን አቆጣጠር የሚያጠናክር ሌላም ማስረጃ አለ። የሐዋርያት ሥራ 7:6 የአብርሃም ዘር ለአራት መቶ ዓመት መከራ እንደተቀበለ ይናገራል። ይሖዋ ግብፃውያን ያደርሱባቸው የነበረውን መከራ ያስወገደው በ1513 ዓ.ዓ. በመሆኑ የመከራው ዘመን የጀመረው በ1913 ዓ.ዓ. መሆን ይኖርበታል። ይህ ዓመት ይስሐቅ ከተወለደ ከአምስት ዓመት በኋላ ይኸውም ጡት በጣለ ጊዜ እስማኤል ‘ባሾፈበት’ ዓመት ላይ ይውላል።—ዘፍ. 15:13፤ 21:8, 9
11 ከ1943 እስከ 2370 ዓ.ዓ.፦ አብርሃም በ1943 ዓ.ዓ. ከነዓን ሲገባ ዕድሜው 75 ዓመት እንደነበረ ተመልክተናል። ከዚህ ተነስተን እስከ ኖኅ ዘመን ያለውን ጊዜ መቁጠር እንችላለን። ከዘፍጥረት 11:10 እስከ 12:4 የተሰጡንን ዓመታት በመጠቀም ይህንን ማድረግ ይቻላል። አራት መቶ ሃያ ሰባት ዓመታት የሚሰጠን ይህ አቆጣጠር እንደሚከተለው ሰፍሯል፦
ከጥፋት ውኃ መጀመሪያ
እስከ አርፋክስድ ልደት 2 ዓመት
ከዚያም እስከ ሴሎም ልደት 35 ዓመት
እስከ ዔቦር ልደት 30 ዓመት
እስከ ፋሌቅ ልደት 34 ዓመት
እስከ ረኡ ልደት 30 ዓመት
እስከ ሴሮህ ልደት 32 ዓመት
እስከ ናኮር ልደት 30 ዓመት
እስከ ታራ ልደት 29 ዓመት
አብርሃም የ75 ዓመት ሰው እስከሆነበት
እስከ ታራ ሞት ድረስ 205 ዓመት
ጠቅላላ ድምር 427 ዓመት
በ1943 ዓ.ዓ. ላይ 427 ዓመት ስንደምር 2370 ዓ.ዓ. ላይ ያደርሰናል። ስለዚህ የኖኅ የጥፋት ውኃ የጀመረው በ2370 ዓ.ዓ. እንደሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ የጊዜ ሰሌዳ ያሳያል።
12 ከ2370 ዓ.ዓ. እስከ 4026 ዓ.ዓ.፦ አሁንም በጊዜ ሂደት ወደኋላ መለስ ብለን ስንቆጥር መጽሐፍ ቅዱስ ከኖኅ የጥፋት ውኃ እስከ አዳም መፈጠር ያለው ጊዜ ምን ያህል እንደሆነ ይነግረናል። ይህን ማወቅ የምንችለው በዘፍጥረት 5:3-29 እና በዘፍጥረት 7:6, 11 ላይ ሰፍረው ከምናገኛቸው መረጃዎች ነው። የጊዜ አቆጣጠሩ እንደሚከተለው ቀርቧል፦
ከአዳም መፈጠር
እስከ ሴት ልደት 130 ዓመት
እስከ ሄኖስ ልደት 105 ዓመት
እስከ ቃይናን ልደት 90 ዓመት
እስከ መላልኤል ልደት 70 ዓመት
እስከ ያሬድ ልደት 65 ዓመት
እስከ ሄኖክ ልደት 162 ዓመት
እስከ ማቱሳላ ልደት 65 ዓመት
እስከ ላሜህ ልደት 187 ዓመት
እስከ ኖኅ ልደት 182 ዓመት
እስከ ኖኅ የጥፋት ውኃ 600 ዓመት
ጠቅላላ ድምር 1,656 ዓመት
ቀደም ሲል በደረስንበት 2370 ዓ.ዓ. ላይ 1,656 ዓመት ስንደምር አዳም ወደተፈጠረበት 4026 ዓ.ዓ. ያደርሰናል፤ የጥንት የዘመን አቆጣጠሮች አዲስ ዓመት የሚጀምረው በበልግ ወራት በመሆኑ ምናልባትም ይህ ወቅት የበልግ ወራት ይሆናል።
13 ታዲያ ይህ ለእኛ ዘመን ምን ትርጉም ይኖረዋል? ቅዱስ ጽሑፉ ሁሉ በአምላክ መንፈስ የተጻፈና ጠቃሚ ነው (እንግሊዝኛ) የተባለው መጽሐፍ በ1963 በወጣው በመጀመሪያ እትሙ ላይ እንዲህ ብሎ ነበር፦ “ታዲያ በ1963 ይሖዋ ከሥራው ሁሉ ካረፈ 5,988 ዓመት ሆኖታል ማለት ነውን? (ዘፍ. 2:3) እንደዚያ ማለት አይደለም። ምክንያቱም አዳም የተፈጠረበትና የይሖዋ የእረፍት ቀን የጀመረበት ጊዜ አንድ አይደለም። አዳም ከተፈጠረ በኋላና በዚያው በስድስተኛው የፍጥረት ቀን ይሖዋ ሌሎች ተጨማሪ እንስሳትንና አእዋፍን የፈጠረ ይመስላል። በተጨማሪም አዳም ለእንስሳቱ ስም እንዲያወጣ አዝዞት ነበር። ይህ ደግሞ የተወሰነ ጊዜ መውሰዱ አይቀርም። ከዚያም ሔዋንን መፍጠር ጀመረ። (ዘፍ. 2:18-22) ‘ከሰባተኛው ቀን’ መጀመሪያ እስከ [1963] ያለፈውን ጊዜ ለማወቅ ከ5,988 ላይ አዳም በተፈጠረበት ጊዜና ‘በስድስተኛው ቀን’ መጨረሻ መካከል ያለፈውን ጊዜ መቀነስ ያስፈልጋል። የመጽሐፍ ቅዱስን የዘመን አቆጣጠር መሠረት በማድረግ ገና ወደፊት የሚመጡ ዘመናትን ለመገመት መሞከር ምንም ፋይዳ የለውም።—ማቴ. 24:36”d
14 የሰው ልጅ በዚህች ምድር ላይ መኖር ከጀመረ በመቶ ሺህ እንዲያውም በሚሊዮን የሚቆጠር ዓመት አልፎታል የሚለው የሳይንስ ሊቃውንት አባባልስ? ይህ አባባል በጽሑፍ እንደሰፈሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥንታዊ ክንውኖች ማረጋገጫ ሊቀርብለት አይችልም። “ጥንታዊው ሰው” መኖር የጀመረበት ዓመት እየተባለ የሚጠቀሰው የተጋነነ አኃዝ በማስረጃ ሊረጋገጥ የማይችልና በግምት ላይ ብቻ የተመሠረተ ነው። እንደ እውነቱ ከሆነ አስተማማኝ ማስረጃ የሚገኝለት ዓለማዊ ታሪክና የዘመን አቆጣጠር ከጥቂት ሺህ ዓመታት አያልፍም። በምድር ላይ የዓለቶችን ድርብርቦሽና የቅሪተ አካላትን ክምችት የሚያፋልሱ እንደ ኖኅ የጥፋት ውኃ ያሉ በርካታ ለውጦች ስለተካሄዱ ከጥፋት ውኃ በፊት የተከናወኑ ሁኔታዎች የተፈጸሙባቸውን ዓመታት በሳይንሳዊ መንገድ ለማወቅ መሞከር ከግምት ያለፈ አይሆንም።e መጽሐፍ ቅዱስ እርስ በርሳቸው ከሚጋጩት የሰዎች መላ ምቶችና ንድፈ ሐሳቦች በተለየ ሁኔታ ስለ አምላክ ምርጥ ሕዝብ በሚተርከው በጥንቃቄ የተመዘገበ ታሪክ አማካኝነት ትክክለኛውን የሰው ልጅ ታሪክ አጀማመር ምክንያታዊ በሆነና እርስ በርሱ በሚስማማ መንገድ ይገልጸዋል።
15 መጽሐፍ ቅዱስንና ታላቁ ጊዜ ጠባቂ ይሖዋ አምላክ የሠራቸውን ሥራዎች ማጥናታችንና ባጠናነው ነገር ላይ ማሰላሰላችን ራሳችንን ዝቅ አድርገን እንድንመለከት ሊያደርገን ይገባል። በእርግጥ ሟች የሆነው የሰው ልጅ አንዳች ከማይሳነው አምላክ ጋር ሲወዳደር እጅግ አነስተኛ ነው። ከብዙ ሺህ ዓመታት በፊት ስለተፈጠሩት የዚህ አምላክ አስደናቂ ፍጥረታት በቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ “በመጀመሪያ አምላክ ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ” በሚለው ቀላል አነጋገር ተገልጿል።—ዘፍ. 1:1
ኢየሱስ ምድር ላይ የኖረበት ዘመን
16 የኢየሱስን ምድራዊ ሕይወት የሚተርኩት በመንፈስ መሪነት የተጻፉ አራቱ ዘገባዎች በሚከተለው ቅደም ተከተል መሠረት እንደተጻፉ ይታመናል፦ ማቴዎስ (በ41 ዓ.ም. ገደማ)፣ ሉቃስ (በ56-58 ዓ.ም. ገደማ)፣ ማርቆስ (በ60-65 ዓ.ም. ገደማ) እና ዮሐንስ (በ98 ዓ.ም. ገደማ) ናቸው። ባለፈው ምዕራፍ ላይ እንደተብራራው በሉቃስ 3:1-3 ላይ ከሰፈሩት መረጃዎች በተጨማሪ የጢባርዮስ ግዛት የጀመረው በ14 ዓ.ም. መሆኑን መሠረት በማድረግ ኢየሱስ ታላቅ አገልግሎቱን ወደጀመረበት ወደ 29 ዓ.ም. እንደርሳለን። በማቴዎስ ላይ የሰፈሩት ክንውኖች የተጻፉት ሁልጊዜ ቅደም ተከተላቸውን ጠብቀው ባይሆንም ሌሎቹ ሦስት የወንጌል ዘገባዎች ግን በአብዛኛው የተጻፉት ዓበይት ክንውኖቹ በተፈጸሙበት ትክክለኛ ቅደም ተከተል መሠረት ይመስላል። የዚህ ምዕራፍ አባሪ በሆነው ሠንጠረዥ ላይ ክንውኖቹ በቅደም ተከተል ቀርበዋል። ከሦስቱ የወንጌል ዘገባዎች መካከል የመጨረሻው ከተጻፈ ከ30 ዓመታት በኋላ የተጻፈው የዮሐንስ ወንጌል በሌሎቹ ላይ የማይገኙ አስፈላጊ ቁም ነገሮችን የሚያሟላ መሆኑን ማየት ይቻላል። የዮሐንስ ወንጌል ኢየሱስ በምድር ላይ አገልግሎቱን ባከናወነባቸው ዓመታት የፋሲካ በዓል አራት ጊዜ መከበሩን መጥቀሱ ከፍተኛ ትርጉም አለው፤ ይህም ኢየሱስ ሦስት ዓመት ተኩል እንዳገለገለና አገልግሎቱ ያበቃው በ33 ዓ.ም. መሆኑን ያረጋግጣል።—ዮሐ. 2:13፤ 5:1፤ 6:4፤ 12:1 እና 13:1
