መዝሙር
118 ይሖዋ ጥሩ+ ስለሆነ ምስጋና አቅርቡለት፤
ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።
2 እስራኤል እንዲህ ይበል፦
“ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።”
3 ከአሮን ቤት የሆኑ እንዲህ ይበሉ፦
“ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።”
4 ይሖዋን የሚፈሩ እንዲህ ይበሉ፦
“ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።”
6 ይሖዋ ከጎኔ ነው፤ አልፈራም።+
ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?+
8 በሰው ከመታመን ይልቅ፣
ይሖዋን መጠጊያ ማድረግ ይሻላል።+
9 በመኳንንት ከመታመን ይልቅ፣
ይሖዋን መጠጊያ ማድረግ ይሻላል።+
11 ከበቡኝ፤ አዎ፣ ዙሪያዬን ከበቡኝ፤
እኔ ግን በይሖዋ ስም
መከትኳቸው።
12 እንደ ንብ ከበቡኝ፤
ሆኖም በእሳት እንደተያያዘ ቁጥቋጦ ወዲያውኑ ጠፉ።
እኔም በይሖዋ ስም
መከትኳቸው።+
13 እወድቅ ዘንድ በኃይል ተገፋሁ፤*
ይሖዋ ግን ረዳኝ።
14 ያህ መጠለያዬና ብርታቴ ነው፤
አዳኝም ሆኖልኛል።+
15 በጻድቃን ድንኳኖች ውስጥ፣
የሐሴትና የመዳን* ድምፅ ይሰማል።
የይሖዋ ቀኝ እጅ ኃይሉን ያሳያል።+
16 የይሖዋ ቀኝ እጅ ከፍ ከፍ አለ፤
የይሖዋ ቀኝ እጅ ኃይሉን ያሳያል።+
17 የያህን ሥራዎች አስታውቅ ዘንድ
በሕይወት እኖራለሁ እንጂ አልሞትም።+
19 የጽድቅን በሮች ክፈቱልኝ፤+
በዚያ ገብቼ ያህን አወድሳለሁ።
20 ይህ የይሖዋ በር ነው።
ጻድቃን በዚያ በኩል ይገባሉ።+
21 መልስ ስለሰጠኸኝና
አዳኝ ስለሆንከኝ አወድስሃለሁ።+
24 ይህ ይሖዋ የሠራው ቀን ነው፤
በዚህ ቀን እንደሰታለን፤ ሐሴትም እናደርጋለን።
25 ይሖዋ ሆይ፣ እባክህ እንድታድነን እንለምንሃለን!
ይሖዋ ሆይ፣ እባክህ ድል አቀዳጀን!
27 ይሖዋ አምላክ ነው፤
ብርሃን ይሰጠናል።+
28 አንተ አምላኬ ነህ፤ እኔም አወድስሃለሁ፤
አምላኬ ሆይ፣ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ።+