ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ማቴዎስ 25
“ዘወትር ነቅታችሁ ጠብቁ”
ኢየሱስ ስለ አሥሩ ደናግል የሚናገረውን ምሳሌ የጠቀሰው ለቅቡዓን ተከታዮቹ ቢሆንም መሠረታዊ ሐሳቡ ለሁሉም ክርስቲያኖች ይሠራል። (w15 3/15 12-16) “ቀኑንም ሆነ ሰዓቱን ስለማታውቁ ዘወትር ነቅታችሁ ጠብቁ” በማለት ተናግሯል። (ማቴ 25:13) ኢየሱስ የተናገረውን ይህን ምሳሌ ማብራራት ትችላለህ?
ሙሽራው (ቁጥር 1)—ኢየሱስ
ተዘጋጅተው ሲጠብቁ የነበሩት ልባሞቹ ደናግል (ቁጥር 2)—የተሰጣቸውን ሥራ በታማኝነት ለመወጣት ዝግጁ የሆኑትና እስከ መጨረሻው ድረስ እንደ ብርሃን አብሪዎች የሚያበሩት ቅቡዓን ክርስቲያኖች (ፊልጵ 2:15)
“ሙሽራው እየመጣ ነው” የሚለው ጫጫታ (ቁጥር 6)—የኢየሱስን መገኘት የሚያሳውቁ ማስረጃዎች
ሞኞቹ ደናግል (ቁጥር 8)—ሙሽራውን ለመቀበል ቢወጡም እስከ መጨረሻው ንቁዎች ያልሆኑና ንጹሕ አቋማቸውን ያልጠበቁ ቅቡዓን ክርስቲያኖች
ልባሞቹ ደናግል ዘይታቸውን ለመስጠት ፈቃደኞች አለመሆናቸው (ቁጥር 9)—የመጨረሻው ማኅተም ከተደረገ በኋላ ታማኞቹ ቅቡዓን፣ ታማኝነታቸውን ያጓደሉትን ቅቡዓን መርዳት አይችሉም፤ ምክንያቱም እንዲህ ማድረግ የሚችሉበት ጊዜ አልፏል
‘ሙሽራው መድረሱ’ (ቁጥር 10)—ወደ ታላቁ መከራ ማብቂያ አካባቢ ኢየሱስ ፍርድ ለመስጠት ይመጣል
ልባሞቹ ደናግል ከሙሽራው ጋር ወደ ሠርጉ ድግስ መግባታቸው፤ ከዚያም በሩ መዘጋቱ (ቁጥር 10)—ኢየሱስ ታማኝ ቅቡዓኑን ወደ ሰማይ ይሰበስባቸዋል፤ ታማኝ ያልሆኑት ቅቡዓን ግን ሰማያዊ ሽልማታቸውን ያጣሉ