17 ኢየሱስ የሞተው በ33 ዓ.ም. መሆኑ በሌላም ማስረጃ ተረጋግጧል። በሙሴ ሕግ መሠረት ኒሳን 15 በማንኛውም ቀን ቢውል ምንጊዜም ልዩ ሰንበት ተደርጎ ይታይ ነበር። ኒሳን 15 ከሳምንታዊው ሰንበት ጋር ከተገጣጠመ ዕለቱ “ታላቅ ሰንበት” በመባል ይታወቅ ስለነበርና ዮሐንስ 19:31 ደግሞ ኢየሱስ በሞተ በማግሥቱ ታላቅ ሰንበት መዋሉን ስለሚናገር ኢየሱስ የሞተው ዓርብ ዕለት ነበር ማለት ነው። ከዚህም በላይ ኒሳን 14 ዓርብ ላይ የዋለው በ31 ወይም በ32 ሳይሆን በ33 ዓ.ም. ብቻ ነበር። ስለዚህ ኢየሱስ የሞተው ኒሳን 14, 33 ዓ.ም. መሆን አለበት።
18 ሰባኛው “ሳምንት”፣ 29-36 ዓ.ም.፦ በዳንኤል 9:24-27 ላይም ኢየሱስ አገልግሎቱን ስለሚያከናውንበት ጊዜ የተገለጸ ሲሆን “ኢየሩሳሌምን ለማደስና መልሶ ለመገንባት ትእዛዝ ከሚወጣበት ጊዜ አንስቶ መሪ የሆነው መሲሕ እስከሚገለጥበት ጊዜ ድረስ” 69 የዓመታት ሳምንታት (483 ዓመታት) እንደሚያልፉ ተተንብዮአል። በነህምያ 2:1-8 መሠረት ይህ ትእዛዝ የወጣው የፋርስ ንጉሥ “አርጤክስስ በነገሠ በ20ኛው ዓመት” ነበር። አርጤክስስ መግዛት የጀመረው መቼ ነበር? ከእሱ በፊት ንጉሥ የነበረው ወላጅ አባቱ ዜርሰስ የሞተው በ475 ዓ.ም. ማብቂያ ላይ ነበር። በመሆኑም አርጤክስስ ሥልጣን የጨበጠው በ475 ዓ.ም. ሲሆን ይህንንም ከግሪክ፣ ከፋርስና ከባቢሎን ከተገኙ ጠንካራ የማስረጃ ምንጮች ማረጋገጥ ይቻላል። ለምሳሌ ያህል፣ ግሪካዊው ታሪክ ጸሐፊ ቱሳይዳይደስ (ትክክለኛ ታሪክ በመጻፍ የታወቀ ነው) አርጤክስስ “ንግሥና እንደያዘ አካባቢ” ግሪካዊው የፖለቲካ ሰው ቴሚስቶክልስ ወደ ፋርስ መሸሹን ጽፏል። በመጀመሪያው መቶ ዘመን የኖረው ሌላው ግሪካዊ ታሪክ ጸሐፊ ዲዶረስ ሲከለስ ደግሞ ቴሚስቶክልስ የሞተው በ471/470 ዓ.ም. እንደነበረ ያረጋግጥልናል። ቴሚስቶክልስ ከአገሩ ሸሽቶ ወደ ፋርስ ከሄደ በኋላ አርጤክስስ ፊት ከመቅረቡ በፊት ለአንድ ዓመት ያህል የፋርስ ቋንቋ ለመማር እንዲፈቀድለት ጠይቆ ፈቃድ አግኝቷል። ስለዚህ ቴሚስቶክልስ በፋርስ መኖር የጀመረው ከ472 ዓ.ዓ. በኋላ ሊሆን ስለማይችል እዚያ የመጣው በ473 ዓ.ዓ. ሳይሆን አይቀርም። ይህ ወቅት ደግሞ አርጤክስስ ‘ንግሥና የያዘበት አካባቢ’ ነበር።
19 በመሆኑም ‘አርጤክስስ የነገሠበት 20ኛው ዓመት’ 455 ዓ.ዓ. ይሆናል ማለት ነው። ወደ ዘመናችን አቆጣጠር ስንሸጋገር ዜሮ ዓመት እንደሌለ ሳንዘነጋ ከአርጤክስስ 20ኛው ዓመት ጀምረን 483 ዓመታት (69 “ሳምንት”) ስንቆጥር “መሪ የሆነው መሲሕ” የተገለጠበት 29 ዓ.ም. ላይ እንደርሳለን። ኢየሱስ በዚያ ዓመት የመከር ወራት ላይ ከተጠመቀና በመንፈስ ቅዱስ ከተቀባ በኋላ መሲሕ ሆነ። ከዚህ በተጨማሪ ትንቢቱ “በሳምንቱም አጋማሽ ላይ መሥዋዕትንና የስጦታ መባን ያስቀራል” በማለት ይገልጻል። ይህ የሆነው ኢየሱስ ራሱን መሥዋዕት አድርጎ በማቅረቡ ምክንያት አይሁዳውያን የሚያቀርቧቸው መሥዋዕቶች ጠቀሜታቸውን ባጡበት ወቅት ነበር። የዚህ ‘ሳምንት አጋማሽ’ ሦስት ዓመት ተኩል የሚፈጅ ሲሆን ኢየሱስ ወደተገደለበት 33 ዓ.ም. የጸደይ ወራት ላይ ያደርሰናል። ይሁን እንጂ በ70ኛው ሳምንት በሙሉ ‘መሪው ለብዙዎች ቃል ኪዳኑን ያጸናል።’ ይህም ከ29 እስከ 36 ዓ.ም. ባሉት ሰባት ዓመታት ይሖዋ ለአይሁዳውያን ልዩ ሞገስ ማሳየቱን እንደሚቀጥል ይጠቁማል። ያልተገረዙ አሕዛብ መንፈሳዊ እስራኤላውያን እንዲሆኑ አጋጣሚው የተከፈተላቸው ከዚህ ጊዜ በኋላ ብቻ ሲሆን ይህንንም በ36 ዓ.ም. ክርስትናን ከተቀበለው ከቆርኔሌዎስ ሁኔታ ማየት ይቻላል።—ሥራ 10:30-33, 44–48፤ 11:1
በሐዋርያት ዘመን የነበሩትን ዓመታት ማስላት
20 በ33 እና በ49 ዓ.ም. መካከል የነበሩት ዓመታት፦ አርባ አራት ዓ.ም. ለዚህ ክፍለ ዘመን ጠቃሚ መነሻና መድረሻ ዓመት ሆኖ ሊያገለግል ይችላል። ጆሴፈስ በጻፈው መሠረት (ጁዊሽ አንቲኩዊቲስ፣ XIX, 351 [viii, 2]) የሮማው ንጉሠ ነገሥት ቀላውዴዎስ (በ41 ዓ.ም.) ከነገሠ በኋላ ቀዳማዊ ሄሮድስ አግሪጳ ለሦስት ዓመት በንግሥናው ቀጥሏል። ሄሮድስ የሞተው በ44 ዓ.ም. መሆኑን ታሪካዊ ማስረጃዎች ያሳያሉ። ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ ስንመለስ፣ አጋቦስ ታላቅ ረሃብ እንደሚከሰት “መንፈስ አነሳስቶት” ትንቢት የተናገረው፣ ሐዋርያው ያዕቆብ በሰይፍ የተገደለው እንዲሁም ጴጥሮስ በፋሲካ በዓል ሰሞን የታሰረውና በተአምራዊ መንገድ የተፈታው ሄሮድስ ከመሞቱ በፊት ነበር። እነዚህ ሁሉ ክስተቶች የተፈጸሙት በ44 ዓ.ም. ሊሆን ይችላል።—ሥራ 11:27, 28፤ 12:1-11, 20-23
21 በትንቢት የተነገረው ረሃብ የደረሰው በ46 ዓ.ም. ገደማ ነበር። በመሆኑም ጳውሎስና በርናባስ “በኢየሩሳሌም እርዳታ ከሰጡ በኋላ” የተመለሱት በዚህ ወቅት መሆን አለበት። (ሥራ 12:25) ወደ ሶርያ አንጾኪያ ከተመለሱ በኋላ የመጀመሪያውን ሚስዮናዊ ጉዞ እንዲያደርጉ በመንፈስ ቅዱስ ተለዩ፤ ጉዞው ቆጵሮስን እንዲሁም በትንሿ እስያ የሚገኙ ሌሎች በርካታ ከተሞችንና አውራጃዎችን የሚያካትት ነበር። በተጨማሪም በትንሿ እስያ ያሳለፉትን የክረምት ወቅት ጨምሮ ከ47 ዓ.ም. የጸደይ ወራት አንስቶ እስከ 48 ዓ.ም. የመከር ወራት ድረስ ያለውን ጊዜ ሊፈጅ ይችላል። ጳውሎስ ቀጣዩን ክረምት ያሳለፈው በሶርያ አንጾኪያ ሊሆን ይችላል፤ ይህ ደግሞ ወደ 49 ዓ.ም. የጸደይ ወራት ያደርሰናል።—ሥራ 13:1–14:28
22 በገላትያ ምዕራፍ 1 እና 2 ላይ የሰፈረው ዘገባ ከዚህ የዘመን ስሌት ጋር የሚገጣጠም ይመስላል። በእነዚህ ምዕራፎች ላይ ጳውሎስ ወደ ክርስትና ከተለወጠ በኋላ ለየት ላለ ዓላማ ሁለት ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም መሄዱን ተናግሯል፤ አንደኛው “ከሦስት ዓመት በኋላ” ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ “ከ14 ዓመት በኋላ” ነው። (ገላ. 1:17, 18፤ 2:1) እነዚህ ሁለት ወቅቶች በዘመኑ አቆጣጠር መሠረት እንደ መደበኛ ቁጥሮች (ኦርዲናል) ከተወሰዱና ዘገባው እንደሚያመለክተው ጳውሎስ ወደ ክርስትና የተለወጠው በሐዋርያት ዘመን መጀመሪያ አካባቢ ከሆነ 3ቱና 14ቱ ዓመታት ከ34-36 እና ከ36-49 ዓ.ም. እንደሆኑ ልናስብ እንችላለን።
23 በገላትያ መጽሐፍ ላይ እንደተገለጸው ጳውሎስ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም የተጓዘው በግዝረት ጉዳይ ላይ ለመነጋገር ሳይሆን አይቀርም፤ ከጳውሎስ ጋር አብሮ የተጓዘው ቲቶ እንዲገረዝ ያልተጠየቀ መሆኑ ይህን ይጠቁማል። ይህ ጊዜ በሐዋርያት ሥራ 15:1-35 ላይ እንደተገለጸው በግዝረት ጉዳይ ላይ ውሳኔ ለማግኘት ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ ከነበረበት ጊዜ ጋር ከተገጣጠመ 49 ዓ.ም. የሚያርፈው ጳውሎስ የመጀመሪያውንና ሁለተኛውን ሚስዮናዊ ጉዞ ባደረገበት ጊዜ መካከል ይሆናል። ከዚህም በላይ ገላትያ 2:1-10 እንደሚለው ጳውሎስ በዚህ አጋጣሚ ተጠቅሞ እየሰበከ ያለውን ወንጌል በኢየሩሳሌም ጉባኤ ላሉት ‘ከፍ ተደርገው ለሚታዩ’ ወንድሞች ገልጾላቸዋል። ይህንም ያደረገው ‘እየሮጠ ያለው በከንቱ እንዳይሆን ስጋት ስላደረበት’ ነበር። ወቅቱም የመጀመሪያ ሚስዮናዊ ጉዞውን እንዳጠናቀቀ ነው ብሎ ማሰቡ ምክንያታዊ ይሆናል። ጳውሎስ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም የተጓዘው ‘በተገለጠለት ራእይ መሠረት’ ነበር።
