ኢዮብ
17 “መንፈሴ ተሰብሯል፤ ዘመኔ አብቅቷል፤
መቃብር ይጠብቀኛል።+
3 እባክህ፣ መያዣዬን ተቀብለህ አንተ ዘንድ አስቀምጥልኝ።
እጄን የሚመታና ተያዥ የሚሆነኝ ሌላ ማን ይኖራል?+
4 ማስተዋልን ከልባቸው ሰውረሃልና፤+
ከዚህም የተነሳ ከፍ ከፍ አታደርጋቸውም።
5 የልጆቹ ዓይን ደክሞ እያለ፣
ያለውን ለወዳጆቹ ሊያካፍል ይችላል።
7 ከሐዘን የተነሳ ዓይኔ ፈዘዘ፤+
እጆቼና እግሮቼም እንደ ጥላ ሆኑ።
8 ቅን የሆኑ ሰዎች በዚህ ነገር በመገረም ትኩር ብለው ይመለከታሉ፤
ንጹሕ የሆነውም፣ አምላክ የለሽ* በሆነው ሰው ይረበሻል።
10 ይሁን እንጂ ሁላችሁም ተመልሳችሁ መከራከራችሁን መቀጠል ትችላላችሁ፤
ከእናንተ መካከል አንድም ጥበበኛ አላገኘሁምና።+
12 ሌሊቱን ወደ ቀን ይለውጣሉ፤
‘ጨለማ ስለሆነ ብርሃን የሚፈነጥቅበት ጊዜ ቀርቧል’ ይላሉ።
14 ጉድጓዱን*+ ‘አንተ አባቴ ነህ!’ እለዋለሁ፤
ትሏን ‘አንቺ እናቴና እህቴ ነሽ!’ እላታለሁ።
15 እንግዲህ የእኔ ተስፋ የት አለ?+
ተስፋ እንዳለኝ አድርጎ የሚያስብስ ማን ነው?