24 የጳውሎስ ሁለተኛ ሚስዮናዊ ጉዞ፤ ከ49-52 ዓ.ም. ገደማ፦ ጳውሎስ ከኢየሩሳሌም ከተመለሰ በኋላ በሶርያ አንጾኪያ የተወሰነ ጊዜ አሳለፈ። ስለዚህ ሁለተኛ ሚስዮናዊ ጉዞውን ለማድረግ ከሶርያ አንጾኪያ የተነሳው በ49 ዓ.ም. የበጋ ወራት መሆን አለበት። (ሥራ 15:35, 36) ይኼኛው ጉዞ ከመጀመሪያው የበለጠ ሰፊ ስለነበር ክረምቱን በትንሹ እስያ ማሳለፍ ግድ ይሆንበታል። የመቄዶንያ ሰዎች ያቀረቡለትን ጥሪ የተቀበለውና ወደ አውሮፓ የተሻገረው በ50 ዓ.ም. የጸደይ ወራት ሳይሆን አይቀርም። ከዚያም በፊልጵስዩስ፣ በተሰሎንቄ፣ በቤርያና በአቴና ወንጌልን ሰብኮ አዳዲስ ጉባኤዎች አቋቋመ። በአብዛኛው በእግር 2,090 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት የሚሸፍነው ይህ ጉዞ በ50 ዓ.ም. የመከር ወራት በአካይያ አውራጃ ወደምትገኘው ወደ ቆሮንቶስ እንዲደርስ አስችሎታል። (ሥራ 16:9, 11, 12፤ 17:1, 2, 10, 11, 15, 16፤ 18:1) የሐዋርያት ሥራ 18:11 በሚናገረው መሠረት ጳውሎስ በቆሮንቶስ የተቀመጠው ለ18 ወራት ሲሆን ይህም ወደ 52 ዓ.ም. መጀመሪያ ላይ ያደርሰናል። ክረምቱ ሲያበቃ ጳውሎስ በኤፌሶን አልፎ ወደ ቂሳርያ በመርከብ መጓዝ ይችላል። በኢየሩሳሌም ላለው ጉባኤ ሰላምታ ካቀረበ በኋላ በ52 ዓ.ም. የበጋ ወራት ገደማ ወደሚኖርበት ወደ ሶርያ አንጾኪያ ተመልሷል።—ሥራ 18:12-22
25 ጳውሎስ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ቆሮንቶስ የሄደው ከ50-52 ዓ.ም. ባሉት ዓመታት ለመሆኑ የመሬት ቁፋሮ ግኝት ተጨማሪ ማስረጃ ይሆነናል። ይህ ማስረጃ ንጉሠ ነገሥት ቀላውዴዎስ ለግሪክ ደልፋይ ነዋሪዎች የጻፈው የመልስ ደብዳቤ ሲሆን “ለአገረ ገዢው . . . ሉሲየስ ጁኒየስ፣ ጋልዮስ” የሚሉትን ቃላት የያዘ ቁራጭ ነው። በጽሑፉ ላይ የሚገኘው 26 ቁጥር ቀላውዴዎስ ለ26ኛ ጊዜ ንጉሠ ነገሥት ሆኖ እንዲገዛ ተቀባይነት ማግኘቱን ያመለክታል በማለት ታሪክ ጸሐፊዎች በአጠቃላይ ይስማማሉ። ሌሎች የተቀረጹ ጽሑፎችም ከነሐሴ 1, 52 ዓ.ም. ቀደም ብሎ ቀላውዴዎስ ለ27ኛ ጊዜ መሾሙን ይጠቁማሉ። አንድ አገረ ገዢ በሥልጣን ላይ የሚቆየው ከበጋ መጀመሪያ አንስቶ ለአንድ ዓመት ነበር። በመሆኑም ጋልዮስ የአካይያ አገረ ገዢ ሆኖ ያሳለፈው አንድ ዓመት ከ51 ዓ.ም. የበጋ ወቅት አንስቶ እስከ 52 ዓ.ም. የበጋ ወቅት ድረስ እንደሚሆን ግልጽ ነው። “ጋልዮስ አካይያን ያስተዳድር በነበረበት ጊዜ አይሁዳውያን ግንባር ፈጥረው በጳውሎስ ላይ ተነሱበት፤ በፍርድ ወንበር ፊት [አቀረቡት]።” ጋልዮስ ጳውሎስን በነፃ ከለቀቀው በኋላ ሐዋርያው ‘ለተወሰኑ ቀናት ቆይቶ’ በመርከብ ወደ ሶርያ ሄደ። (ሥራ 18:11, 12, 17, 18) ይህም ጳውሎስ ለ18 ወራት በቆሮንቶስ የቆየበት ጊዜ ያበቃው በ52 ዓ.ም. የጸደይ ወራት መሆኑን የሚያረጋግጥ ይመስላል። ሌላው የጊዜ አመልካች ጳውሎስ ቆሮንቶስ ሲደርስ “የጳንጦስ ተወላጅ የሆነ አቂላ የተባለ አይሁዳዊ አገኘ፤ ይህ ሰው ቀላውዴዎስ አይሁዳውያን ሁሉ ከሮም እንዲወጡ ባዘዘው መሠረት ከሚስቱ ከጵርስቅላ ጋር በቅርቡ ከጣሊያን የመጣ ነበር” የሚለው ዘገባ ነው። (ሥራ 18:2) በአምስተኛው መቶ ዘመን መጀመሪያ ላይ የኖረው ታሪክ ጸሐፊ ፓውለስ ኦሮሲየስ እንደጻፈው ከሆነ አይሁድ ከሮም እንዲወጡ ትእዛዝ የተላለፈው በቀላውዴዎስ ዘጠነኛ ዓመት ሲሆን ይህም በ49 ወይም በ50 ዓ.ም. መጀመሪያ ላይ ነበር። በመሆኑም አቂላና ጵርስቅላ በዚያ ዓመት የመከር ወቅት ከመግባቱ በፊት ቆሮንቶስ ደርሰው ሊሆን ይችላል። ይህም ጳውሎስ ከ50 ዓ.ም. የመከር ወራት ጀምሮ እስከ 52 ዓ.ም. የጸደይ ወራት ድረስ በቆሮንቶስ እንዲቀመጥ ያስችለዋል።
26 የጳውሎስ ሦስተኛ ሚስዮናዊ ጉዞ፣ ከ52-56 ዓ.ም. ገደማ፦ ጳውሎስ በሶርያ አንጾኪያ “የተወሰነ ጊዜ ካሳለፈ” በኋላ በድጋሚ ወደ ትንሹ እስያ ያመራ ሲሆን ኤፌሶን የደረሰው ከ52-53 ዓ.ም. ባለው የክረምት ወቅት ሳይሆን አይቀርም። (ሥራ 18:23፤ 19:1) ጳውሎስ “ለሦስት ወራት” ከዚያም ደግሞ “ለሁለት ዓመት” በኤፌሶን እያስተማረ ከቆየ በኋላ ወደ መቄዶንያ ሄደ። (ሥራ 19:8-10) ከጊዜ በኋላ ከኤፌሶን ለመጡት የበላይ ተመልካቾች በመካከላቸው “ሦስት ዓመት” እንዳገለገለ ተናግሯል፤ እርግጥ ይህ አኃዝ ጳውሎስ ጠቅለል አድርጎ ለመግለጽ የተጠቀመበት ነው። (ሥራ 20:31) ጳውሎስ ሦስት ወር የሚፈጀውን የክረምት ወቅት በግሪክ፣ ቆሮንቶስ ለማሳለፍ ‘የጴንጤቆስጤ በዓል’ ከተከበረ በኋላ በ55 ዓ.ም. መጀመሪያ ላይ ከኤፌሶን የተንቀሳቀሰ ይመስላል። ከዚያም ተመልሶ በስተ ሰሜን አቅጣጫ በመጓዝ በ56 ዓ.ም. የፋሲካ በዓል ወቅት ፊልጵስዩስ ደረሰ። ከዚያ ተነስቶ በጥሮአስና በሚሊጢን በኩል አድርጎ እስከ ቂሳርያ ድረስ በመርከብ ከሄደ በኋላ ጉዞውን በመቀጠል በ56 ዓ.ም. ለጴንጤቆስጤ በዓል ኢየሩሳሌም ደረሰ።—1 ቆሮ. 16:5-8፤ ሥራ 20:1-3, 6, 15, 16፤ 21:8, 15-17
27 መደምደሚያዎቹ ዓመታት፣ ከ56-100 ዓ.ም.፦ ጳውሎስ ተይዞ የታሰረው ኢየሩሳሌም ከደረሰ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ነበር። ወደ ቂሳርያ ተወስዶ ፊስጦስ በፊሊክስ ምትክ አገረ ገዢ ሆኖ እስከመጣበት ጊዜ ድረስ ለሁለት ዓመት ታስሮ ቆየ። (ሥራ 21:33፤ 23:23–35፤ 24:27) ፊስጦስ የመጣበትና ጳውሎስ ወደ ሮም የተላከበት ጊዜ 58 ዓ.ም. ሳይሆን አይቀርም። ጳውሎስ መርከብ ተሰብሮበት ማልታ በምትባለው ደሴት ክረምቱን ካሳለፈ በኋላ ጉዞው የተጠናቀቀው በ59 ዓ.ም. ሲሆን በሮም ታስሮ እያለ እየሰበከና እያስተማረ ለሁለት ዓመት ያህል ወይም እስከ 61 ዓ.ም. ገደማ ድረስ እዚያ መቆየቱን ዘገባው ያመለክታል።—ሥራ 27:1፤ 28:1, 11, 16, 30, 31
28 በሐዋርያት ሥራ ላይ የሰፈረው ታሪካዊ ዘገባ ከዚህ ያለፈ የሚነግረን ነገር ባይኖርም ጳውሎስ ከእስር ተለቆ የሚስዮናዊነት ሥራውን በመቀጠል ወደ ቀርጤስ፣ ግሪክና መቄዶንያ እንደተጓዘ የሚያመለክቱ ፍንጮች አሉ። እስከ ስፔን ድረስ ርቆ ይሂድ አይሂድ አይታወቅም። ጳውሎስ በ65 ዓ.ም. ገደማ ሮም ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ከታሰረ በኋላ በኔሮ ትእዛዝ በሰማዕትነት እንዳለፈ ይታመናል። ሮም ውስጥ ከፍተኛ ቃጠሎ መነሳቱን ተከትሎ ኔሮ በክርስቲያኖች ላይ ኃይለኛ ስደት ያስነሳው በሐምሌ 64 ዓ.ም. መሆኑን ዓለማዊ የታሪክ ምንጮች ይናገራሉ። ጳውሎስ ‘በሰንሰለት’ የታሰረበትና ከዚያም የተገደለበት ጊዜ ከዚህ ወቅት ጋር ይስማማል።—2 ጢሞ. 1:16፤ 4:6, 7
29 ሐዋርያው ዮሐንስ የጻፋቸው አምስት መጻሕፍት የተጻፉት ንጉሠ ነገሥት ዶሚሺያን በክርስቲያኖች ላይ ያመጣው ስደት ማብቂያ ላይ ነበር። ዶሚሺያን ከ81-96 ዓ.ም. ከቆየው የንግሥና ዘመኑ ውስጥ በመጨረሻዎቹ ሦስት ዓመታት እንደ እብድ አድርጎት እንደነበር ይነገራል። ዮሐንስ የራእይ መጽሐፍን የጻፈው በ96 ዓ.ም. ገደማ በጳጥሞስ ደሴት ላይ በግዞት እያለ ነበር። ወንጌሉንና ሦስት ደብዳቤዎቹን የጻፈው ከእስር ከተለቀቀ በኋላ በኤፌሶን ወይም በአቅራቢያዋ ሆኖ ነበር። ከሐዋርያት ሁሉ መጨረሻ ላይ የሞተው ዮሐንስ ሲሆን ይህም በ100 ዓ.ም. ገደማ ነበር።
30 ስለዚህ በዓለም የታሪክ መዛግብት ላይ የሰፈሩ ክስተቶችን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሰፈረው የዘመን ስሌትና ትንቢት ጋር በማወዳደር የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች በጊዜ ሂደት መቼ እንደተፈጸሙ በግልጽ መረዳት እንችላለን። የመጽሐፍ ቅዱስ የዘመን ስሌት እርስ በርሱና ከታሪክ ጋር የሚስማማ መሆኑ ቅዱሳን መጻሕፍትን እንደ አምላክ ቃል አድርገን በሙሉ እምነት እንድንቀበል ያስችለናል።
[የግርጌ ማስታወሻዎች]
a ይህን ምዕራፍ በምናጠናበት ጊዜ ቅዱሳን ጽሑፎችን ጠለቅ ብሎ ማስተዋል (እንግሊዝኛ) ከተባለው መጽሐፍ ጥራዝ 1 ገጽ 458-67 ጋር ብናመሳክር ጥሩ ይሆናል።
b ጥናት ቁጥር 2 አንቀጽ 28, 29
c አብርሃም ኤፍራጥስን ከተሻገረበት ጊዜ እስከ ይስሐቅ ልደት 25 ዓመት፣ ከዚያም እስከ ያዕቆብ ልደት 60 ዓመት ሲሆን ያዕቆብ ወደ ግብፅ ሲወርድ 130 ዓመት ሆኖት ነበር።—ዘፍ. 12:4፤ 21:5፤ 25:26፤ 47:9
d በ2016 ይህ ዘመን ከ6041 ላይ መቀነስ ይኖርበታል።
e የመስከረም 22, 1986 ንቁ! (እንግሊዝኛ) ገጽ 17–27፤ የሚያዝያ 8, 1972 ንቁ! (እንግሊዝኛ) ገጽ 5-20
[በገጽ 21 ላይ የሚገኝ ሠንጠረዥ]
የኢየሱስ ምድራዊ ሕይወት አበይት ክንውኖች አራቱ ወንጌሎች በጊዜ ቅደም ተከተል
ምልክት፦ “ገ” የሚለው “ገደማ” ማለት ነው።
ጊዜ ቦታ ክንውን
ኢየሱስ አገልግሎቱን ከመጀመሩ በፊት የተከናወኑ ነገሮች
3 ዓ.ዓ. ኢየሩሳሌም፣ ቤተ መቅደስ መጥምቁ ዮሐንስ እንደሚወለድ ለዘካርያስ
አስቀድሞ ተነገረው ሉቃስ 1:5-25
2 ዓ.ዓ. ገ. ናዝሬት፤ ይሁዳ ኢየሱስ እንደሚወለድ ለማርያም አስቀድሞ ተነገራት፤
እሷም ኤልሳቤጥን ልትጠይቅ ሄደች ሉቃስ 1:26-56
2 ዓ.ዓ. የይሁዳ መጥምቁ ዮሐንስ ተወለደ፤ ከዚያም በበረሃ ያሳለፈው ሕይወት
ኮረብታማ ምድር ሉቃስ 1:57-80
2 ዓ.ዓ. ቤተልሔም ኢየሱስ (ሌሎች ነገሮች ሁሉ በእሱ አማካኝነት ወደ ሕልውና
ጥቅ. 1 ገ.የመጡበት ቃል) የአብርሃምና የዳዊት ዘር ሆኖ ተወለደ
ቤተልሔም አንድ መልአክ ምሥራች አበሰረ፤ እረኞች ሕፃኑን ሊያዩ ሄዱ
አቅራቢያ ሉቃስ 2:8-20
ቤተልሔም፤ ኢየሩሳሌም ኢየሱስ ተገረዘ (በ8ኛው ቀን)፣ ቤተ መቅደስ
ተወሰደ (ከ40ኛው ቀን በኋላ) ሉቃስ 2:21-38
1 ዓ.ዓ. ኢየሩሳሌም፤ ናዝሬት ኮከብ ቆጣሪዎች፤ ወደ ግብፅ መሸሽ፤
ወይም 1 ዓ.ም. ቤተልሔም፤ ሕፃናት ተገደሉ፤ የኢየሱስ መወለድ ማቴ 2:1-23
12 ዓ.ም. ኢየሩሳሌም የአሥራ ሁለት ዓመቱ ኢየሱስ በፋሲካ በዓል ላይ፤ ወደ ቤት ሄደ
ኢየሱስ አገልግሎቱን ሲጀምር የተከናወኑ ነገሮች
29፣ መከር የዮርዳኖስ ወንዝ የኢየሱስ መጠመቅና መቀባት፣ በዳዊት የዘር ሐረግ
ሰው ሆኖ ቢወለድም የአምላክ ልጅ እንደሆነ ተገለጸ
የይሁዳ የኢየሱስ መጾምና መፈተን ማቴ 4:1-11
ምድረ በዳ ማር 1:12, 13 ሉቃስ 4:1-13
የላይኛው የዮርዳኖስ የመጀመሪያዎቹ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ዮሐ 1:35-51
ሸለቆ
በገሊላ የምትገኘው ቅፍርናሆም የኢየሱስ የመጀመሪያው ተአምር፤
ቃና፤ ወደ ቅፍርናሆም ሄደ ዮሐ 2:1-12
30፣ ፋሲካ ኢየሩሳሌም የፋሲካ በዓል መከበር፤ ነጋዴዎችን ከቤተ መቅደስ
አባረረ ዮሐ 2:13-25
ኢየሩሳሌም ከኒቆዲሞስ ጋር ተነጋገረ ዮሐ 3:1-21
ይሁዳ፤ ሄኖን የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት አጠመቁ፤
ዮሐንስ እየቀነሰ ይሄዳል ዮሐ 3:22-36
በሰማርያ የምትገኘው ኢየሱስ ወደ ገሊላ እየሄደ ሳለ ሳምራውያንን አስተማረ
ሲካር ዮሐ 4:4-43
ኢየሱስ በገሊላ ያከናወነው ታላቅ አገልግሎት
ናዝሬት፤ ቃና፤ አንድ ልጅ ፈወሰ፤ የተሰጠውን ተልዕኮ አነበበ፤ ሳይቀበሉት
ቅፍርናሆም ቀሩ፤ ወደ ቅፍርናሆም ሄደ ማቴ 4:13-16
ይሁዳ በይሁዳ ምኩራቦች ሰበከ ሉቃስ 4:44
31፣ ፋሲካ ኢየሩሳሌም በበዓሉ ላይ ተገኘ፤ አንድ ሰው ፈወሰ፤ ፈሪሳውያንን
አወገዘ 5:1-47
ከኢየሩሳሌም ደቀ መዛሙርቱ በሰንበት እሸት ቀጠፉ ማቴ 12:1-8
መልስ (?) ማር 2:23-28 ሉቃስ 6:1-5
በቅፍርናሆም አቅራቢያ 12ቱ ሐዋርያት ሆነው ተመረጡ ማር 3:13-19
ያለ ተራራ ሉቃስ 6:12-16
በቅፍርናሆም አቅራቢያ የተራራው ስብከት ማቴ 5:1–7:29
ቅፍርናሆም የጦር መኮንኑን አገልጋይ ፈወሰ ማቴ 8:5-13
ናይን የመበለቲቱን ልጅ ከሞት አስነሳ ሉቃስ 7:11-17
ገሊላ በእስር ላይ ያለው ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን
ወደ ኢየሱስ ላከ ማቴ 11:2-19 ሉቃስ 7:18-35
ገሊላ ከተሞች ተነቀፉ፤ ለሕፃናት የተገለጡ ነገሮች፤
ልዝብ ቀንበር ማቴ 11:20-30
ገሊላ ኃጢአተኛ የሆነች ሴት እግሩ ላይ ዘይት አፈሰሰች፤
ዕዳ የነበረባቸው ሰዎች ምሳሌ ሉቃስ 7:36-50
ገሊላ ከ12ቱ ጋር በገሊላ ያደረገው ሁለተኛው የስብከት ጉዞ
ገሊላ አጋንንት አስወጣ፤ ከብዔልዜቡል ጋር ያብራል
ተብሎ ተከሰሰ ማቴ 12:22-37 ማር 3:19-30
ገሊላ ጸሐፍትና ፈሪሳውያን ምልክት እንዲያሳያቸው ጠየቁ
ገዳራ፣ አጋንንት ያደሩባቸው ሁለት ሰዎች ተፈወሱ፤ አጋንንት
ከገሊላ ባሕር አሳማዎች ውስጥ ገቡ ማቴ 8:28-34
ደቡባዊ ምሥራቅ ማር 5:1-20 ሉቃስ 8:26-39
ቅፍርናሆም (?) ሁለት ዓይነ ስውሮችንና ጋኔን ዲዳ ያደረገውን ሰው
ፈወሰ ማቴ 9:27-34
ናዝሬት ወዳደገበት ከተማ ዳግመኛ ሄደ፤ አሁንም ተቀባይነት
32፣ ፋሲካ ቅፍርናሆም (?)፤ ከገሊላ ባሕር በስተ ሰሜን ምሥራቅ ሐዋርያት ከስብከት ጉዞ
በተቃረበበት ጊዜ ተመለሱ፤ 5,000 ሰዎችን መገበ
ከገሊላ ባሕር ጌንሴሬጥ ኢየሱስን ሊያነግሡት ሞከሩ፤ በባሕር ላይ ተራመደ፤
በስተ ሰሜን ምሥራቅ፤ ብዙ ሰዎች ፈወሰ ማቴ 14:22-36
ቅፍርናሆም ኢየሱስ “ሕይወት የሚያስገኝ ምግብ” እንደሆነ ተናገረ፤
ብዙዎች ተሰናክለው ትተውት ሄዱ ዮሐ 6:22-71
32፣ ከፋሲካ ቅፍርናሆም የአምላክን ቃል ከንቱ የሚያደርጉ ወጎች ማቴ 15:1-20
ፊንቄ፤ ዲካፖሊስ 4,000 ሰዎችን መገበ ማቴ 15:21-38 ጢሮስ አቅራቢያ፣ ሲዶና፤ ማር 7:24–8:9
ከዚያ ወደ ዲካፖሊስ፤
መጊዶን ሰዱቃውያንና ፈሪሳውያን እንደገና ምልክት
ቅፍርናሆም ለቀረጥ የሚከፈል ገንዘብ በተአምር ተገኘ
ኢየሱስ በኋላ ላይ በይሁዳ ያከናወነው አገልግሎት
32፣ ኢየሩሳሌም ኢየሱስ በዳስ በዓል ላይ ለሕዝቡ የሰጠው ትምህርት
የዳስ በዓል ዮሐ 7:11-52
ኢየሩሳሌም ከበዓሉ በኋላ አስተማረ፤ አንድ ዓይነ ስውር
ፈወሰ ዮሐ 8:12–9:41
ይሁዳ ሊሆን ይችላል 70ዎቹ እንዲሰብኩ ተላኩ፤ ተመልሰው ሪፖርት
አቀረቡ ሉቃስ 10:1-24
ይሁዳ፤ ቢታንያ ስለ ደጉ ሳምራዊ ተናገረ፤ በማርታና
በማርያም ቤት ሉቃስ 10:25-42
ይሁዳ ሊሆን ይችላል የናሙናውን ጸሎት እንደገና አስተማረ፤
ያለመታከት መለመን ሉቃስ 11:1-13
ይሁዳ ሊሆን ይችላል የሐሰት ክስ አስተባበለ፤ ትውልዱ የሚወገዝ
እንደሆነ አመለከተ ሉቃስ 11:14-36
ይሁዳ ሊሆን ይችላል ኢየሱስ በአንድ ፈሪሳዊ ቤት ማዕድ ፊት ቀርቦ ሳለ
ግብዞችን አወገዘ ሉቃስ 11:37-54
ይሁዳ ሊሆን ይችላል የአምላክን አሳቢነት አስመልክቶ የተሰጠ ንግግር፤
ታማኝ መጋቢ ሉቃስ 12:1-59
ይሁዳ ሊሆን ይችላል በሰንበት የአካል ጉዳተኛ የሆነች ሴት
ፈወሰ፤ ሦስት ምሳሌዎች ሉቃስ 13:1-21
32፣ ኢየሩሳሌም ኢየሱስ በመታደስ በዓል ላይ ተገኘ፤ ጥሩ እረኛ
የመታደስ በዓል ዮሐ 10:1-39
ኢየሱስ በኋላ ላይ ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ያከናወነው አገልግሎት
ከዮርዳኖስ ማዶ ብዙዎች በኢየሱስ አመኑ ዮሐ 10:40-42
ፔሪያ ወደ ኢየሩሳሌም እየተጓዘ ሳለ በየከተማውና
(ከዮርዳኖስ ማዶ) በየመንደሩ አስተማረ ሉቃስ 13:22
ፔሪያ ወደ መንግሥቱ መግባት፤ የሄሮድስ ዛቻ፤
የተተወ ቤት ሉቃስ 13:23-35
ፔሪያ ሊሆን ይችላል ትሕትና፤ ስለ አንድ ትልቅ የራት ግብዣ
የተነገረ ምሳሌ ሉቃስ 14:1-24
ፔሪያ ሊሆን ይችላል ደቀ መዝሙር መሆን የሚያስከፍለውን ዋጋ
ማስላት ሉቃስ 14:25-35
ፔሪያ ሊሆን ይችላል ምሳሌዎች፦ የጠፋ በግ፣ የጠፋ ሳንቲም፣
አባካኙ ልጅ ሉቃስ 15:1-32
ፔሪያ ሊሆን ይችላል ምሳሌዎች፦ ዓመፀኛ የቤት አስተዳዳሪ፣
ሀብታሙ ሰውና አልዓዛር ሉቃስ 16:1-31
ፔሪያ ሊሆን ይችላል ይቅር ባይነትና እምነት፤ የማይጠቅሙ ባሪያዎች
ቢታንያ ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት አስነሳው ዮሐ 11:1-46
ኢየሩሳሌም፤ ኤፍሬም ቀያፋ ኢየሱስ እንዲገደል ያቀረበው
ሐሳብ፤ ኢየሱስ አካባቢውን ለቆ ሄደ ዮሐ 11:47-54
ሰማርያ፤ ገሊላ በሰማርያና በገሊላ ሲያልፍ ፈወሰ
እንዲሁም አስተማረ ሉቃስ 17:11-37
ሰማርያ ወይም ምሳሌዎች፦ ትወተውት የነበረች መበለት፣
ገሊላ ፈሪሳዊና ቀረጥ ሰብሳቢ ሉቃስ 18:1-14
ፔሪያ ፔሪያን አቋርጦ ተጓዘ፤ ፍቺን በተመለከተ
ትምህርት ሰጠ ማቴ 19:1-12 ማር 10:1-12
ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ያከናወነው የመጨረሻ አገልግሎት
ኒሳን 8፣ 33 ቢታንያ ከፋሲካ በዓል ስድስት ቀን አስቀድሞ ቢታንያ
ደረሰ ዮሐ 11:55–12:1
ኒሳን 9 ቢታንያ በሥጋ ደዌ በተያዘው በስምዖን ቤት ተጋበዘ፤
ማርያም ኢየሱስን ቀባችው፤ አይሁዳውያን ኢየሱስንና አልዓዛርን ለማየት መጡ
ቢታንያ- ክርስቶስ እንደ ድል አድራጊ ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም
ኢየሩሳሌም ገባ ማቴ 21:1-11, 14-17
ኒሳን 10 ቢታንያ- ፍሬ አልባ የሆነችው የበለስ ዛፍ ተረገመች፤
ኢየሩሳሌም ለሁለተኛ ጊዜ ቤተ መቅደሱን አጠራ
ኢየሩሳሌም ከግሪኮች ጋር የተደረገ ውይይት፤ የአይሁዳውያን
አለማመን ዮሐ 12:20-50
ኒሳን 11 ቢታንያ- ፍሬ አልባዋ በለስ ደርቃ ተገኘች
ኢየሩሳሌም ማቴ 21:19-22 ማር 11:20-25
ኢየሩሳሌም፣ ግብርን፣ ትንሣኤንና ትእዛዝን በተመለከተ ኢየሱስን
ቤተ መቅደስ ለማጥመድ የቀረቡ ጥያቄዎች ማቴ 22:15-40
ኢየሩሳሌም፣ የመበለቲቱ አነስተኛ መዋጮ ማር 12:41-44
ቤተ መቅደስ ሉቃስ 21:1-4
ኒሳን 13 በኢየሩሳሌም አቅራቢያና ለፋሲካ በዓል የተደረገ ዝግጅት ማቴ 26:17-19
(ሐሙስ በኢየሩሳሌም ውስጥ ማር 14:12-16 ሉቃስ 22:7-13
ከሰዓት በኋላ)
ኢየሩሳሌም ኢየሱስ የሐዋርያቱን እግር አጠበ ዮሐ 13:1-20
ኢየሩሳሌም ረዳት፤ እርስ በርስ መዋደድ፤ መከራ፤
የኢየሱስ ጸሎት ዮሐ 14:1–17:26
ጌቴሴማኒ በአትክልቱ ስፍራ ሳለ የተሰማው ከፍተኛ
ጭንቀት፤ የኢየሱስ አልፎ መሰጠትና መያዝ
ኢየሩሳሌም በሐና፣ በቀያፋና በሳንሄድሪን ፊት ለፍርድ መቅረብ፤
ጴጥሮስ ካደ ማቴ 26:57–27:1
ኢየሩሳሌም ከሃዲው ይሁዳ ራሱን ሰቀለ ማቴ 27:3-10
ኢየሩሳሌም ጲላጦስ ፊት ቀረበ፣ ከዚያም ወደ ሄሮድስ ተወሰደ፤
በኋላ ደግሞ እንደገና ወደ ጲላጦስ ተወሰደ
(ዓርብ ከቀኑ ጎልጎታ፣ የኢየሱስ በመከራ እንጨት ላይ ተሰቅሎ መሞትና
ዘጠኝ ሰዓት ገ.) ኢየሩሳሌም ከዚያ ጋር የተያያዙ ክንውኖች ማቴ 27:31-56
ኒሳን 15 ኢየሩሳሌም ካህናትና ፈሪሳውያን መቃብሩ እንዲጠበቅ
አደረጉ ማቴ 27:62-66
ከኒሳን 16 በኋላ ኢየሩሳሌም፤ ገሊላ ከዚያ በኋላ ኢየሱስ ክርስቶስ በተደጋጋሚ
ታየ ማቴ 28:16-20 [1 ቆሮ. 15:5-7]
[በገጽ 28 ላይ የሚገኝ ሠንጠረዥ]
ታሪካዊ ክንውኖች የተፈጸሙባቸውን ዘመናት የሚያሳይ ሰንጠረዥ
ገ. የሚለው “ገደማ” ማለት ነው።
ጊዜ ክንውን ጥቅስ
4026 ዓ.ዓ. አዳም ተፈጠረ ዘፍ 2:7
ከ4026 ዓ.ዓ. የኤደን ቃል ኪዳን፣ ዘፍ 3:15
በኋላ የመጀመሪያው ትንቢት
ከ3896 ዓ.ዓ. ቃየን አቤልን ገደለው ዘፍ 4:8
በፊት
3896 ዓ.ዓ. ሴት ተወለደ ዘፍ 5:3
3404 ዓ.ዓ. ጻድቁ ሄኖክ ተወለደ ዘፍ 5:18
3339 ዓ.ዓ. ማቱሳላ ተወለደ ዘፍ 5:21
3152 ዓ.ዓ. ላሜህ ተወለደ ዘፍ 5:25
3096 ዓ.ዓ. አዳም ሞተ ዘፍ 5:5
3039 ዓ.ዓ. ሄኖክ ተወሰደ፤ ትንቢት ዘፍ 5:23, 24፤ ይሁዳ 14
የሚናገርበት ዘመን አበቃ
2970 ዓ.ዓ. ኖኅ ተወለደ ዘፍ 5:28, 29
2490 ዓ.ዓ. አምላክ የሰውን ዘር በተመለከተ ዘፍ 6:3
ውሳኔ አስተላለፈ
2470 ዓ.ዓ. ያፌት ተወለደ ዘፍ 5:32፤ 9:24፤ 10:21
2468 ዓ.ዓ. ሴም ተወለደ ዘፍ 7:11፤ 11:10
2370 ዓ.ዓ. ማቱሳላ ሞተ ዘፍ 5:27
2369 ዓ.ዓ. ከጥፋት ውኃ በኋላ የተደረገው ቃል ኪዳን ዘፍ 8:13፤ 9:16
2368 ዓ.ዓ. አርፋክስድ ተወለደ ዘፍ 11:10
ከ2269 ዓ.ዓ. በኋላ የባቤል ግንብ ግንባታ ዘፍ 11:4
2020 ዓ.ዓ. ኖኅ ሞተ ዘፍ 9:28, 29
2018 ዓ.ዓ. አብርሃም ተወለደ ዘፍ 11:26, 32፤ 12:4
1943 ዓ.ዓ. አብርሃም ወደ ከነአን ሲጓዝ ኤፍራጥስን ዘፍ 12:4, 7፤ ዘፀ 12:40፤
ተሻገረ፤ የአብርሃም ቃል ኪዳን ጸና፤ ገላ 3:17
እስከ ሕጉ ቃል ኪዳን ድረስ ያለው
የ430 ዓመት ጊዜ ጀመረ
1932 ዓ.ዓ. እስማኤል ተወለደ ዘፍ 16:15, 16
1919 ዓ.ዓ. የግርዘት ቃል ኪዳን ተደረገ ዘፍ 17:1, 10, 24
ሰዶምና ገሞራ ተፈረደባቸው ዘፍ 19:24
1918 ዓ.ዓ. ሕጋዊ ወራሽ የሆነው ይስሐቅ ተወለደ፤ ዘፍ 21:2, 5፤ ሥራ 13:17-20
“450 ዓመት ያህል” የተባለው ጊዜ ጀመረ
1881 ዓ.ዓ. ሣራ ሞተች ዘፍ 17:17፤ 23:1
1878 ዓ.ዓ. ይስሐቅና ርብቃ ተጋቡ ዘፍ 25:20
1868 ዓ.ዓ. ሴም ሞተ ዘፍ 11:11
1858 ዓ.ዓ. ኤሳውና ያዕቆብ ተወለዱ ዘፍ 25:26
1843 ዓ.ዓ. አብርሃም ሞተ ዘፍ 25:7
1818 ዓ.ዓ. ኤሳው የመጀመሪያዎቹን ሁለት ሚስቶቹን አገባ ዘፍ 26:34
1795 ዓ.ዓ. እስማኤል ሞተ ዘፍ 25:17
1774 ዓ.ዓ. ያዕቆብ ሊያን እና ራሔልን አገባ ዘፍ 29:23-30
1767 ዓ.ዓ. ዮሴፍ ተወለደ ዘፍ 30:23, 24
1761 ዓ.ዓ. ያዕቆብ ከካራን ወደ ከነአን ተመልሶ ሄደ ዘፍ 31:18, 41
1761 ዓ.ዓ. ገ. ያዕቆብ ከመልአክ ጋር ታገለ፤ ዘፍ 32:24-28
እስራኤል ተብሎ ተጠራ
1750 ዓ.ዓ. የዮሴፍ ወንድሞች፣ ዮሴፍን ለባርነት ሸጡት ዘፍ 37:2, 28
1738 ዓ.ዓ. ይስሐቅ ሞተ ዘፍ 35:28, 29
1737 ዓ.ዓ. ዮሴፍ የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትር ተደረገ ዘፍ 41:40, 46
1711 ዓ.ዓ. ያዕቆብ ሞተ ዘፍ 47:28
1657 ዓ.ዓ. ዮሴፍ ሞተ ዘፍ 50:26
ከ1613 ዓ.ዓ. በፊት ኢዮብ መከራ ደረሰበት ኢዮብ 1:8፤ 42:16
ከ1600 ዓ.ዓ. በኋላ ግብፅ የመጀመሪያው የዓለም ኃያል ዘፀ 1:8
መንግሥት ሆነች
1514 ዓ.ዓ. ገ. ሙሴ በእሳት የተያያዘ ቁጥቋጦ አየ ዘፀ 3:2
1513 ዓ.ዓ. ፋሲካ፤ እስራኤላውያን ግብፅን ለቀው ወጡ፤ ዘፀ 12:12፤
ይሖዋ በቀይ ባሕር አዳናቸው የግብፅ መንግሥት ዘፀ 14:27, 29, 30፤
ኃይል ተዳከመ፤ የ400 ዓመቱ የመከራ ጊዜ አበቃ ዘፍ 15:13, 14
በሲና ተራራ (ኮሬብ) የሕጉ ቃል ኪዳን ተደረገ ዘፀ 24:6-8
ሙሴ በምድረ በዳ የዘፍጥረት መጽሐፍን አጠናቀረ፤ ዮሐ 5:46
መጽሐፍ ቅዱስን የመጻፍ ሥራ ተጀመረ
1512 ዓ.ዓ. የማደሪያ ድንኳኑ ሥራ ተጠናቀቀ ዘፀ 40:17
የአሮን የክህነት ሥርዓት ተቋቋመ ዘሌ 8:34-36
ሙሴ ዘፀአትንና ዘሌዋውያንን ጽፎ አጠናቀቀ ዘሌ 27:34፤ ዘኁ 1:1
1473 ዓ.ዓ. ገ. ሙሴ የኢዮብ መጽሐፍን ጽፎ አጠናቀቀ ኢዮብ 42:16, 17
1473 ዓ.ዓ. ሙሴ በሞዓብ ሜዳ እያለ ዘኁልቁን ጽፎ አጠናቀቀ ዘኁ 35:1፤ 36:13
በሞዓብ ከእስራኤል ጋር የተደረገው ቃል ኪዳን ዘዳ 29:1
ሙሴ በሞዓብ በሚገኘው ነቦ ተራራ ላይ ሞተ ዘዳ 34:1, 5, 7
እስራኤላውያን በኢያሱ እየተመሩ ወደ ከነአን ገቡ ኢያሱ 4:19
1467 ዓ.ዓ. እስራኤላውያን፣ የምድሪቱን አብዛኛውን ክፍል ተቆጣጠሩ፤ ኢያሱ 11:23፤
በሐዋርያት ሥራ 13:17-20 ላይ የተጠቀሰው ኢያሱ 14:7, 10-15
“450 ዓመት ያህል” የተባለው ጊዜ አበቃ፤
1450 ዓ.ዓ. ገ. የኢያሱ መጽሐፍ ተጽፎ ተጠናቀቀ ኢያሱ 1:1፤ 24:26
ኢያሱ ሞተ ኢያሱ 24:29
1107 ዓ.ዓ. ዳዊት በቤተልሔም ተወለደ 1ሳሙ 16:1
1100 ዓ.ዓ. ገ. ሳሙኤል የመሳፍንት መጽሐፍን ጽፎ አጠናቀቀ መሳ 21:25
1090 ዓ.ዓ. ገ. ሳሙኤል የሩት መጽሐፍን ጽፎ አጠናቀቀ ሩት 4:18-22
1078 ዓ.ዓ. ገ. የአንደኛ ሳሙኤል መጽሐፍ ተጽፎ ተጠናቀቀ 1ሳሙ 31:6
1077 ዓ.ዓ. ዳዊት በኬብሮን የይሁዳ ንጉሥ ሆነ 2ሳሙ 2:4
1070 ዓ.ዓ. ዳዊት በመላው እስራኤል ላይ ንጉሥ ሆነ፤ 2ሳሙ 5:3-7
ኢየሩሳሌምን ዋና ከተማው አደረጋት
1040 ዓ.ዓ. ገ. ጋድ እና ናታን የሁለተኛ ሳሙኤል መጽሐፍን 2ሳሙ 24:18
ጽፈው አጠናቀቁ
1037 ዓ.ዓ. ሰለሞን ዳዊትን ተክቶ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ 1ነገ 1:39፤ 2:12
1034 ዓ.ዓ. ሰለሞን ቤተ መቅደሱን መገንባት ጀመረ 1ነገ 6:1
1027 ዓ.ዓ. በኢየሩሳሌም የተካሄደው የቤተ መቅደስ ግንባታ ተጠናቀቀ 1ነገ 6:38
1020 ዓ.ዓ. ገ. ሰለሞን መኃልየ መኃልይን ጽፎ አጠናቀቀ መኃ 1:1
ከ1000 ዓ.ዓ. በፊት ሰለሞን መክብብ መጽሐፍን ጽፎ አጠናቀቀ መክ. 1:1
997 ዓ.ዓ. ሮብዓም በሰለሞን ምትክ ነገሠ፤ መንግሥቱ ተከፈለ፤ 1 ነገ. 11:43፤
ኢዮርብዓም የእስራኤል ንጉሥ ሆኖ መግዛት ጀመረ 1 ነገ. 12:19, 20
993 ዓ.ዓ. ሺሻቅ ይሁዳን ወርሮ ከቤተ መቅደሱ ውድ ነገሮችን ወሰደ 1 ነገ. 14:25, 26
980 ዓ.ዓ. አብያም (አብያ) በሮብዓም ምትክ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ 1 ነገ. 15:1, 2
977 ዓ.ዓ. አሳ በአብያም ምትክ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ 1 ነገ. 15:9, 10
976 ዓ.ዓ. ገ. ናዳብ በኢዮርብዓም ምትክ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ 1 ነገ. 14:20
975 ዓ.ዓ. ገ. ባኦስ በናዳብ ምትክ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ 1 ነገ. 15:33
952 ዓ.ዓ. ገ. ኤላ በባኦስ ምትክ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ 1 ነገ. 16:8
951 ዓ.ዓ. ገ. ዚምሪ በኤላ ምትክ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ 1 ነገ. 16:15
ኦምሪ እና ቲብኒ በዚምሪ ምትክ የእስራኤል ነገሥታት ሆኑ 1 ነገ. 16:21
947 ዓ.ዓ. ገ. ኦምሪ ብቻውን የእስራኤል ንጉሥ ሆኖ መግዛት ጀመረ 1 ነገ. 16:22, 23
940 ዓ.ዓ. ገ. አክዓብ በኦምሪ ምትክ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ 1 ነገ. 16:29
936 ዓ.ዓ. ኢዮሳፍጥ በአሳ ምትክ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ 1 ነገ. 22:41, 42
919 ዓ.ዓ. ገ. አካዝያስ በአክዓብ ምትክ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ 1 ነገ. 22:51, 52
917 ዓ.ዓ. ገ. ኢዮራም በአካዝያስ ምትክ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ 2 ነገ. 3:1
913 ዓ.ዓ. ኢዮራም ‘የይሁዳ ንጉሥ’ ሆኖ ከኢዮሳፍጥ ጋር 2 ነገ. 8:16, 17
መግዛት ጀመረ
906 ዓ.ዓ. ገ. አካዝያስ በኢዮራም ምትክ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ 2 ነገ. 8:25, 26
905 ዓ.ዓ. ገ. ንግሥት ጎቶልያ የንግሥና ሥልጣን በመንጠቅ 2 ነገ. 11:1-3
በይሁዳ ላይ መግዛት ጀመረች
ኢዩ በኢዮራም ምትክ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ 2 ነገ. 9:24, 27፤ 10:36
898 ዓ.ዓ. ኢዮዓስ በአካዝያስ ምትክ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ 2 ነገ. 12:1
876 ዓ.ዓ. ኢዮዓካዝ በኢዩ ምትክ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ 2 ነገ. 13:1
859 ዓ.ዓ. ገ. ኢዮዓስ በኢዮዓካዝ ምትክ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ 2 ነገ. 13:10
858 ዓ.ዓ. አሜስያስ በኢዮዓስ ምትክ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ 2 ነገ. 14:1, 2
844 ዓ.ዓ. ገ. ዳግማዊ ኢዮርብዓም በኢዮዓስ ምትክ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ 2 ነገ. 14:23
ዮናስ፣ የዮናስ መጽሐፍን ጽፎ አጠናቀቀ ዮናስ 1:1, 2
829 ዓ.ዓ. ዖዝያ (አዛርያስ) በአሜስያስ ምትክ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ 2 ነገ. 15:1, 2
820 ዓ.ዓ. ገ. የኢዩኤል መጽሐፍ የተጻፈው በዚህ ጊዜ ሳይሆን አይቀርም ኢዩ. 1:1
804 ዓ.ዓ. ገ. አሞጽ፣ የአሞጽ መጽሐፍን ጽፎ አጠናቀቀ አሞጽ 1:1
792 ዓ.ዓ. ገ. ዘካርያስ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ (6 ወራት) 2 ነገ. 15:8
791 ዓ.ዓ. ገ. ሻሉም በዘካርያስ ምትክ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ 2 ነገ. 15:13, 17
መናሄም በሻሉም ምትክ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ
780 ዓ.ዓ. ገ. ፈቃህያህ በመናሄም ምትክ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ 2 ነገ. 15:23
778 ዓ.ዓ. ገ. ፋቁሄ በፈቃህያህ ምትክ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ 2 ነገ. 15:27
778 ዓ.ዓ. ገ. ኢሳይያስ የነቢይነት ተልዕኮውን ማከናወን ጀመረ ኢሳ. 1:1፤ 6:1
777 ዓ.ዓ. ኢዮዓታም በዖዝያ (አዛርያስ) ምትክ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ 2 ነገ. 15:32, 33
761 ዓ.ዓ. ገ. አካዝ በኢዮዓታም ምትክ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ 2 ነገ. 16:1, 2
758 ዓ.ዓ. ገ. ሆሺአ የእስራኤል ንጉሥ ሆኖ መግዛት ጀመረ 2 ነገ. 15:30
745 ዓ.ዓ. ሕዝቅያስ በአካዝ ምትክ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ 2 ነገ. 18:1, 2
ከ745 ዓ.ዓ. በኋላ ሆሴዕ፣ የሆሴዕ መጽሐፍን ጽፎ አጠናቀቀ ሆሴዕ 1:1
740 ዓ.ዓ. አሦር እስራኤልን ድል አደረገ፣ ሰማርያን ተቆጣጠረ 2 ነገ. 17:6, 13, 18
732 ዓ.ዓ. ሰናክሬም ይሁዳን ወረረ 2 ነገ. 18:13
ከ732 ዓ.ዓ. በኋላ ኢሳይያስ፣ የኢሳይያስ መጽሐፍን ጽፎ አጠናቀቀ ኢሳ. 1:1
ከ717 ዓ.ዓ. በፊት ሚክያስ፣ የሚክያስ መጽሐፍን ጽፎ አጠናቀቀ ሚክ. 1:1
717 ዓ.ዓ. ገ. የምሳሌ መጽሐፍን የማጠናቀሩ ሥራ ተጠናቀቀ ምሳሌ 25:1
716 ዓ.ዓ. ምናሴ በሕዝቅያስ ምትክ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ 2 ነገ. 21:1
661 ዓ.ዓ. አምዖን በምናሴ ምትክ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ 2 ነገ. 21:19
659 ዓ.ዓ. ኢዮስያስ በአምዖን ምትክ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ 2 ነገ. 22:1
ከ648 ዓ.ዓ. በፊት ሶፎንያስ፣ የሶፎንያስ መጽሐፍን ጽፎ አጠናቀቀ ሶፎ. 1:1
647 ዓ.ዓ. ኤርምያስ የነቢይነት ተልዕኮውን ተቀበለ ኤር. 1:1, 2, 9, 10
ከ632 ዓ.ዓ. በፊት ናሆም፣ የናሆም መጽሐፍን ጽፎ አጠናቀቀ ናሆም 1:1
632 ዓ.ዓ. ነነዌ በከለዳውያን እና በሜዶናውያን እጅ ወደቀች ናሆም 3:7
ባቢሎን የዓለም ኃያል መንግሥት ሆነች
628 ዓ.ዓ. ኢዮዓካዝ በኢዮስያስ ምትክ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ 2 ነገ. 23:31
ኢዮዓቄም በኢዮዓካዝ ምትክ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ 2 ነገ. 23:36
628 ዓ.ዓ. ገ. ዕንባቆም፣ የዕንባቆም መጽሐፍን ጽፎ አጠናቀቀ ዕን. 1:1
625 ዓ.ዓ. ናቡከደነጾር (ዳግማዊ) የባቢሎን ንጉሥ ሆነ፤ ኤር. 25:1
የግዛት ዘመኑ የሚቆጠረው ከ624 ዓ.ዓ. አንስቶ ነው
620 ዓ.ዓ. ናቡከደነጾር፣ ኢዮዓቄም እንዲገብርለት አደረገ 2 ነገ. 24:1
618 ዓ.ዓ. ከኢዮዓቄም በኋላ ዮአኪን የይሁዳ ንጉሥ ሆነ 2 ነገ. 24:6, 8
617 ዓ.ዓ. ናቡከደነጾር፣ የመጀመሪያዎቹን አይሁዳውያን ምርኮኞች ዳን. 1:1-4፤
ወደ ባቢሎን አጋዘ
ሴዴቅያስ የይሁዳ ንጉሥ እንዲሆን ተሾመ 2 ነገ. 24:12-18
613 ዓ.ዓ. ሕዝቅኤል ነቢይ ሆኖ ማገልገል ጀመረ ሕዝ. 1:1-3
609 ዓ.ዓ. ናቡከደነጾር፣ ለሦስተኛ ጊዜ በይሁዳ ላይ ዘመተ፤ 2 ነገ. 25:1, 2
በኢየሩሳሌም ላይ ከበባ ማድረግ ጀመረ
607 ዓ.ዓ. በአምስተኛው ወር (አብ)፣ ቤተ መቅደሱ ተቃጠለ 2 ነገ. 25:8-10፤
እንዲሁም ኢየሩሳሌም ጠፋች ኤር. 52:12-14
በሰባተኛው ወር፣ አይሁዳውያን ይሁዳን ትተው ሄዱ፤ 2 ነገ. 25:25, 26፤
“የተወሰኑት የአሕዛብ ዘመናት” መቆጠር የሚጀምሩት ሉቃስ 21:24
ከዚህ ጊዜ አንስቶ ነው
ኤርምያስ፣ ሰቆቃወ ኤርምያስን ጻፈ የሰቆቃወ
ኤርምያስ መግቢያ፣ ሰብዓ ሊቃናት
607 ዓ.ዓ. ገ. አብድዩ፣ የአብድዩ መጽሐፍን ጻፈ አብ. 1
591 ዓ.ዓ. ገ. ሕዝቅኤል፣ የሕዝቅኤል መጽሐፍን ጽፎ አጠናቀቀ ሕዝ. 40:1፤ 29:17
580 ዓ.ዓ. የአንደኛ እና የሁለተኛ ነገሥት እንዲሁም ኤር. 52:31፤
የኤርምያስ መጻሕፍት ተጽፈው ተጠናቀቁ 2 ነገ. 25:27
539 ዓ.ዓ. ባቢሎን በሜዶናውያን እና በፋርሳውያን እጅ ወደቀች፤ ዳን. 5:30, 31
ሜዶ ፋርስ አራተኛው የዓለም ኃያል መንግሥት ሆነ
537 ዓ.ዓ. ፋርሳዊው ቂሮስ፣ አይሁዳውያን ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመለሱ 2 ዜና 36:22, 23፤
ያስተላለፈው አዋጅ ተግባራዊ ሆነ፤ ኢየሩሳሌም ባድማ ሆና
ያሳለፈቻቸው 70 ዓመታት አበቁ ኤር. 25:12፤ 29:10
536 ዓ.ዓ. ገ. ዳንኤል፣ የዳንኤል መጽሐፍን ጽፎ አጠናቀቀ ዳን. 10:1
536 ዓ.ዓ. በዘሩባቤል መሪነት የቤተ መቅደሱ መሠረት ተጣለ ዕዝራ 3:8-10
522 ዓ.ዓ. ቤተ መቅደሱን የመገንባቱ ሥራ ታገደ ዕዝራ 4:23, 24
520 ዓ.ዓ. ሐጌ፣ የሐጌ መጽሐፍን ጽፎ አጠናቀቀ ሐጌ 1:1
518 ዓ.ዓ. ዘካርያስ፣ የዘካርያስ መጽሐፍን ጽፎ አጠናቀቀ ዘካ. 1:1
515 ዓ.ዓ. ዘሩባቤል የሁለተኛውን ቤተ መቅደስ ግንባታ አጠናቀቀ ዕዝራ 6:14, 15
475 ዓ.ዓ. ገ. መርዶክዮስ፣ የአስቴር መጽሐፍን ጽፎ አጠናቀቀ አስ. 3:7፤ 9:32
468 ዓ.ዓ. ዕዝራ እና ካህናቱ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ ዕዝራ 7:7
460 ዓ.ዓ. ገ. ዕዝራ፣ የአንደኛ እና ሁለተኛ ዜና መዋዕል እንዲሁም ዕዝራ 1:1፤
የዕዝራ መጻሕፍትን ጽፎ አጠናቀቀ፤ 2 ዜና 36:22
የመዝሙር መጽሐፍን የማጠናቀሩ ሥራ ተጠናቀቀ
ከ443 ዓ.ዓ. በኋላ ነህምያ፣ የነህምያ መጽሐፍን ጽፎ አጠናቀቀ ነህ. 5:14
ሚልክያስ፣ የሚልክያስ መጽሐፍን ጽፎ አጠናቀቀ ሚል. 1:1
406 ዓ.ዓ. ኢየሩሳሌምን እንደገና የመገንባቱ ሥራ እንደተጠናቀቀ ዳን. 9:25
ከሁኔታዎች መረዳት ይቻላል
332 ዓ.ዓ. አምስተኛው የዓለም ኃያል መንግሥት የሆነው ግሪክ ዳን. 8:21
ይሁዳን መግዛት ጀመረ
280 ዓ.ዓ. ገ. ግሪክኛውን ሰብዓ ሊቃናት የማዘጋጀቱ ሥራ ተጀመረ
165 ዓ.ዓ. ቤተ መቅደሱ በግሪክ የጣዖት አምልኮ ከረከሰ በኋላ ዮሐ. 10:22
እንደገና ተወሰነ፤ የመታደስ በዓል
37 ዓ.ዓ. ገ. ሄሮድስ (በሮም የተሾመ ንጉሥ) የኃይል እርምጃ በመውሰድ
ኢየሩሳሌምን በቁጥጥሩ ሥር አደረገ
2 ዓ.ዓ. አጥማቂው ዮሐንስ እና ኢየሱስ ተወለዱ ሉቃስ 1:60፤ 2:7
29 ዓ.ም. ዮሐንስ እና ኢየሱስ አገልግሎታቸውን ጀመሩ ሉቃስ 3:1, 2, 23
33 ዓ.ም. ኒሳን 14፣ ኢየሱስ መሥዋዕት በመሆን ለአዲሱ ቃል ኪዳን ሉቃስ 22:20፤ 23:33
መሠረት ጣለ፤ ተሰቀለ
ኒሳን 16፣ ኢየሱስ ከሞት ተነሳ ማቴ. 28:1-10
ሲዋን 6፣ መንፈስ ቅዱስ ፈሰሰ፤ ጴጥሮስ፣ አይሁዳውያን ሥራ 2:1-17, 38
በጴንጤቆስጤ ዕለት፣ ወደ ክርስቲያን ጉባኤ መግባት የሚችሉበት መንገድ ከፈተ
36 ዓ.ም. 70ዎቹ የዓመታት ሳምንታት አበቁ፤ ጴጥሮስ ዳን. 9:24-27፤
ቆርኔሌዎስ ከተባለው ካልተገረዙት አሕዛብ መካከል ሥራ 10:1, 45
ወደ ክርስትና ከመጣው የመጀመሪያው ሰው ጋር ተገናኘ
41 ዓ.ም. ገ. ማቴዎስ፣ የማቴዎስ ወንጌልን ጻፈ
47-48 ዓ.ም. ገ. ጳውሎስ፣ የመጀመሪያ ሚስዮናዊ ጉዞውን ጀመረ ሥራ 13:1–14:28
49 ዓ.ም. ገ. የበላይ አካሉ፣ ከአሕዛብ ወገን ለመጡት አማኞች ሥራ 15:28, 29
ግርዘትን በተመለከተ ውሳኔ አስተላለፈ
49-52 ዓ.ም. ገ. የጳውሎስ ሁለተኛ ሚስዮናዊ ጉዞ ሥራ 15:36–18:22
50 ዓ.ም. ገ. ጳውሎስ በቆሮንቶስ ሆኖ 1 ተሰሎንቄን ጻፈ 1 ተሰ. 1:1
51 ዓ.ም. ገ. ጳውሎስ በቆሮንቶስ ሆኖ 2 ተሰሎንቄን ጻፈ 2 ተሰ. 1:1
50-52 ዓ.ም. ገ. ጳውሎስ በቆሮንቶስ ወይም በሶርያዋ አንጾኪያ ሆኖ ገላ. 1:1
ለገላትያ ክርስቲያኖች ደብዳቤ ጻፈ
52-56 ዓ.ም. ገ. የጳውሎስ ሦስተኛ ሚስዮናዊ ጉዞ ሥራ 18:23–21:19
55 ዓ.ም. ገ. ጳውሎስ በኤፌሶን ሆኖ 1 ቆሮንቶስን፣ 1 ቆሮ. 15:32፤
በመቄዶንያ ሆኖ ደግሞ 2 ቆሮንቶስን ጻፈ 2 ቆሮ. 2:12, 13
56 ዓ.ም. ገ. ጳውሎስ በቆሮንቶስ ሆኖ ለሮም ክርስቲያኖች ደብዳቤ ጻፈ ሮም 16:1
56-58 ዓ.ም. ገ. ሉቃስ፣ የሉቃስ ወንጌልን ጻፈ ሉቃስ 1:1, 2
60-61 ዓ.ም. ገ. ጳውሎስ በሮም ሆኖ የሚከተሉትን ደብዳቤዎች ጻፈ፦
ኤፌሶን ኤፌ. 3:1
ፊልጵስዩስ ፊልጵ. 4:22
ቆላስይስ ቆላ. 4:18
ፊልሞና ፊልሞና 1
61 ዓ.ም. ገ. ጳውሎስ በሮም ሆኖ ለዕብራውያን ክርስቲያኖች ደብዳቤ ጻፈ ዕብ. 13:24፤ 10:34
ሉቃስ በሮም ሆኖ የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍን ጽፎ አጠናቀቀ
ከ62 ዓ.ም. በፊት የኢየሱስ ወንድም የሆነው ያዕቆብ በኢየሩሳሌም ሆኖ ያዕ. 1:1
“ያዕቆብ” በሚል ስም የሚጠራውን ደብዳቤውን ጻፈ
60-65 ዓ.ም. ገ. ማርቆስ፣ የማርቆስ ወንጌልን ጻፈ
61-64 ዓ.ም. ገ. ጳውሎስ በመቄዶንያ ሆኖ 1 ጢሞቴዎስን ጻፈ 1 ጢሞ. 1:3
ጳውሎስ በመቄዶንያ (?) ሆኖ ቲቶን ጻፈ ቲቶ 1:5
62-64 ዓ.ም. ገ. ጴጥሮስ በባቢሎን ሆኖ 1 ጴጥሮስን ጻፈ 1 ጴጥ. 1:1፤ 5:13
64 ዓ.ም. ገ. ጴጥሮስ በባቢሎን (?) ሆኖ 2 ጴጥሮስን ጻፈ 2 ጴጥ. 1:1
65 ዓ.ም. ገ. ጳውሎስ በሮም ሆኖ 2 ጢሞቴዎስን ጻፈ 2 ጢሞ. 4:16-18
96 ዓ.ም. ገ. ዮሐንስ በጳጥሞስ ሳለ የራእይ መጽሐፍን ጻፈ ራእይ 1:9
98 ዓ.ም. ገ. ዮሐንስ፣ የዮሐንስ ወንጌልን እንዲሁም ዮሐ. 21:22, 23
1፣ 2 እና 3 ዮሐንስ ተብለው የሚጠሩትን ደብዳቤዎች ጻፈ፤
መጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ ተጠናቀቀ
100 ዓ.ም. ገ. በሕይወት የነበረው የመጨረሻው ሐዋርያ ማለትም ዮሐንስ ሞተ 2 ተሰ. 2:7
ማሳሰቢያ፦ በሠንጠረዡ ውስጥ የተጠቀሱት አብዛኞቹ ዓመታት ትክክለኛውን ጊዜ የሚጠቁሙ ቢሆንም አንዳንዶቹ ዓመታት ግን ካለው ማስረጃ አንጻር ሊሆን ይችላል ተብሎ የተገመተውን ጊዜ የሚያመለክቱ ናቸው። በዚህ ሠንጠረዥ ውስጥ የተጠቀሱት ጊዜያት ሊለወጡ የማይችሉ አይደሉም፤ ከዚህ ይልቅ ይህ ሠንጠረዥ የተዘጋጀው የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ክንውኖቹ በየትኛው ጊዜ ላይ እንደተፈጸሙ እንዲሁም በእነዚህ ጊዜያት መካከል ያለውን ተዛማጅነት እንዲያስተውሉ ለመርዳት ታስቦ ነው።
[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ ሠንጠረዥ]
የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት ሰንጠረዥ
(አንዳንዶቹ መጻሕፍት የተጻፉበት ጊዜ [እና ቦታ] በእርግጠኝነት አይታወቅም። ገ የሚለው ምልክት “ገደማ” ማለት ነው።)
የዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት (ዓመተ ዓለም)
የመጽሐፉ ስም ጸሐፊው የተጻፈበት ቦታ ተጽፎ የሚሸፍነው ጊዜ
ያለቀበት ጊዜ
ዘፍጥረት ሙሴ ምድረ በዳ 1513 “በመጀመሪያ” እስከ 1657
ዘፀአት ሙሴ ምድረ በዳ 1512 1657-1512
ዘሌዋውያን ሙሴ ምድረ በዳ 1512 1 ወር (1512)
ዘኁልቁ ሙሴ ምድረ በዳና የሞዓብ ሜዳ 1473 1512-1473
ዘዳግም ሙሴ ሞዓብ ሜዳ 1473 2 ወራት (1473)
ኢያሱ ኢያሱ ከነአን 1450 ገ. 1473-1450 ገ.
መሳፍንት ሳሙኤል እስራኤል 1100 ገ. 1450 ገ.–1120 ገ.
ሩት ሳሙኤል እስራኤል 1090 ገ. መሳፍንት የገዙባቸው
11 ዓመታት
1 ሳሙኤል ሳሙኤል፣ ጋድ፣ ናታን እስራኤል 1078 ገ. 1180 ገ.-1078
2 ሳሙኤል ጋድ፣ ናታን እስራኤል 1040 ገ. 1077–1040 ገ.
1 እና 2 ነገሥት ኤርምያስ ይሁዳ እና ግብፅ 580 1040 ገ.-580
1 እና 2 ዜና መዋዕል ዕዝራ ኢየሩሳሌም (?) 460 ገ. ከ1 ዜና 9:44 በኋላ
1077-537
ዕዝራ ዕዝራ ኢየሩሳሌም 460 ገ. 537–467 ገ.
ነህምያ ነህምያ ኢየሩሳሌም ከ443 በኋላ 456–ከ443 በኋላ
አስቴር መርዶክዮስ ሹሻን፣ ኤላም 475 ገ. 493–475 ገ.
ኢዮብ ሙሴ ምድረ በዳ 1473 ገ. በ1657 እና 1473
መካከል ከ140 ዓመት በላይ
መዝሙር ዳዊት እና ሌሎች 460 ገ.
ምሳሌ ሰለሞን፣ አጉር፣ ልሙኤል ኢየሩሳሌም 717 ገ.
መክብብ ሰለሞን ኢየሩሳሌም ከ1000 በፊት
መኃልየ መኃልይ ሰለሞን ኢየሩሳሌም 1020 ገ.
ኢሳይያስ ኢሳይያስ ኢየሩሳሌም ከ732 በኋላ ከ778 ገ.–ከ732 በኋላ
ኤርምያስ ኤርምያስ ይሁዳ እና ግብፅ 580 647-580
ሰቆቃወ ኤርምያስ ኤርምያስ ኢየሩሳሌም አቅራቢያ 607
ሕዝቅኤል ሕዝቅኤል ባቢሎን 591 ገ. 613–591 ገ.
ዳንኤል ዳንኤል ባቢሎን 536 ገ. 618–536 ገ.
ሆሴዕ ሆሴዕ ሰማርያ (አውራጃ) ከ745 በኋላ ከ804 በፊት–ከ745 በኋላ
ኢዩኤል ኢዩኤል ይሁዳ 820 ገ. (?)
አሞጽ አሞጽ ይሁዳ 804 ገ.
አብድዩ አብድዩ 607 ገ.
ዮናስ ዮናስ 844 ገ.
ሚክያስ ሚክያስ ይሁዳ ከ717 በፊት 777 ገ.-717
ናሆም ናሆም ይሁዳ ከ632 በፊት
ዕንባቆም ዕንባቆም ይሁዳ 628 ገ. (?)
ሶፎንያስ ሶፎንያስ ይሁዳ ከ648 በፊት
ሐጌ ሐጌ ኢየሩሳሌም 520 112 ቀናት (520)
ዘካርያስ ዘካርያስ ኢየሩሳሌም 518 520-518
ሚልክያስ ሚልክያስ ኢየሩሳሌም ከ443 በኋላ
የግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት ሠንጠረዥ (ዓመተ ምሕረት)
የመጽሐፉ ስም ጸሐፊው የተጻፈበት ቦታ ተጽፎ የሚሸፍነው ጊዜ
ያለቀበት ጊዜ
ማቴዎስ ማቴዎስ ፓለስቲና 41 ገ. 2 ዓ.ዓ.–33 ዓ.ም.
ማርቆስ ማርቆስ ሮም 60-65 ገ. 29-33 ዓ.ም.
ሉቃስ ሉቃስ ቂሳርያ 56-58 ገ. 3 ዓ.ዓ.–33 ዓ.ም.
ዮሐንስ ሐዋርያው ዮሐንስ ኤፌሶን ወይም 98 ገ. መግቢያውን ሳይጨምር፣
በአቅራቢያው 29-33 ዓ.ም.
ሥራ ሉቃስ ሮም 61 ገ. 33–61 ዓ.ም. ገ.
ሮም ጳውሎስ ቆሮንቶስ 56 ገ.
1 ቆሮንቶስ ጳውሎስ ኤፌሶን 55 ገ.
2 ቆሮንቶስ ጳውሎስ መቄዶንያ 55 ገ.
ገላትያ ጳውሎስ ቆሮንቶስ ወይም 50-52 ገ.
የሶርያዋ አንጾኪያ
ኤፌሶን ጳውሎስ ሮም 60-61 ገ.
ፊልጵስዩስ ጳውሎስ ሮም 60-61 ገ.
ቆላስይስ ጳውሎስ ሮም 60-61 ገ.
1 ተሰሎንቄ ጳውሎስ ቆሮንቶስ 50 ገ.
2 ተሰሎንቄ ጳውሎስ ቆሮንቶስ 51 ገ.
1 ጢሞቴዎስ ጳውሎስ መቄዶንያ 61-64 ገ.
2 ጢሞቴዎስ ጳውሎስ ሮም 65 ገ.
ቲቶ ጳውሎስ መቄዶንያ (?) 61-64 ገ.
ፊልሞና ጳውሎስ ሮም 60-61 ገ.
ዕብራውያን ጳውሎስ ሮም 61 ገ.
ያዕቆብ ያዕቆብ (የኢየሱስ ወንድም) ኢየሩሳሌም ከ62 በፊት
1 ጴጥሮስ ጴጥሮስ ባቢሎን 62-64 ገ.
2 ጴጥሮስ ጴጥሮስ ባቢሎን (?) 64 ገ.
1 ዮሐንስ ሐዋርያው ዮሐንስ ኤፌሶን ወይም በአቅራቢያው 98 ገ.
2 ዮሐንስ ሐዋርያው ዮሐንስ ኤፌሶን ወይም በአቅራቢያው 98 ገ.
3 ዮሐንስ ሐዋርያው ዮሐንስ ኤፌሶን ወይም በአቅራቢያው 98 ገ.
ይሁዳ ይሁዳ (የኢየሱስ ወንድም) ፓለስቲና (?) 65 ገ.
ራእይ ሐዋርያው ዮሐንስ ጳጥሞስ 96 ገ.